TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ያለፈውን አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ የለውጥ ሂደትን የሚቃኘው አዲስ ወግ መድረክ የሁለተኛ ቀን ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። አዲስ ወግ የመቻቻልና የመከባበር ውይይትና የንግግር ባሕልና የሚያስተዋውቅ መድረክ ነው። መጋቢት 14 ቀን 2011 ጠዋት እየተደረጉ ባለው ውይይት አቶ ደሳለኝ ራሕማቶ፣ ዶ/ር ሰዒድ ኑሩ፣ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉና ወ/ሮ ብርሃኔ አሰፋ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት፤ የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ሥራ ፈጠራና ማኅበራዊ አካታችነት ዙሪያ በግብርና ምርታማነት፣ የጥቅል ኢኮኖሚው ሚዛን መዛባትና የዕዳ ጫና ላይ በስፋት እየተወያዩ ነው።

#PMOEthiopia #አዲስወግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ ወግ ውይይት መዝጊያ ላይ በመገኘት መድረኩ ሐሳባችንን ከአደባባይ ወደ አዳራሽ ለመሰብሰብ: ጉልበታችንን ከድንጋይና ዱላ ወደ ሐሳብ በማምጣት የተለያዩ ሸክሞቻችንን ጥለን ኢትዮጵያን በትብብር ወደፊት ለመውሰድ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚከተሉትን ዋና ዋና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስብራቶች አንሥተዋል፦

1. ከግልና ከራስ ቡድን ጥቅም በዘለለ በአንድነት ስሜት አለመንቀሳቀስ፤

2. በምንጠይቀው ልክ በተሰማራንበት መስክ አመርቂ ውጤት አለማስመዝገብ፤

3. ዋልታ ረገጥነት፤

4. ያለፈውን ያሁኑንና የወደፊቱን አስማምቶ አለመጓዝ፤

5. የተሠማራንበትን ሞያ ገሸሽ አድርጎ በፖለቲካ አቀንቃኝነት ብቻ መጠመድ፤

6. እስከ አሁን የተገኙ ድሎችን ማሳነስ፤ የሚዛን መዛነፍ፤

7. መገናኛ ብዙኃን ታሪክ የመጻፍ ሂደት ውስጥ መሆናቸውን ቸል በማለት ጠብ አጫሪና የተዛባ ዘገባ ማሠራጨት፤

8. የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ሥነ ምግባር አለመኖር ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያጠቃልሉም መንግሥታቸው ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ለማካሄድ አመቺ ከባቢን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

#PMOEthiopia #አዲስወግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia