TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የስዋዚላንድ መንግስት የድግምትና ጥንቆላ ውድድር በሃገሪቱ ማገዱን ኤ ኤፍ ፒን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከጥንቆላና ጥንታዊ ከሆኑ ልማዶች ጋር የተያያዘ ድርጊት የሚከውኑ ግለሰቦች ከተገኙ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሃገሪቱ የመንግሰት ቃል-አቀባይ ፐርሲ ሲመላኔ መናገራቸውን በዘገባው ተመልክቷል፡፡

በሳምንቱ መጨረሻም በሃገሪቱ የሚገኙ የድግምት ፈዋሾች የእርስ በርስ የጥንቆላና ድግምት ፉክክር ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው እንደነበር አጃንስ ፋራንስ ፕሬስ በዘገባው ጠቅሷል።

የአፍሪካ ጋማ የተሰኘው የጥንት አባቶች ባህላዊ የፈውስ ፉክክር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሊዘጋጅ እንደነበርም ታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድን በዋቢነት በመጥቀስ ዘገባው አመልክቷል።

ባህላዊ ፈዋሽ የነበረው ሚስተር ጋማ እኤአ በ1982 ህልፈተ ህይወታቸው በተሰማው በዳግማዊ ሶቡዛ የንግስና ዘመን ተመሳሳይ በሆነ ውድድር ላይ ተሳትፎ ያደርጉ እንደነበርም ታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድ አክሏል።

ንጉሱ ይህን #እርምጃ ለመውሰድ የወሰኑት አንዳንድ ሃሰተኛ ፈዋሾችን ለማጥፍት ፈልገው ይሆናል፤ ነገር ግን ይህን ትክክለኛ ውድድር ባልተደራጀ ሁኔታ መከልከል ተገቢ አይደለም ሲሉሚስተር ጋማ መናገራቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡

Via #BBC/#ENA
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

ሰላምን ባህል ማድረግ የሰላም ጥቅምን በመገንዘብ ለሰላም ምቹ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ በትኩረት መንቀሳቀስ ሲቻል ነው፡፡

ሰላም ካለ፡-

•ለውጥና እድገት ማምጣት፤
•ከአድሏዊ አሰራር ነጻ መሆን፤
•ግጭትን በውይይት መፍታት፤
•ከማህበራዊ መፈረካከስ ወደ አንድነት መምጣት፤
•ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎን ማሳደግ፤
•ነፃ አስተሳሰብን ማዳበር፤
•የተፈጥሮ ደህንነትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ሰላማችን ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማረሚያ ቤቶችና የታራሚዎች አያያዝ #ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አደገኛ እፅ ሲያዘዋውር የተገኘው #ኢትዮጲያዊ ወጣት በእስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ ታፈሰ ተስፋየ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 (1ለ) ስር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመተላለፍ አደገኛ እፅችን በማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡

ተከሳሽ ታህሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 5 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ለመሄድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ከደረሰ በኋላ ለመብረር በዝግጅት ላይ እንዳለ በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ እፅ ክትትልና ቁጥጥር ዲቪዥን አባሎች በተደረገ ፍተሻ በያዘው የጀርባ ቦርሳ ውስጥ በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ክብደቱ 3 ኪ.ግ የሆነ የኮኬይን ዕፅ ይዞ መገኘቱን በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡

ተከሳሽ በኢትዮጲያ ደረጃ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወር እንዲሁም በጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለ እፅ ይዞ በመገኘቱ በፈፀመው መርዛማ እፆችን ይዞ በመገኘትና በማዘዋወር ወንጀል መከሰሱን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያብራራል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽን ጥፋተኛ የሚያስብሉ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤቶችን፣ የሰውና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን በግብዓትነት በመጠቀም ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ተከራክሯል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ተኛ የወንጀል ችሎት ሀምሌ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማክሸፉን አስታወቀ። ምክር ቤቱ በሀገሪቱ የመንግሥት ቴሌቪዥን ባቀረበው መግለጫ እንዳለው ከከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ጋር በተገናኘ 16 ወታደራዊ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ጀኔራል ጀማል ኦማር በመግለጫቸው መፈንቅል መንግስት የተሞከረው በተወሰኑ ወታደራዊ መኮንኖች፣ የደህንነት አባላት እና ከሃላፊነት የተሰናበቱ አካላት መሆኑን ተናግረዋል።

መፈንቅል መንግስቱ መቼ እንደተሞከረ ያልተናገሩት ጀኔራሉ፥ በመደበኛ ወታደራዊ ሃይሉ መክሸፉን ነው ያነሱት። ሴራውን በማቀነባበር የተሳተፉ ተጨማሪ ሃይሎችን ለመያዝም ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ጀኔራል ኦማር ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት እና የተቃዋሚ ሃይሎች ሀገሪቱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመራ የሽግግር ምክር ቤት ለማቋቋም መስማማታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦አል ጄዚራ
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2011 የትምህርት ዘመን በተፈጠሩ ተፈጥሯዊ እና ሰውሰራሽ ችግሮች ምክንያት ከ300ሺ በላይ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን ሳይከታተሉ እንደቀሩ ማወቅ ተችሏል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍም ትምህርት ሚኒስተር ከበጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጋር በመተባበር በመደበኛው የትምህርት ጊዜ ውስጥ መስጠት ያልተቻለውን ትምህርት በክረምቱ ወቅት ለመሸፈን እየሰራ እንዳለ አሳውቋል፡፡ በዚህ የበጎፍቃድ ዘመቻ ውስጥ ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ተማሪዎቹ የደረሰባቸውን የስነ-ልቦና ጉዳት ጭምር ታይቶ ይህንን ችግር የሚቀርፍ የስነ-ልቦና ሥልጠናዎችና የማነቃቂያ ንግግሮች ተካተውበታል፡፡

ሥራው በተሻለና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ሲሆን በጎፈቃደኞችም በዚሁ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ተማሪዎቹን በትምህርት ቁሳቁስ ለመደገፍ ቀደም ተብሎ የገቢ ማሰባሰቢያዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ የፕሮግራሙ አስተባባሪ እንደገለጹት የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን በሚያስመርቅበት ወቅት ይህንን ሥራ ለመደገፍ የሚውል የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራና ሁሉም ወላጅ ከትምህርታቸው የተስተጓጎሉትን ተማሪዎች እንደ ልጆቻቸው በመቁጠር ልጃቸው የደረሰበት ደረጃ እንዲደርሱና ከትምህርት ሕይወታቸው እንዳይስተጓጎሉ በሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ በዚህ ዙሪያ በቀጣይም ያሉትን ሥራዎች እየተከታተልን ለናንተው ለቤተሰቦቻችን የምናደርስ ይሆናል፡፡

Via TIKVAH-ETH
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰት ነው!

አርቲስት ሄለን በድሉ #በባለቤቷ የአሲድ ጥቃት ደረሰባት ተብሎ በፌስቡክ መንደር የሚመላለሰው ወሬ ሀሰት ነው።

Via #GetuTemsgen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢህአዴግ ከአባል ፓርቲዎቹ መግለጫ በኋላ ወዴት ያመራል?

የኢህአዴግ ዕጣ

ኢህአዴግ በድሮ ግርማ ሞገሱ አለን?

ክልሎች ግጭት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ?

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አብሮ መስራት

ኢህአዴግ ምን ያድርግ?

ተከታዩን የቢቢሲ አማርኛ ዘገባ የንብቡ👇
--- https://telegra.ph/EPRDF-07-12 ---
#update ጨፌ ኦሮሚያ ከሃምሌ 7 እስከ ሃምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡ በጉባኤው በክልሉ የ70 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነአቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ ላይ የቀሪ አንድ ምስክርን ቃል ዛሬ ረፋድ ሰምቷል፡፡ ዐቃቢ ሕግ በተከሳሾች ላይ የሰነድ ማስረጃ እና የሰው ምስክሮችን አቅርቦ ካሰማ በኋላ ፍርድ ቤቱ የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ብይን እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በእነአቶ በረከትና አቶ ታደሰ የክስ መዝገብ ሦስተኛው ተከሳሽ ከጤና ችግር ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ተሻለ የሕክምና ተቋም እንዲላኩ ጠይቀዋል፡፡ እንደ አብመድ ዘገባ ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ ያቀረቡትን የሕክምና ማስረጃ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በ2011 በጀት አመት 198 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡንና ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ22 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

📎በ2012 በጀት ዓመት ሚኒስቴር መ/ቤቱ #በፓርላማ እንዲሰበሰብ የፀደቀለት የገቢ ዕቅድ 224 ቢሊየን ብር ሲሆን ይህን ዕቅድ በመለጠጥ 248 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ነድፎ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተደራጅታችሁ በሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ ብንባልም እስካሁን #መመሪያ ስላልተዘጋጀ ስራ ፈትተናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናገሩ፡፡ አስተዳደሩም መመሪያው #በቅርቡ ይወጣል ብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሥራ እድል የተመቻቸላቸው እና አስፈላጊውን መስፈርት ያሟሉ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በዛሬው እለት የቀጠር መዲና ዶሃ ገብተዋል። ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ፣ ቀጠር እና ዮርዳኖስ ጋር የስራ ስምምነት የተፈራረመ ቢሆንም ስምምነቱ ተግባራዊ ሳይሆን ረዥም ጊዜ ቆይቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ጉባኤ (Senate) ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው ስብስባ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ለሆኑት ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው በሚያካሂደው የምረቃ በዓል ላይ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጣቸው ወስኗል፡፡

የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ስነስርዓቱም ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓት በሚካሄድበት በሚሊኒየም አዳራሽ ይከናወናል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የቢሮ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አሁን ያለበት ህንፃ ለሌላ አላማ የተገነባ እና ለሚዲያ ስራ አመቺ ባለመሆኑ አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታ ለማካሄድ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

በተቋሙ ስር ያሉ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ችግር እና በሌሎች የሎጂስቲክ እጥረቶች ዙሪያም የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ስራ አስኪያጁ ለኢ/ር ታከለ ኡማ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኩል ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

ለኮርፖሬሽኑ አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ የግንባታ ቦታ የከተማ አስተዳደሩ አመቺ የሆነ ቦታ እንደሚሰጥም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ከሁለቱ አካላት የተውጣጡ 4 አባላትን የያዘ ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ያዘጋጀውና ''ለኢንዱስትሪ ልማት እንሩጥ'' በሚል መሪ ቃል እሁድ ሀምሌ 7/2011 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው 3ኛው ዙር የአምስት ኪ.ሜ የኢትዮጵያ የቢዝነስ ሩጫ መራዘሙን ም/ቤቱ አስታወቀ። ም/ቤቱ ለኢፕድ በላከው መግለጫ በመስቀል አደባባይ ሩጫውን ለማካሄድ የዝግጅት #መደራረብና ፈቃድ ባለማግኘት ምክንያት ፕሮግራሙ ወደ ሀምሌ 14/2011 ዓ.ም መተላለፉን አስታውቋል።

አዝናኝ እና ለጤና አስተዋፅዖ ባለው ስፖርታዊ ሁነት መላው ማህበረሰብ በተለይም የግሉ ዘርፍ አባላት በኢንዱስትሪ ልማት ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ጎልብቶ በዘርፉ ያላቸው ሚና እና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ የሩጫ ፕሮግራም ለሶስተኛ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን በዚህም ም/ቤቱ ይቅርታ ጠይቋል። የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በፕሮግራሙ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ም/ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ኮማንድ ፖስት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፦

በአማራና ቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ ከሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይና በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር የሚደረግበት ኮማንድ ፖስት ተግባራዊ እንዲደረግ ተወሰነ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CP-07-12
ከኮማንድ ፖስት የተሰጠ መግለጫ👉https://telegra.ph/CP-07-12-2
#update ቦይንግ ኩባንያ በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ በደረሱት አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች 100 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መድቤያለሁ ቢልም ባለ ጉዳዮቹ ግን ስለ ካሳው የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡ ቦይንግ እነማንን ለካሳው እንደሚመርጥም አልታወቀም፡፡ ካሳይ ከፋዮቹ ከአየር መንገዶቹ ሳይሆን የአውሮፕላኑ አምራች መሆኑም ያልተለመደ ነው- ብሏል ሮይተርስ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ስለ ካሳው ምንም መረጃ የለንም ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያና ኬንያ መንግሥታትም ከቦይንግ ጋር ስለ ጉዳዩ አልተነጋገሩም፡፡ አውሮፕላኑ የተከሰከሰባቸው ሰፊ ማሳዎች ባለቤት አርሶ አደሮችም ማሳዎቻቸው እስካሁን ታጥረው ያሉ ሲሆን ካሳ ስለመፈቀዱ በይፋ የሰሙት ነገር የለም፡፡

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ያወጣው መመሪያ የህግ ክፍተት እንዳለበት የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አስታወቀ።

ተጭማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CONDO-07-12