በትንሹ የ70 ሰዎች ህይወት አለፈ🔝
#በባንግላዲሽ ዋና ከተማ #ድሃካ በተከሰተ ቃጠሎ በትንሹ 70 ሰዎች ሞቱ። በዋና ከተማዋ ጥንታዊ የመኖሪያ ሰፈር የተከሰተው ቃጠሎ የተነሳው በአንድ ህንጻ ውስጥ የነበረ ተቀጣጣይ የኬሚካል መጋዘን ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል።
የእሳት ቃጠሎው በፍጥነት ወደ መኖሪያ መንደሮች በመስፋፋት ከፍተኛ አደጋ አድረሷል ነው የተባለው።
ከ50 ያላነሱ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የተወሰኑት አስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው ተብሏል።
በአካባቢው በሰርግ ላይ የታደሙ ሰዎችም የአደጋው ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው።
አደጋው የደረሰው ከ300 ዓመታት በላይ እድሜ ባለቤት በሆነው የቻውክባዛር መንደር ነው።
ይህ ጥንታዊ ስፍራ በጣም ጠባብ መንገዶች ያሉት ሲሆን በመኖሪያ ህንጻዎች መካከል ያለው ክፍተትም እጅግ ጠባብ መሆኑ አደጋውን የከፋ እንዳደረገው ተነግሯል።
ቃጠሎውን ለማጥፋት 200 የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ ሲሆን የውሃ እጥረትና የመንገዱ ጠባብ መሆን እንዳስቸገራቸው ተጠቆሟል። እሳቱ የተከሰተበት ምክንያት #እየተጣራ መሆኑም ታውቋል።
ምንጭ፦ቢቢሲ፣ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስነ- ህዝብ ፈንድ ለ4ኛው ዙር አገር አቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤታማነት #ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በነገራችን ላይ...
የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ቆጠራውን አስመልክቶ ለክልል፣ ለከተማ አስተደደር፣ ለዞንና ለወረዳ የቆጠራ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ያዘጋጀውን ስልጠና ትላንት መስጠት ጀምሯል።
ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ...
የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ቆጠራውን አስመልክቶ ለክልል፣ ለከተማ አስተደደር፣ ለዞንና ለወረዳ የቆጠራ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ያዘጋጀውን ስልጠና ትላንት መስጠት ጀምሯል።
ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝
በሀዋሳ እየተካሄደ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ~ያለምንም እንከን #በሰላም እየተከናወነ ይገኛል። ሰልፈኛው በአሁን ሰዓት በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም በመሰብሰብ ላይ ይገኛል።

ጅግጅጋ🔝
የስምንተኛው #የኢትዮጵያ_ከተሞች_ፎረም የማጠቃለያ ፕሮግራም ጅግጅጋ በሚገኘው የሱማሌ ክልል ቤተመንግስት አዳራሽ ተጀምሯል። በማጠቃለያው ልዩ ልዩ #ሽልማቶች በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጡ ሲሆን #የዘጠነኛው_ፎረም አዘጋጅ ከተማም የሚታወቅ ይሆናል።

ሸዋሮቢት~ሰላም ናት!!
የሸዋሮቢት ከተማ #ፍፁም_ሰላማዊ በሆነው መደበኛ እንቅስቃሴዋ ውስጥ ናት። የከተማይቱ ነዋሪዎች የዘውትር መደበኛ እንቅስቃሴያቸውን እያደረጉ ነው።
ሰናይ ቀን!

ጉዞ ሉሲ~ለሰላምና ለፍቅር!
‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር መርሀ-ግብር›› ትላንት ምሽት በሚሊኒዬም ተጀምሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ካሰው ‹‹ዘረኝነት፣ መለያዬት፣ ማግለልና ንፉግነት የኛ የኢትዮጵያዊነት ባሕል አይደለም፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የነበረንን መተዛዘን፣ #ፍቅርና #አንድነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለውጥ የሚጀምረው ከራስ ነውና ለለውጥ እዘጋጃለሁ፤ ለለውጥ እንዘጋጅ›› በሚል #የአንድነት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ ከአፋር ክልል ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ሉሲ የአምስት ቀናት ቆይታ እያደረገች ሕዝቡ #በአንድነቱ ዙሪያ እንደሚወያይ የገለጹት ሚኒስትሯ ‹‹ሉሲንና ሌሎች አንድ የሚያደርጉን በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶችን በታላቅ ክብር ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ ፓርላማ አጓጉዘን ወደ አፋር በመሸኘት ይጀመራል›› ነው ያሉት፡፡
ሉሲ የእገሌ የሚባል ሃይማኖት፣ ብሔር፣ አስተሳሰብ ወይም ሌላ #ወካይ_ያልሆነች የሁሉም የሰው ዘር ግንድ መሆኗን የጠቀሱት ሚንስትሯ ‹‹ደግነትና አብሮነት ስላልተለየን በጎ ትሩፋት ሳይሠራ የሚውል #ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ የተራበ ሳያበላ፣ የተጠማ ሳያጠጣ፣ የወደቀ ሳያነሳ፣ የሞተ ሳይቀብር አይውልም፤ ኢትዮጵያዊነትም ይህ ነው›› ብለዋል፡፡ እንኳን እርስ በእርስ ከሌላውም ዓለም ጋርም ኢትዮጵያዊ በሉሲ የተዛመደ መሆኑንና #ዘረኝነት የኢትዮጵያዊነት ባሕል አለመሆኑን ነው ዶክተር ሂሩት ያስገነዘቡት፡፡
በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ አንጋፋና ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል።
Via AMMA

የአንድነት ጥሪ ለመላው ኢትዮጵያዊያን!
‹‹ዘረኝነት፣ መለያየት፣ ማግለልና ንፉግነት የኛ የኢትዮጵያዊነት ባሕል አይደለም፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የነበረንን #መተዛዘን፣ #ፍቅርና #አንድነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለውጥ የሚጀምረው ከራስ ነውና ለለውጥ እዘጋጃለሁ፤ ለለውጥ እንዘጋጅ›› ዶክትር #ሂሩት_ካሳው