TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : ዛሬ ምሽትም 4:17 ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል። በተለይም ደግሞ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል። ጠንከር ያለ እንደነበረም ጠቁመዋል። ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ጣፎ ... ሌሎችም አካባቢዎች…
#Update
ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ አፋር፣ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።
" ዛሬ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። መጠናቸው ግን ዝቅ ያለ ነው። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ግን በጣም ያስፈራ ነበር። ሁኔታ አለመቆሙ እጅግ አስደንግጦናል ፤ የከፋ ነገር እንዳይፈጠር እያልን በሰቀቀን ውስጥ ነን " ብለዋል።
ከደቂቃዎች በፊት የነበረው መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ከተማ ብዙ ቦታዎች በደንብ ተሰምቷል።
እቃ አንቀሳቅሷል፣ አልጋ ላይ ያሉ ሰዎች ሲንቀሳቁም እንደነበር ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ስሜቱን ያልሰሙ ቦታዎችም ንዝረቱ ተሰምቷል።
" ተሰምቶን አያቅም እኮ " የሚሉ ሰዎችም ዛሬ ምሽት ስሜቱን እያተውታል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ የላኩ ቤተሰቦች " ከወትሮ የተለየ ነበር ድንጋጤን ፈጥሮብናል " ሲሉ ገልጸዋል።
አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የሚኖር ነዋሪ " የዛሬው ይለይ ነበር። በተኛሁበት ሲነቃነቅ ተሰምቶኛል ደንግጬ ወደ መሬት ወረድኩ " ብሏል።
ሌላ መልዕክቱን የላከ የቤተሰባችን አባል ፥ ነዋሪነቱ ጃክሮስ እንደሆነ ቪላ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ስለ ንዝረቱን ከዚህ ቀደም በሚዲያ ከሚሰሙት ውጭ በተግሻር ተሰምቷቸው እንደማያውቅ ዛሬ ግን እንደተሰማቸው ገልጿል።
" በጣም ነው ፍራቻ የለቀቀብን " ሲል ሁኔታውን ገልጿል።
አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " ንዝረቱን በደንብ እንደሰሙ ቋቋ የሚል ድምጽም እንደተሰማቸው " ጠቁመዋል።
ሌላኛዋ የመልዕክት ላኪ ቤተሰባችን " የእቃ እንቅስቃሴ እንደነበር ፤ እሷም በተቀመጠችበት መንቀሳቀሷን ፤ በፊት ከነበረው ይለይ እንደነበር " ገልጻለች።
ቱሉዲምቱ ፣ አራብሳ ፣ ጃክሮስ ፣ ጋርመንት ፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ አያት ፣ አያት 49 ፣ ጎሮ፣ አባዶ፣ ካራ፣ ጣፎ፣ ... ከሌሎችም ብዙ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላቱን መልዕክት ተቀብሏል።
ውድ የአፋር እና የሌሎችም የክልል ከተሞች ቤተሰቦቻችን " ሁኔታው የተለመደ ነው " ብላችሁ እንዳትዘናጉ አደራ እያልን በዚህ ሊንክ👇 https://t.iss.one/tikvahethiopia/93268 ያለውን የጥንቃቄ መንገዶች በማስተወሻችሁ ላይ አኑሩት።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

#Update ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ አፋር፣ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል። " ዛሬ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። መጠናቸው ግን ዝቅ ያለ ነው። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ግን በጣም ያስፈራ ነበር። ሁኔታ አለመቆሙ እጅግ አስደንግጦናል ፤ የከፋ ነገር እንዳይፈጠር እያልን በሰቀቀን ውስጥ ነን " ብለዋል። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው መንቀጥቀጥ…
#Update
4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል።
ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ መጠን ያላቸው በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበው የነበረ ሲሆን ከፍተኛው 4.8 ነበር።
ዛሬም አዋሽ እና አካባቢው ላይ 4.3 እና ከዚያ በላይ የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ነበሩ።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar

January 1,2025
በግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠር (GC) አዲሱ ዓመት 2025 ገብቷል።
በዓለማችን ላይ እጅግ በርካታ ሀገራት አዲሱን ዓመት 2025 ተቀብለዋል።
ከዓለማችን ሀገራት መካከል ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሷ የዘመን አቆጣጠር ያላት ሲሆን የግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠርን (GC) እንደ ዘመን መለወጫ አትጠቀምም።
የ13 ወራት ፀጋ ባለቤቷ ኢትዮጵያችን🇪🇹ከሌሎች ሀገራት የዘመን አቆጣጠሯ መለየቱ ብቻ ሳይሆን የራሷ የሆኑ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ ፊደል ፣ ጥበብ ያለባት ሀገር ናት።

🚨#እንድታውቁት " ከሌሊቱ 6:00 እስከ 6:15 ሰዓት ላይ ርችት ይተኮሳል " - ፖሊስ የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። ዋና መምሪያው ለአዲስ አበባ ፖሊስ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን…
#እንድታውቁት
አዲስ አበባ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት ሲሰማ የነበረው ከፍተኛ የሆነ ድምጽ የፈረንጆቹን 2025 አዲስ ዓመት አስመልክቶ ሲተኮስ የነበረ ርችት ነው።
የፈረንጆችን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ከለሊት 6:00 እስከ 6:15 ድረስ ርችት እንደሚተኮስ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖሽ የእንጨት ስራዎች / Posh wood works
ከመጀመሪያዎቹ መሀል ይሁኑ ! ውጭ ሀገር ያዩት እርሶ ቤትም አይቀርም በሀገራችን የመጀመሪያው የሆኑ የአልሙኒየም ፍሬም መስታዎት በሮችን የተላበሱ የእንጨት ስራ ውጤቶችን ለእናንተ ለደንበኞቻችን ፤ይዘን መተናል
" ልዩ ውበት ይገባዎታል! "
ፖሽ የእንጨት ስራዎች / Posh wood works
Closet / Cupboard
Kitchen cabinet
TV Unit
Dressing
📍አድራሻ፦ ጀሞ 1 የተባበሩት ማደያ ውሰጥ
- 22 ከጎላጎል አጠገብ ኖህ ሪልስቴት 3ኛ ፎቅ
📲 0929414154
📲 0983915600
📲 0954777788 /99
ቴሌ ግራማችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/webnewood

#SafaricomEthiopia
🔥⚽️ ትኩስ የስፖርት ዜና በስልካችን! 💬
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ!
በElite ስፖርት በሽ ዜናዎች⚡️
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether

" በአምቡላንሶቹ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ዘግናኝ ነው " - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በሠራተኞቹ እና በአምቡላንሶቹ ላይ " ዘግናኝ " ሲል የገለጸው ጥቃት መፈጸሙን አመለከተ።
የማኅበሩ አምቡላንሶች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ እና በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ለህይወት አድን ተግባር በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ባልታወቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት የሁለቱም አምቡላንስ አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ጉዳት የተዳረጉ ሲሆን አምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹም ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል።
ማኅበሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሠራተኞቹን ጨምሮ በበጎፈቃደኞቹ እና ተሽከርካሪዎቹ ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶች አማካኝነት ሰብዓዊ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ወገኖች ለማድረስ ፈተና እየሆነበት እንደሆነ አሳውቋል።
ጥቃት የሚፈፅሙ የትኛውም ተፋላሚ ኃይሎች ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶችን የሚፃረርና ከማኅበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን ተረድተው የማኅበሩ ሠራተኞች፣ በጎፈቃደኞችም ሆኑ ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሰብዓዊ ተግባራቸውን ማከናወን እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ማኅበረሰቡም ድርጊቶቹን እንዲያወግ ተማፅኖ አቅርቧል። እናቀርባለን፡፡
ማኅበሩ " የወገኖቻቸውን ህይወት ለመታደግ ሲንቀሳቀሱ የጥቃት ሰለባ በመሆን መተኪያ የሌላት ውድ ህይወታቸውን ላጡ ሠራተኞች እና በጎፈቃደኞች ቤተሰቦች መፅናናትን እንዲሁም ለተጎዱት በቶሎ ማገገምን እንመኛለን " ብሏል።

Photo
#Mekelle
መቐለ ያለ ከንቲባ አንድ ወር ሆናዋታል።
በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከተማዋ እንዲስተዳድሩ ህዳር 22/2017 ዓ.ም የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ፅህፈት ቤታቸው አልገቡም።
የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፓሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።
ከህዳር 23 አስከ ዛሬ እሮብ ታህሳስ 23/ 2017 ዓ.ም አንድ ወር ሙሉ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነቸው መቐለ የሚያስተዳድራት ከንቲባ የለም ፤ ተገልጋዮች ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆን በምሬት ይገልፃሉ።
ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አከባቢዋ የተወጣጡ ወጣቶች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ከንቲባ ስራ እንዲጀምሩ ያለመ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ወጣት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ህጋዊው ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤታቸው ሳይገቡ ከቦታው ንቅንቅ እንደማይሉ ፤ ከተማዋ የግርግር እና ረብሻ ምንጭ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ ድምፃቸው በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

አዲስ አበባ ውስጥ አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መገኘት አስገዳጅ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ከዛሬ ታህሳስ 23 , 2017 ዓ.ም (Jan 1st 2025) ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ሆኗል።
በሌላ ተያያዥ መረጃ ...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ " ፋይዳን ለባንክ አገልግሎት አስገዳጅነት " ትዕዛዝ ወደ ትግበራ መግባት ተከትሎ የተለያዩ ባንኮች የማርኬቲንግ እና ኮርፖሬት ህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ሀላፊዎች ያሳተፈ በጥምረት ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አሳውቆናል።
ከኃላፊዎች ጋር በነበረ ውይይት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርአያስላሴ ፤ " የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ባንኮች በፋይዳ መታወቂያ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን ልክ እንደ አንድ የባንክ አገልግሎት አጽንዖት ተሰጥቶት እንዲሰሩ " ሲሉ አሳስበዋል።
#ፋይዳለኢትዮጵያ #መታወቅ #አካታች #DigitalID

ADDIS ABABA NO 3 Total Tax Payers.pdf
6.4 MB
#እንድታውቁት
" 12 ሺ ለሚሆኑ ግብር ከፋዮች የታክስ መክፈያ ማዕከል ቅያሪ ተደርጓል " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ ለማድረግ እና ካለው የተገልጋይ ብዛት አኳያ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስቸግር በመሆኑ ለ12 ሺህ የመካከለኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ክፍያ ማዕከል (Tax Center) ቦታ ቅያሪ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ " የቦታ ቅያሪው የተደረገው በቦታው የበርካታ ግብር ከፋዮች ጫና በመኖሩ የተወሰነውን በመቀነስ ግብር ከፋዩ በአቅራቢያው ማግኘት የሚችልበትን እድል ለመፍጠር ነው " ብለዋል።
ቅያሪው የተደረገው ከስታዲየም አካባቢ የሃ ህንፃ ወደ ጉርድ ሾላ ከሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው ሜሪዲያን ኮንቬሽን ሴንተር ነው።
በአዲስ አበባ 11 የአንስተኛ ፣ 5 የመካከለኛ እና 1 የከፍተኛ ግብር ከፋይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚገኙ ሲሆኑ የአሁኑ 17ኛው ቅርንጫፍ ነው ተብሏል።
የቦታ ቅያሪው የሚመለከታቸው ተገልጋዮች ስማቸውን ከላይ በተያያዘው ፋይል በመመልከት ከጥር 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" ወቅታዊ ጥያቄያችሁን ሰምተናል ፤ ከሚመለከተው አካል ምላሽ ይሰጥበታል " - የትግራይ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ አመራሮች
ከመቐለ እና አከባቢዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተሰባሰቡ በሺህ የሚሆኑ ወጣቶች የሚበዙባቸው ሰልፈኞች ዛሬ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ወደ ከተማዋ የከንቲባ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሰባስበው ነበር።
የአስተዳደሩ ዋና በሮችና ዙሪያው የሚጠብቁ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፓሊሶች በአከባቢው የነበሩ ሲሆን በባነር የተፃፉ መፈክሮች በመያዝና ድምፅ በማሰማት ወደ አስተዳደሩ ህንፃ በተለያዩ አቅጣጫ የተመሙ ሰልፈኞች አንድ ላይ አንዳይሰባሰቡ አድርገዋቸዋል።
በአንዱ አቅጣጫ የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ከከንቲባው ህንፃ ዋና በር በቅርብ ርቀት በመሆን ፦
- ጊዚያዊ አስተዳደሩ አይፈርስም !
- በመንግስት ላይ እምቢታ ያወጁ ሃይሎች ላይ እርምጃ ይወሰድ !
- መንደርተኝነት እና ኋላቀርነት ይወገድ !
- ከፓርቲ መንግስት ይቀድማል !
- መንግስት ለማፍረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይቁም !
- የህዝቦች አንድነት ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ በጥብቅ እንቃወማለን !
- እምባገነንነት ፣ጭቆናና አፈና አንቀበልም !
- መቐለ የልማት እንጂ የአመፅ መነሃሪያ አይደለችም !
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች በድማፃችን ይከበራሉ !
- የአመፅ መሪዎች ወደ ህግ ይቅረቡ !
- እውነተኛ የህዝብ ትግል አይቀለበስም !
- ህዝብ እና እውነት የያዘ ያሸንፋል !
- እናሸንፋለን ! ... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ከፍ ባለ ድምፅ አሰምተዋል።
የሰልፈኞቹ ጥያቄ ያዳመጡ በቦታው የተገኙ የክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች " ወቅታዊ የሰልፈኞቹ ጥያቄ ከሚመለከተው አካል ምላሽ እንደሚሰጠው " በመንገር ሰልፈኞቹ ወደ መጠቡበት አከባቢ በሰላም እንዲመለሱ አድርገዋል።
በሰልፈኞቹ መካከል ይሁን ከፀጥታ አካላት ጋር የተፈጠረ ግርግር እና ግጭት እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ቦታው ደረስ በአካል በመገኘት አረጋግጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፃቸው " የትግራይ ትንሳኤ እውን እንዲሆን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንነሳ " የሚል ይዘት ያለው ፅሁፍ አጋርተዋል።
በተመሳሳይ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እየመከረ ሲሆን ፤ በምክክሩ የዞን እና የክልሉ የፀጥታ አመራሮች ተሳታፊ እንደሆኑ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ይህ መረጃ ተዘጋጅቶ የተላከው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle