TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ጉባኤው በሠላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን እና የፀጥታ ሃይሎችን ያሳተፈ ኮማንድ ፓስት መቋቋሙን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው እየሰጠ ያለው ድጋፍ አበረታች መሆኑን ጠቁመው፥ ይህ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የሀገሪቱን ብሎም የከተማዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት አኳያም ጉባኤው የራሱ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ፥ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጐን በመቆም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዩች ሲያጋጥሙት በስልክ ቁጥር፤ 011-126-43-77፣ 011-126-43-59፣ 011-827-41-51 ፣ 011-111-01-11 እና 991 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችልም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም በሚከተሉት መንገዶች ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፤

ከአየር መንገድ – ቦሌ ቀለበት መንገድ – ፍሬንድ ሺፕ – ጃፓን ኤምባሲ – ወሎ ሰፈር – ኦምሎፒያ – ፍላሚንጎ – መስቀል አደባባይ – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – 1ኛ/ ከፓርላማ መብራት – ሜክስኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ።

ከብሄራዊ ቲያትር – በፍልውሃ – በብሄራዊ ቤተ መንግስት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤

ከፓርላማ መብራት – ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፤

ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከጦር ሃይሎች – በሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች፤
በኮካኮላ ድልድይ – በአብነት ተክለኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ፤

ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፥ ሳር ቤት በቴሌ አድርገው ቀለበት መንገድ በሳር ቤት ወደ ቄራ ጎተራ፤

የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፥ በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ ሲግናል – ቀለበት መንገድ ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ  ቀለበት መንገድ – መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ – ቀለበት መንገድ መገናኛ አድዋ ጎዳና አዋሬ አራት ኪሎ – ከፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መጠቀም ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪም እንግዶች በአጀብ በሚያልፉበት ወቅት አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለፖሊስ አባላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 28 ክላሽንኮቭ፣ 459 ሽጉጦች እና በመቶ ሺህዎች የሚቁጠሩ የአሜሪካ ዶላር #በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል #ከሁለት_ክልሎች በረቀቀ መንገድ ተደብቀው ወደ አዲስ አበባ የገቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚህም መሰረት የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ 18 ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ወደ መሃል ከተማ የገባ 25 ታጣፊ እና 3 ባለ ሰደፍ በድምሩ 28 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪው ሹፌር እና ረዳትም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በተመሳሳይ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤቴል ሆስፒታል ጀርባ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ግቢ በኮሮላ የቤት ተሽከርካሪ ውስጥ 459 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና 2 የዝሆን ጥረስ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልፀዋል።

እንዲሁም የካቲት 29 2011 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቤቴል ሆስፒታል እየተባለ በሚጠራው አካባቢም ከ700 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ምክትል ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia