TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Earthquake : ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ጨምሮ ቀን ላይ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር የአፋር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ገልጸዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየጨመረ ነው ብለዋል።
አንድ የቤተሰባችን አባል፥ " አላህ መፍትሄውን ይስጠን ፤ ያረጋጋው እንጂ እጅግ በጣም ያስፈራል ፤ የዓለሙ ፈጣሪ አላህ መጨረሻችንን ያሳምረው " ሲል ገልጿል።
መሬት መንቀጥቀጡ እየፈጠረ ያለው ንዝረት በተለያዩ ከተሞችም መሰማቱን ለመረዳት ችለናል።
በፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ የሚገኝ ሲሆን ትላንትና ከፍተኛ የሆነው በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar
@tikvahethiopia

#Earthquake ለሊት 7:13 ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ የጀርመኑ ጂኦ ሳይንስ እና የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመላክታል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተመዘገበው ከአቦምሳ 39 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው። ይህ ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.0 ፣ 4.5 ፣ 4.6 ፣ 4.7 ... የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች ቀን፣ ምሽት እና ለሊቱን…
#Kesem_Dam
🚨 "በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በከሰም ግድብ አከባቢ ያሉ ነዋሪዎች በብዛት እየለቀቁ ነው" - ነዋሪዎች
🔴 " ግድቡ ዲዛይኑ እስከ 7.0 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ ይችላል ተብሎ ይገመታል " - ጽ/ቤቱ
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች የመሬት መሰንጠቆች በመፈጠራቸውና በተፈጠሩ ስጋቶች ምክንያት ነዋሪዎች ካሉበት አከባቢ ወደ ሌላ አከባቢ እየሸሹ መሆኑን ሰምተናል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአፋር ቤተሰብ በትላንትናው ዕለት በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አርብሃራ ቀበሌ እና ዶኾ ቀበሌ በመገኘት በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት እቃቸውን ጭነው ሲጓዙ የነበሩ ነዋሪዎችን አግኝቶ አነጋግሯል።
ኃሳባቸውን የሰጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች የመሬት መንቀጥቀጡ እንዲሁም እሱን ተከትሎ የሚሰማው ድምጽ በተለይ ለልጆቻቸው ፍርኃት እንደፈጠረባቸው አስረድተዋል።
ከትላንት በስቲያ ከአርብሀራ ቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው መልካወረር ከተማ የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍ በማለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች ለሶላት (ዱኣ ለማድረግ) ወደ መስጂድ እንደገቡ ነው የገለጹት።
በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት እቃቸውን በሦስት እግር ተሽከርካሪ ጭነው አከባቢውን ሲለቁ ያገኘናቸው ወጣቶች " ብዙ ሰው ለቋል፤ አረ ሁሉም ለቋል እዚያ ሰፈር ያለ ሁሉም እየለቀቀ ነው " በማለት ወደ አዋሽ አርባ እየተጓዙ መሆኑን ተናግረዋል።
የአስፋልት መሰንጠቅ በተከሰተበት ቦታ ያገኘነው አንድ ነዋሪ እንዳስረዳው በርካታ ሰዎች እየለቀቁ ያሉት በወረዳው ከሚገኘው የከሰም ግድብ አከባቢ ያሉ ነዋሪዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።
" ከ7 ጀምሮ [በትላንትናው ዕለት] ያለውን ሁኔታ ብታየው በሚገርም ሁኔታ እቃ እየተጫነ ነው፤ በጣም ደግሞ በትናንሽ መኪኖች በባጃጅም ሁሉም እንደ አቅሙ እንደ ኑሮ ደረጃው እቃውን ጭኖ እየወጣ ነው። " ሲልም ነው ያስረዳው።
በተለይም " ግድቡ የመሰንጠቅ አደጋ ደርሶበታል " በሚል የፋብሪካው ሰራተኞች ጨምሮ ነዋሪው በሌሊት ጭምር እቃውን እየጫነ፤ ግመሎቹንና እንስሳቱን እየነዳ ከአከባቢው መሸሹን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረዳት ችሏል።
ዛሬ ጠዋትም በከሰም ያሉ ነዋሪዎችን ያነጋገርን ሲሆን ትላንት ሌሊት በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶች ከቤታቸው ወጥተው አስፓልት ላይ ማደራቸውን ነግረውናል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንጋት ላይም በመቀጠሉ በርካቶች ንብረታቸውን ይዘው ወደ አዋሽ አርባ እየሸሹ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ነዋሪዎች በመንግሥት በኩል በቂ የማረጋጋትም ሆነ ድጋፍ የማድረግ ሥራ በአከባቢው እንዳልተሰራነው የገለጹት።
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ለሚገኘው ከሰም ስኳር ፋብሪካ አገልግሎት የሚሰጠው የከሰም ግድብ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ነው።
የግድቡ ባለሞያዎች ነዋሪዎች አከባቢውን ለቀው የሄዱት " ግድቡን ውሃ እየጣሰ ነው " በሚል ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን መግለጻቸውን ከአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደን አብዶ ስለ ግድቡ አሁናዊ ሁኔታ ለቲክቫህ ምን ምላሽ ሰጡ ?
" የግድቡ አካባቢ ላይ ያለውን አሁናዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልን ስለሆነ ምንም አይነት ችግሮች የሉም በአሁን ሰዓት ሰላም ነው።
ከግድቡ 30 እና 40 ኪሜ ላይ ነው መንቀጥቀጡ ከበድ ያለው። ቦታው ላይ ካሉ አስተዳደሮች እስካሁን ድረስ ከግድቡ ጋር የተያያዘ የደረሰን መጥፎ መረጃ የለም።
ግድቡ ዲዛይኑ እስከ 7.0 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ ይችላል ተብሎ ይገመታል እስካሁን እዚህ አልደረሰም ባለሞያዎች እየተከታተሉ ያለውን ስጋት ሪፖርት ያደርጋሉ እኛም ለሚመለከተው አካል እናስተላልፋለን።
በተፋሰስ ውስጥ ያለውን ህብረተሰብ የማንቃት እና ያለውን ሂደቶችን ኮሚቴ ተዋቅሮ መረጃ የሚለዋወጡበት ሂደት ከክልሉ መስኖና ቆላማ ቢሮ እስከ እስከ አደጋ መከላከል ድረስ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ነው " ብለዋል።

#Update ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ አፋር፣ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል። " ዛሬ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። መጠናቸው ግን ዝቅ ያለ ነው። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ግን በጣም ያስፈራ ነበር። ሁኔታ አለመቆሙ እጅግ አስደንግጦናል ፤ የከፋ ነገር እንዳይፈጠር እያልን በሰቀቀን ውስጥ ነን " ብለዋል። ከደቂቃዎች በፊት የነበረው መንቀጥቀጥ…
#Update
4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል።
ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ መጠን ያላቸው በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበው የነበረ ሲሆን ከፍተኛው 4.8 ነበር።
ዛሬም አዋሽ እና አካባቢው ላይ 4.3 እና ከዚያ በላይ የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ነበሩ።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar
@tikvahethiopia
4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል።
ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ መጠን ያላቸው በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበው የነበረ ሲሆን ከፍተኛው 4.8 ነበር።
ዛሬም አዋሽ እና አካባቢው ላይ 4.3 እና ከዚያ በላይ የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ነበሩ።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 4:18 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ተመዝግቧል። የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ልክ 4:18 ላይ ከአዋሽ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አመላክቷል። ይህ 4.8 ሆኖ የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ከተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ ነው። ትላንትና ሰኞ ከጥዋት አንስቶ የተለያየ…
#Earthquake : እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬም ቀጥሏል።
ዛሬ ረቡዕ ከጥዋት አንስቶ እስከ ምሽት በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ከ4.5 እስከ 4.9 ድረስ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌና አካባቢው ተከስቷል።
ሰሞኑን ጠንከር ያለውና ተደጋግሞም እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል።
ወገኖቻችን የመሬት መንቀጥቀጡ ካየለባቸው ቦታዎች ቤታቸውን ጥለው ለመውጣት እየተገደዱ ይገኛሉ።