TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የፀረ_ጥላቻ_ንግግር" ዘመቻ🔝

በሁሉም የሀገሪቱ #ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በበራሪ ወረቀቶች፣ በባነር፣ በፖስተር እንዲሁም በድምፅ ቅስቀሳ #መልዕክቶቻችንን እንደርሳለን!

ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ!

#ቲክቫህኢትዮጵያ---ተቀላቀሉን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🚫STOP HATE SPEECH🚫

#TikvahEthiopia #Facebook #Telegram #Twitter ሀገራችንን እናድን! የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን ወደአስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እየከተታት ይገኛል። ሁላችም ከጥላቻ ንግግሮች ራሳችንን በማራቅ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

#ከጥላቻ_ንግግሮች_እንቆጠብ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከምሥራቅ ሐረርጌ ከባቢሌ ወረዳ ተፈናቅለዉ 8 ወር ያሕል በተለያዩ አካባቢዎች ጊዚያዊ መጠለያ ዉስጥ ሠፍረዉ የነበሩ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ወደየቀየዉ #መመለሳቸዉን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባንድ ዙር 150 ሺህ በላይ ወጣቶችን የብድር ተጠቃሚ የሚያደርግ ዕቅድ ነድፌያለሁ ማለቱን ሸገር ዘግቧል፡፡ ተቋሙ ከ18-34 ዕድሜ ላሉ ሥራ ወጣቶች ተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ መድቧል፡፡ የመደበኛው ብድር ወለድ 10 በመቶ ሲሆን የተዘዋዋሪ ብድሩ ግን 8 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ዋስትናውም ርስበርሳቸው ሲቧደኑ የሚሰጥ ቀናል ዋስትና ነው፡፡ ተቋሙ በ3 ዐመት የሚከፈል እስከ 1 ሚሊዮን ብር ብድር ይሰጣቸዋል፡፡ የከተማዋ አስተዳደር በቅርቡ ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ የመደበውን 2 ቢሊዮን ብር ተቋሙ ያስተዳድራል፡፡

Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና የጠየቁትን የስታድየም #ማስፋፍያ ጥያቄ ተቀብሎ አፀደቀ፡፡ በዚህም መሠረት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የ10,000 ካሬ እና ለኢትዮ ቡና የ8772.7 ካሬ የማስፋፍያ ቦታ የስታዲየም ግንባታ በሚፈፅሙበት ቦታ ዙርያ እንዲሰጥ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት(በረከት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የባሕር ዳር ዙሪያ ፍርድ ቤት ታደሠ ካሳ መዝገብ 9 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መስርቷል፡፡ ክሱ በጥረት ኮርፖሬት የሃብብት ብክነት ማድረስ ነው፡፡ ሁለቱ ተከሰሾች ፍኖተ ሰላም ተክሌና እጸገነት ጌታቸው የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ በሀገር ውስጥ ባለመገኘታቸው ዛሬ ችሎት አልቀረቡም፡፡ ሌሎቹ ግን ቀርበዋል፡፡ ተከሳሽ ታደሠ ሰነዶች እንዲሰጧቸው የጠየቁ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ በበኩለ ሰጥቻቸዋለሁ፤ ሌሎች የጠየቋውን ሰነዶች ያልሰጠኋቸው ግን በምርመራዬ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳርፍ ነው ሲል ተከራክሯል፡፡ ከ2ኛ ተከሳሽ በስተቀር ዋስትና ቢሰጣቸው አልቃወምም ብሏል፡፡ ችሎቱም 6ኛ ተከሳሽ የ150 ሺህ ብር፣ 3ኛ፣ 5ኛና 7ኛ ተከሳሽ ደሞ 100 ሺህ ብር ዋስትና ለመጋቢት 26 እንዲያቀርቡ አዟል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባስኬቶ ነው! ~ ድረሱልን!
(ከጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን)

* 7 ሕጻናት በረሃብ ሞተዋል

* 12 ሰዎች በእርስ በእርስ ግጭት ሞተዋል

* 37, 800 ዜጎች ተፈናቅለዋል

አሁን ከአዲስ አበባ ወደ ባስኬቶ ደወልኩ።

[ ከአቶ ሳሙኤል ደሳለኝ የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳር ጋር አወጋን ]

ከመሎ ወረዳ 11 ቀበሊያት ወደ ባስኬቶ ልዩ ወረዳ የተፈናቀሉ 37 ሺህ 800 ወገኖች አገር እና ሕዝብ ድረሱልን የሚል ድምፅ እያሰሙ መሆናቸውን አስረድተዋል።

አያይዘውም ተፈናቃዮቹ በስድስት መጠለያዎች እንደተሰባሰቡ ገልፀዋል። መፈናቀል የጀመሩት በጥቅምት ወር እንደነበረ ነግረውኛል።

በስድስት መጠለያዎቹ

* ውሃ የለም!

* ምግብ የለም!

* እርጉዝ እናቶች ጫካ እየወለዱ ናቸው

* ሕጻናት በምግብና በመጠጥ እጦት ሕይወታቸው አልፏል።

* ተፈናቃዮች ለተላላፊ በሽታ ተጋልጠዋል።

በባስኬቶ ልዩ ወረዳ የተፈጠረው ሰብአዊና ማኅበራዊ ቀውስ ለክልሉ መንግሥት አቤቱታ በተደጋጋሚ ማቅረባቸውን አቶ ሳሙኤል ደሳለኝ የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ገልፀውልኛል።

***
እናንት ያገሬ ልጆች ...

ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ አገር እና ሕዝብ የማዳን ሥራ እንረባረብ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የልኡል አለማየሁ አፅም ወደ እናት ሀገሩ እንዲመለስ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቀረበች። በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሣው የተመራ ልዑክ ለንደን በሚገኘው የዊንዘን ቤተመንግስት ጉብኝት አድርገጓል።

የልኡካን ቡድኑ የልኡል አለማየሁ ቴዎድሮስን መካነ መቃብር እንዲሁም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አፄ ሃይለስላሴ ይጸልዩበት የነበረውን ወንበር ጎብኝተዋል። ሚኒስትሯ በልኡል አለማየሁ መቃብር ላይም አበባ አስቀምጠዋል።

ከትውልድ ቦታው ተለይቶ ህይወቱ ያለፈው ልኡል አለማየሁ አፅም በትውልድ ሀገሩ እንዲያርፍ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ስለሆነ በክብር ወደ አገሩ እንዲመለስ ሚኒስትሯ ጠይቀዋል።

በእለቱ ልኡካን ቡድኑን በመቀበል ቦታውን ያስጎበኙት የእንግሊዝ መንስግት ተወካይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት ውጤቱን እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡

ሂደቱን በተመለከተ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመከታተል እልባት እንዲያገኝ አስፈላጊውን ጥረት እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ምንጭ:- የውጭጉዳይ ሚንስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech #ኢትዮጵያን_እናድን!

በማህበራዊ ሚዲያ በየቀኑ የሚታየው #የጥላቻ_ንግግር ሀገራችንን ወደለየለት ቀውስ ውስጥ እና ወደማንወጣው #አስከፊ ችግር ውስጥ ይከታታልና ሁላችንም የጥላቻ ንግግሮችን በመቃወም፤ ተሳዳቢዎችን ከተቻለ ለማረም ካልሆነም #Block በማድረግ ይህች ሀገራ እየሄደችበት ካለው የቁልቁለት ጉዞ በፍጥነት ልናስቆማት ይገባል።

#የፀረ_ጥላቻ_ህጉ_ይፍጠንልን!!
#የፌደራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምርጫ ቦርድ አዴፓ እና ኦዴፓ የሚሉ ስሞችን አላውቅም አለ፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እና ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)’ን በአዲሱ ስምቸው እንደማያውቃቸው አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳን ድርጅቶቹ የስም ለውጥ ማድረጋቸውን ለህዝቡ ይፋ ቢያደርጉም አዲሱ ስማቸው እንዲጸድቅላቸው እስካሁን ለምርጫ በርድ ምንም አይነት ማመልከቻ አለማስገባታቸው ነው የተነገረው፡፡ በዚህም አዴፓ እና ኦዴፓ የሚሉት ስሞች እስካሁን የቦርዱ የፓርቲ ስም ዝርዝሮች ውስጥ አለመካተታቸውን ነው የተገለጸው፡፡

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጥረት ኮርፖሬት በ2018 የአውሮፓዊያኑ በጀት ዓመት 458 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ኮርፖሬቱ በበጀት ዓመቱ 709 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም የእቅዱን 26 በመቶ ብቻ ነው ማሳካት የቻለው። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጥረት ኮርፖሬት ወደ ክልሉ የህዝብ ሀብትነት እንዲሸጋገር በቅርቡ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia