አደገኛ እፅ ሲያዘዋውር የተገኘው #ኢትዮጲያዊ ወጣት በእስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ ታፈሰ ተስፋየ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 (1ለ) ስር የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት በመተላለፍ አደገኛ እፅችን በማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ታህሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 5 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ለመሄድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ከደረሰ በኋላ ለመብረር በዝግጅት ላይ እንዳለ በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ እፅ ክትትልና ቁጥጥር ዲቪዥን አባሎች በተደረገ ፍተሻ በያዘው የጀርባ ቦርሳ ውስጥ በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ክብደቱ 3 ኪ.ግ የሆነ የኮኬይን ዕፅ ይዞ መገኘቱን በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡
ተከሳሽ በኢትዮጲያ ደረጃ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወር እንዲሁም በጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለ እፅ ይዞ በመገኘቱ በፈፀመው መርዛማ እፆችን ይዞ በመገኘትና በማዘዋወር ወንጀል መከሰሱን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያብራራል፡፡
ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽን ጥፋተኛ የሚያስብሉ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤቶችን፣ የሰውና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን በግብዓትነት በመጠቀም ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ተከራክሯል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ተኛ የወንጀል ችሎት ሀምሌ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia