TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TPLF/ህወሓት እና #ADP/አዴፓ

"አሁን የአዴፓ ድርጀት የራሱን ትላልቅ ጓዶች የገደለ ሃይል ማውገዝ አቅቶት በአርበኝነት ተረት ለመፍጠር ሲሞክር ስታይ ወይ ተምታትቶበታል ወይም ድርጅቱ የሆነ ነገር ይበል፡፡የራስህ ጓዶች የገደለን ሰው አርበኛ ነው ጀግና ነው ማለት የጀመረ ድረጅት በግሌ አጠገቡ መቀመጥ ይከብደኛል፡፡እና የሄንን በደንብ አጥርቶ ይምጣ ነው ያልነው፡፡አሰላለፍ ማለት እሱ ነው፡፡ስለአሰላለፍ ስታወራ እገሌ ጀግና ነው እገሌ አንዲህ ነበረ ኣይደለም የምትለው፡፡ #አምባቸው_መኮነን ህዝብ የመረጠው የአማራ ክልል መሪ ነው፣ምግባሩ ከበደ በህዝብ የተመረጠ የአማራ ክልል መሪ ነው፣ሌሎቸም እነዚህ ሰዎች በጠራራ ፀሃይ የገደለ ሰው አርበኛ ነው፣አንበሳ ነበረ ማለት ትክክል ኣይደለም ፡፡ አሁን በዚህ ግርግር ውስጥ በኣደባባይ ሰውን የገደለ ላለማውገዝ ተረት የሚፈጥር አመራር ፣እኔ እንደ ጓድ ፣ የሞቱት ጓዶቼ ናቸው የሄን ዓይነት አቋም የሚያሳይ ድርጅትጋር አብረን ለመጓዝ እርግጠኞች መሆን አንቸልም የሚል የአቋም መግለጫ መስጠት ጤነኝነት ነው፡፡ለድርጅቱም ማዘን ንው፡፡" አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢሳት ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

ምንጭ፦ TPLF ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነገ ሐምሌ 06/2011 በባሕር ዳር ስብሰባውን እንደሚጀምር ታውቋል። #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ሰኔ 15 በነበረው የፀጥታ ችግር ከታሰሩ 218 ተጠርጣሪዎች መካከል 113ቱ መፈታታቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ እስከሚካሂድ ድረስ ከተማዋን ማስተደደሬን እቀጥላለሁ ብሏል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-07-12-4
ኢትዮ ቴሌኮም የአዲስ በጀት ዓመትን መጀመር አስመልክቶ ደንበኞችን ለማመስገን ለሦስት ቀናት የሚቆይ የኢንተርኔት ፣ የአጭር የጽሁፍ መልእክት እና የድምጽ አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል ድርጅቱ #ወደፊትም ይህን አሰራር ተግባራዊ ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

"ይህች ሃገር የቆመችው #በጠመንጃ ብዛት ሳይሆን በህዝቦቿ ፀሎት ነው፤ በእስልምና እና በክርስትና ሃይማኖት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በየ ቤተ-እምነታችሁ ለሃገራችሁ ፀሎት አድርጉ፤ ልጆቻችሁንም ስለ ሃገር ፍቅር ስለ አንድነት አስተምሩ!" ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ

ሰላማችን ህልውናችን ነው!!
ሰላም እደሩ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀገራችን የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት #እያስመረቁ ይገኛሉ።

🎓TIKVAH-ETH ለመላው ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡

🗞ቀን ሃምሌ 6/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9637 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በ10 ኮሌጆችና 12 ትምህርት ቤቶቹ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 9637 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 2763 ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው 5876 ተማዎችን በመደበኛ ፕሮግራም፣ የቀሩትን 3761 ተማሪዎችን ደግሞ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 230ዎቹ በሶስተኛ ድግሪ የተመረቁ ናቸው።

ከእነዚህም 2085 ተማሪዎችን በማታ ፕሮግራም፣ 319 ተማሪዎችን በርቀት እንዲሁም 1995 ተማሪዎችን ደግሞ በክረምት ፕሮግራም ነው አሰልጥኖ ዛሬ ያስመረቀው።

በተጨማሪም ለአገሪቷ ሰፊ ግልጋሎት በመስጠት ለሚታወቁት ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንዲሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም የክብር ዶክተሬት ማዕረግ ሰጥቷል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን አጠቃላይ ከ32 ዩኒቨርሲቲዎች 120 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመረቁም ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ተመራቂ ተማሪዎች ለሀገር በመስራት ብድሯን መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 9 ሺህ 637 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ወላጆች ማየት የሚፈልጉት የተመራቂ ተማሪዎችን ስኬት ነው ያሉ ሲሆን፥ ተመራቂ ተማሪዎችም ወላጆቸውን ማስታወስ ይገባቸዋል ብለዋል።

እንዲሁም ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ያሉ መምህራኖቻቸውን ሊያስታውሱ እንደሚገባ እና እነሱን ሊያስደስቱ የሚችሉ ተግባራትን እንዲፈፅሙ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመራቂ ተማሪዎች በማንኛውም ጉዳች ሊደራደሩ ይገባል ያሉት ሲሆን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ግን ድርድር አያስፈልግም ብለዋል።

ለተመራቂ ተማሪዎች መልካም ምኞታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዩኒቨርስቲዎች የምርምር፣ የተለያዩ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባቸው እና ጥልቅ ትንተና የሚካሄድባቸው ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ተመራቂዎችም የአገልግሎት መርሆችን፣ መስጠት፣ ፍቅር እና በህይወት ዘመን ለመማር ዝግጁ መሆንን ሊከተሉ ይገባል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 9 ሺህ 637 ተማሪዎችን ባስመረቀበት ወቅት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
''ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው'' ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
_______________________________________________

ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 9 ሺህ 637 ተማሪዎች ዛሬ ባስመረቀበት ወቅት ነው።

በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩ ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው ብለዋል።

ተመራቂዎቹ እዚህ ለመድረስ ሳይማሩ ያስተማሯቸው ቤተሰቦቻቸው፣ በብዙ መስዋእት ያስተማሯቸው አስተማሪዎቻቸው እና ከበጀቷ ትልቁን በጀት የመደበችላቸው ሀገራቸው ብዙ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ እንደከፈለችላቸው ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኑሮ ቀንበር ሳይደናገጡ የተከፈለላቸውንም ዋጋ ዋጋ ሳያሳጡ እዚህ መድረሳቸው ለትውልድ መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደሚቻል ማሳያም ነው ብለዋል፡፡

ትልቁ እውቀትን መሸመቻ መድረክ ትምህርት ቤት ቢሆንም ተመራቂዎች ከዩኒቨርስቲ ለቀው ቢውጡም ትምህርት እንደማያቆም የተናገሩት ዶክተር አብይ ተማሪዎቹ ለትዳር፣ ለስራ እንዲሁም ለህይወት ፈተናና ትምህርት እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በቂ ናት ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ለሆኑት ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል፡፡ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና አቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን ከጠ/ሚር አብይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረ_ብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

ተመራቂዎች በኢትዮጵያ እየታዬ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና ዘረኝነት እንዲታገሉ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳሰበ፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተከታታይ ሶስትና ከዚያ በላይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 64 ተማሪዎች ማስመረቁ ታውቋል፤ 1 ሺህ 226 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ ተመራቂዎች ያካበቱትን እውቀት ተጠቅመው ሕዝባቸውን እና ሀገራቸውን በታማኝነት እና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየታዬ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና ዘረኝነት ለመታገልም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮውን ሳይጨምር ከ26 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋቻሞ_ዩኒቨርሲቲ

ከ23,500 በላይ ተማሪዎችን በዋናው ግቢ፣ በዱራሜ፣ በንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል እያስተማረ የሚገኘው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ 3,144 ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ፕሮግራሞችና ሰባት የትምህርት አይነቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ሰለጠናቸውን 198 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነስርዐቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ‘’ተመራቂዎች የሀገራችሁና የራሳችሁ ህይወት ብሩህ እንዲሆን በሀገርና ወገን ፍቅር በማስተዋልና በስራወዳድነት እንዲሁም በማንበብና በመማር ራሳችሁን በማነፅ እንድትኖሩ’’ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በ2009 ዓ.ም የማስተማር ስራውን የጀመረው ዩኒቨርሲቲው በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን አስተምሯል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ መርሃ ግብሮች ከመጀመሪይል እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ9 ሺ800 በላይ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት በዩኒቨርሲቲው ስታዲየም በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከል 28.4% የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ ተነግሯል። በዘንድሮ ዓመት በዩኒቨርሲቲው ለነበረው ፍፁም ሰላማዊ የመማር ማስተር ሂደት የከተማ ማህበረሰብ እንዲሁም አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላደረገው አስተዋፆ ምስጋና ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ11ኛው ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4000 በላይ ተማሪዎችን በድምቀት አስመርቋል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ሲሳተፉ ለነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ክቡር ዶክተር ዘብዲዮስ ጨማ ላለፉት 40 ዓመታት በወላይታ ባህል፣ ቋንቋ፣ እና በወላይታ ታሪክ ላይ በስፋት ለሰሯቸው ስራዎች የእውቅናና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ሌላኛው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው ኢትዮጵያዊ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገ/ወልድ ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ወልደሰማያት ገ/ወልድ 7ቱን የወላይታ ወረዳዎች በመቆርቆር የሚታወቁ የልማት አርበኛ እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል። ህይወታቸውን በሙሉ በወላይታ ውስጥ ሲሰሩ በነበሩ የልማት ስራዎች ላይ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፆ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት 4 ሺህ 44 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል👇
___ https://telegra.ph/WSU-07-13 _____
#update የኢፌደሪ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስቲትዩት በማስተርስ ዲግሪና በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 454 ተማሪዎችን አስመረቀ። ኢንስቲትዩቱ  በዕለቱ 218 ሴትና 1ሺህ 236 ወንድ ተማሪዎችን በማስተርስ ዲግሪና በመጀመሪያ ዲግሪ አሰልጥኖ አስመርቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅድመና በድህረ ምረቃ መርሀ ግብሮች ያስተማራቸውን ዘጠኝ ሺህ 860 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/HU-07-13-2
#Congratulations

በሐረር ከተማ የሚገኘው የሰዎች ለሰዎች የእርሻና የቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ለስድስተኛ ጊዜ #ያሰለጠናቸውን 198 ተማሪዎችን በመጀመርያ ድግሪ ዛሬ አስመርቋል። የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አትሌት ሻለቃ ሐይሌ ገብረስላሴ በምረቃው ስነስርዓት ወቅት “ተመራቂ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃን በመተውና የበለጸገ አስተሳሰብን በማጎልበት እራስን በስራ የመለወጥ ስራ ላይ ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል” ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia