TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MinistryOfPeace

ለሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጥ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ሽልማት በሰላም ሚኒስቴር  ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ተሰጥቷል፡፡ የሰላም ቤተሰቦች መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማትም  ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሸልመዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-21-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MinistryOfPeace

በአፋር ክልል እና በሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረ ችግር በውይይት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሔ ዳይሬክተር ጄኔራል ምግባሩ አያሌው እንደገለፁት ሚኒስቴሩ ወደ ሁለቱ ክልሎች የላከው የልዑካን ቡድን የሁለቱን ክልሎች የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል።

ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው ግብረ ኃይል ለችግሩ እልባት ለመሻት መጠነ ሰፊ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተር ጀኔራሉ ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ጎን ለጎን በመሰጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አክለዋል። በዋናነት ለችግሩ እልባት ተሰጥቷል፤ በቀጣይነት ዘላቂ የሆነ ሰላም በአካባቢው እንዲኖር የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰራም ተናግረዋል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MinistryOfPeace

የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ ስርዓት አካል የሆነው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ስራ ሊገባ እንደሆነ አብስሯል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የቅድመ ማስጠንቀቂያው ስርዓት ማህበረሰቡን ከተለያዩ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ስርዓቱ የሙከራ ጊዜዉን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናቶች ውስጥ አገባዶ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

በመተከል ዞን ከ97 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

ከ58 ሺ በላይ ዜጎች ግልገል በለሰ ከተማ ይገኛሉ ፤ 39 ሺህ 679 ተፈናቃዮች በአማራ ክልል አዊ ብሔርስብ አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ።

ዜጎች ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ ያተደረገ ድጋፍ ፦

• በግልገል በለሰ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ33 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ ፣ 4 ሺ 38 ኩንታል ዓልሚ ምግብ እና 187 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

• አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ሺህ 404 ኩንታል ስንዴ እና 10 ሺህ 316 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

ይህ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ለአብመድ አሳውቋል። #MinistryOfPeace

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MinistryofPeace

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ዶክተር አኔቴ ዌበር ጋር ተወያይተዋል።

በውይይየታቸው ወ/ሮ ሙፈሪያት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ልማት በተለያዩ መስኮች እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ አመስግነዋል።

ዶ/ር አኔቴ ዌበር በበኩላቸው፥የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም ዘመናት የቆየውን መልካም የዲፕሎማሲያዊ እና የልማት ትብብር ለመቀጠል ያለውን ጠንካራ ፍላጎት መግለጻቸውን የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia