TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት የሟቾች ቁጥር 5 ደረሰ፤ አንድ የፖሊስ አባልም የደረሰበት አልታወቀም፡፡ ትናንት በግምት ከቀኑ 7-8፡00 ባለው ጊዜ በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት ግጭት መቀስቀሱና የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቀደም ብሎ ተዘግቦ ነበር፡፡ ዘግይቶ በወጣ መረጃ ደግሞ በግጭቱ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል፤ የሟቾች አስከሬንም ለቤተሰቦቻቸው ተሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የፖሊስ አባል እስካሁን #አልተገኘም፡፡ የተንቀሳቃሽ ስልኩ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ መገኘቱንና የፖሊስ አባሉ ግን እስካሁን ያለበት ሁኔታና ቦታ አለመታወቁ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር #ውብሸት_መኮንን ተገልጿል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንነው ረሳናቸው
(ጌዲኦ-ኢትዮጵያ)

በቡድን ተከፋፍለን፤ ህይወታችንን በማይቀይሩ አጀንዳዎች ተጠምደን ስንቱን ስንባባል የምንውል ሰዎች ምነው ስለነዚህ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን ለመናገር አፋችን ተለጎመ?

ሰው ነኝ የምንል ሁሉ፤ኢትዮጵያዊ ነኝ የምንል ሁሉ ምንነው ታዲያ እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችንን ዞር ብለን ማየት አቃተን?

በማዕበራዊ ድረገፅ በማይረቡ እና ህይወታችንን በማይቀይሩ ወሬዎች ላይ አስተያየት ስንሰጥ የምንውል ሰዎች ምነው እነዚህን ምስኪን ወገኖቻችን ረሳናቸው?

ምነው ከመንጋው ተነጥለን፤ እንደሰው አዝነን ስለነዚህ ሰዎች ችግር እና መከራ ብንነጋገር፤ ሰውነትን መርሳትስ ተገቢ ነው? ነገስ የኛ መውደቂያ የት እንደሆነ እናውቅ ይሆን?

ወገኖቼ ተኝተናል እንንቃ!
አካሄዳችን ሊታረም ይገባል!
አመለካከታችን ሊታረም ይገባል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዲኦ

በጌዲኦ ዞን #ገደብ እና #ጎቲቲ ወረዳዎች በርካታ ተፈናቃዮች ያለ ምግብ እና ህክምና #እርዳታ በስቃይ አሉ። በህክምና እጦት 15 ህጻናት #የአይናቸውን_ብርሃን አተዋል። አብዛኞቹ በመጠለያ እና በምግብ እጦት #በመሰቃየት ላይ ናቸዉ። የተራድኦ ድርጅቶች እርዳታ ማቅረብ #አልቻልንም ብለዋል። ወቅቱ የዝናብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቸግሩን የከፋ አድርጎታል።

Via Bisrat Melese
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ

#የአሜሪካ_መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቹ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ስለተጠራ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።
-----------------------------------------------
የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል የሚለውን መረጃ ከየት እንደተገኘ ባይታወቅም የከተማ አስተዳደሩ ወይም የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እውቅና የሰጠው ሰልፍ ግን የለም።
-----------------------------------------------
ነገር ግን "ለአዲስ አበባ ምን ይደረግ?" በሚል በባልደራስ አዳራሽ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ህዝባዊ ውይይት እንደሚደረግ ለማውቅ ችያለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአርክቴክቸር ትምህርት መስክ በመደበኛ መርሃ ግብር በባችለር ድግሪ ያስተማራቸውን 43 ተማሪዎችን ለ3ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

33-ወ
10-ሴ

Via WSU
@tsegbwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 28 ክላሽንኮቭ፣ 459 ሽጉጦች እና በመቶ ሺህዎች የሚቁጠሩ የአሜሪካ ዶላር #በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል #ከሁለት_ክልሎች በረቀቀ መንገድ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መሰረት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ወደ መሃል ከተማ የገባ 25 ታጣፊ እና 3 ባለ ሰደፍ በድምሩ 28 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪው ሹፌር እና ረዳትም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በተመሳሳይ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቴል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ በኮሮላ የቤት ተሽከርካሪ ውስጥ 459 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና 2 የዝሆን ጥረስ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልፀዋል።

እንዲሁም የካቲት 29 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቤቴል ሆስፒታል እየተባለ በሚጠራው አካባቢም ከ700 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የተጠራ ሰልፍ የለም‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ነገ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በነገው እለት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጭው መረጃ ትክክል አለመሆኑን አስታውቀዋል።

ለነገ ህጋዊ መስመርን ተከትሎ እና ባለቤትነቱን ወስዶ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ያቀረበ አካል #እንደሌለም አስታውቅዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አክለውም ብህረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጠሩ ህጋዊ ባለቤትነት ከሌላቸው ሰልፎች ሊቆጠብ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ምክንያቱም ይህንን አጋጣሚ እንደ ምቹ ሁኔታ የሚጠቀሙ ኃይሎች በኅብረተሰቡ ላይ #የሽብር ተግባራት ለመፈጸም የሚያስችል እንቅስቃሴ ስለሚኖር ከወዲሁ ይህንን ተገንዝቦ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

#በመዲናዋ ያለ ፈቃድ ሠልፍ የሚያካሄዱ አካላትም ኃላፊነት እንዳለባቸው በመረዳት ግን ህጋዊ አሰራሩን መከተል አለባቸው ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ህብህረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጠሩ ህጋዊ ባለቤትነት ከሌላቸው ሰልፎች #ሊቆጠብ ይገባል።" ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ዓመት ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ #ገድለዋል በተባሉ 3 ወታደሮች ላይ #ሞት ሲፈርድ በአንድ ወታደር ላይ ደግሞ የ10 ዓመት እሥራት በየነ። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ባለፈው ዓመት የተፈጸመው የዚህ ግድያ ዓላማ #ዘረፋ ነበር። ትናንት ያስቻለው ፍርድቤቱ ከወታደሮቹ ጋር ተባብረዋል ከተባሉ ሁለት ሲብሎች አንዱ እድሜ ይፍታህ ሌላኛው ደግሞ የ8 ዓመት እሥራት ተፈርዶበታል። አራቱም ወታደሮች ማዕረጋቸው ተገፎ ከጦር ኃይሉም መሰናበታቸው ተዘግቧል።

Via ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፌስቡክ

ለ1 ሳምንት #ከፌስቡክ እንድንርቅ የሚለው የመጀመሪያው ቅስቀሳ ለብዙዎች ጥቅም የሌለው መስሎ ታይቷቸዋል። ዋነኛ አላማ አድርጎት የነበረው በ7 ቀን ውስጥ የጥላቻ፣ ፣የጦርነት ቅስቀሳዎችን፣ የሽብር፣ የስድብ ፅሁፎችን ባለማየታችን አእምሮአችን የሚሰማውን ሰላም ለማስገንዘብ ነው። ቀጣዩ ስራችን እንደኛ ሰዎችን ሰላም እንዲሰማቸው አጠቃላይ ፌስቡክን በሰላም፣ አንድነት እና የፍቅር መልዕክቶች ማጥለቅለቅ ይሆናል። ሁላችንም ሀላፊነት አለብን ምክንያቱም ያለችን አንዲት ሀገር ብቻ ስለሆነች! በጥላቻ ሀገራችን ከመጥፋቷ በፊት እኛ የአቅማችንን እንሞክር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራፍ ሁለት!

ለ2 ሳምንት የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #NoHateSpeechMovement /ETHIOPIA/ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮችን የምንዋጋበት፤ የተለያዩ መልዕክቶችን ፖስት በማድረግ ጥላቻን የምናሸንፍበት ሳምንታት ይሆናሉ! #ቲክቫህኢትዮጵያ

ዘመቻው የሚካሄደው፦
#Facebook
#Telegram
#Twitter ላይ ይሆናል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር የበጎ እሴቶች መናጃ፣ የወንጀሎች #መጥሪያ እንዲሁም አድልኦና መገለል አምጪ እኩይ ተግባር ነው!

#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia