TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
”በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የተጀመረው መርሃ-ግብር ይጠናከራል”-የአማራ ክልል መንግሥት

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተፈናቀሉ ወገኖችን  መልሶ ለማቋቋም የተጀመረው መርሃ-ግብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል  በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበል አስታወቁ፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደው የአማራ ልማት ማህበር(አልማ) የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌ ቶን የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ የአማራ ተወላጅ ባለሀብቶች  በአይምባና በአርባባ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ መላኩ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የክልሉ መንግሥት በግጭቱ የተፈናቀሉ ወገኖች ከዕለት እርዳታ ጀምሮ በዘላቂነት የሚቋቁመበት መርሃ ግብር ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

”መንግሥት የአካባቢውን ሰላምና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው” ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የተጀመረውን ጥረት በማገዝ በኩልም ቤታቸው ለተቃጠለባቸው አባወራዎች 70ሺህ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ መላኩን ተናግረዋል፡፡

ባለሀብቶቹ ጉበኝቱን የሚያደርጉት ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ በማየት ድጋፋቸው የሚጠናከርበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የባለሀብቶቹ ተወካይ አቶ ተካ አስፋው ”ባየነው ነገር ልባችን ተነክቷል፤ ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው ሴቶችና ህጻናት ጭምር ለተረጂነት መዳረጋቸው አሳስቦናል” ብለዋል፡፡

ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ባለሀብቶች ድጋፋቸውን በማጠናከር ተፈናቃዮችን በማቋቋም የዜግነት ግዴታችን እንወጣለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአርባባ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙት ተፈናቃዮች መካከል አቶ ጋሻው ብርሃኑ እንዳሉት ”ረጅም ርቀት ተጉዛችሁ እኛን በአካል ለማየትና ችግራችንንም ለመካፈል ባለሀብቶች በመምጣታችሁ ከልብ ተደስተናል፡፡”

መንግሥት የጀመረውን ሰላም በማስፈን ወደ ቀያቸው በፍጥነት እንዲመለሱ የክልሉ አመራር ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል፡፡

በአማራና ቅማንት ሕዝቦች መካከል የተፈጠረው ግጭት የዜጎችን ሞት፣ የንብረት ውድመትና የዜጎች መፈናቀል አድርሷል ያሉት ደግሞ በአርባባ መጠለያ የሚገኙት አቶ መላኩ ውብነህ ናቸው፡፡

መንግሥት አቅሙ በፈቀደ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን የመሰከሩት አስተያየት ሰጪው፣ወደ መኖሪያ ቀያቸው በአፋጣኝ እንዲመለሱ ጥረት እንዲጠናከርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ከዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በዞኑ በተቋቋሙ 13 ጊዜያዊ መጠለያዎችና ከዘመድ ጋር ተጠግተው የሚኖሩ ከ58ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡

ባለሀብቶቹ በጎንደር ከተማ በአባይ አክሲዮን ማህበር የተቋቋመውን የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካም ጎብኝተዋል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ከመተሃራ ከተማ ተፈናቅለው በአዋሽ ከተማ ለተጠለሉ ዜጎች እርዳታ ተጠየቀ። በግጭቱ የ7 ሰዎች ህይዎትም አልፏል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሚያስተዳድራቸው ሁለት መቶ ያህል ወረዳዎች እና 20 የዞን አስተዳደሮች በሀላፊነት ያስቀመጣቸውን አመራሮች በአዳዲስ ለመተካትና አንዳንዶቹንም በአዲስ ሀላፊነት ለመሾም እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰምቷል። ዋዜማ ራድዮ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቻለሁ እንዲሁም ከክልሉ አንድ ከፍተኛ ተሿሚ አረጋግጫለሁ ብሎ እንደዘገበው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በሚያስተዳድረው የኦሮምያ ክልል የተሻለ #ብቃትና #ልምድ ያላቸውን አመራሮች ለመመደብ ዝግጅቱን አጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ #አብራሪዎቹን ለማሰልጠን የሚያስችሉ የተሟሉ ሰባት ምስለ በረራዎች ወይም የበረራ ማሰልጠኛዎች አሉት።

•በአሁን ወቅት ብቁና የተሟሉ ኪው 400፣ ቢ737 ኤን ጂ፣ ቢ 737 ማክስ፣ ቢ 767 ፣ ቢ 787 ፣ ቢ 777 እና ኤ 350 የተሰኙ ሰባት ምስለ በረራዎች አሉት።

•በዋሽንግተን ፓስት የወጣው መረጃ በመረጃ ላይ ያልተደገፈና #የተሳሳተ ነው።

•ማነነታቸው ካልታወቁ አካላት ተገኙ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ከበረራ ስለታገደው #ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ትኩረት ለማስቀየር ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን🔝

የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር (ቁንዳላ) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም አቀባበል እየተደረገለ ነው፡፡ በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ አርበኞች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ150 ዓመታት በላይ በብሪታኒያ የቆየውን የንጉሱን ቁንዳላ የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 11/2011 ዓ.ም ነበር በይፋ የተረከበው፡፡ የኢፌዴሪ መንግስት በባህል እና ቱሪዝም ሚንስትር በኩል በልዩ ልዩ መንገዶች ከሀገር የወጡ ቅርሶችን የማስመለስ ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ። ባንኩ ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በገኝው የተፈናቃዮች መረጃ መሰረት ከንዘቡን ለክልሎች እንደሚከተለው ማከፋፈሉን አስታውቋል፦

•ለሶማሌ ክልል 35 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር፣

•ለኦሮሚያ ክልል 33 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር፣

•ለደቡብ ክልል 18 ሚሊየን ብር፣

•ለአማራ ክልል 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር፣

•ለትግራይ ክልል 3 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር፣

•ለቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣

•ለጋምቤላ ክልል 454 ሺህ ብር፣

•ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 387 ሺህ ብር እና ለሀረሬ ክልል 62 ሺህ ብር ባንኩ ድጋፍ አድርጓል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ያለፈውን አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ የለውጥ ሂደትን የሚቃኘው አዲስ ወግ መድረክ የሁለተኛ ቀን ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። አዲስ ወግ የመቻቻልና የመከባበር ውይይትና የንግግር ባሕልና የሚያስተዋውቅ መድረክ ነው። መጋቢት 14 ቀን 2011 ጠዋት እየተደረጉ ባለው ውይይት አቶ ደሳለኝ ራሕማቶ፣ ዶ/ር ሰዒድ ኑሩ፣ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉና ወ/ሮ ብርሃኔ አሰፋ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት፤ የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ሥራ ፈጠራና ማኅበራዊ አካታችነት ዙሪያ በግብርና ምርታማነት፣ የጥቅል ኢኮኖሚው ሚዛን መዛባትና የዕዳ ጫና ላይ በስፋት እየተወያዩ ነው።

#PMOEthiopia #አዲስወግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia