TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EZEMA #FreedomandEqualityParty

በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዘጋጅቶታል የተባለውና “የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና” የሚል ርእስ ያለው ሰነድ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ነው።

በዚሁ ሰነድ መነሻነትም ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የፓርቲው ስም አሉታዊ በሆነ መንገድ በመጠቀሱ ማብራሪያ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ህዝብ ግንኙነት ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ከትላንት ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረውን ሰነድ'' ኢዜማን የማያወክል እና ኢዜማ የማያዉቀዉ'' ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ፓርቲው ፥ ''...በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያለውን አረዳድ እና የወደፊት ተስፋ በመፅሀፍት አሳትሞ እና ህዝብ እንዲያዉቅ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ነው ...ለዚህም መፅሃፊት ፩ እና ፪፣ የፓርቲውን ፕሮግራም፣ የዜጎች መድረክ እትሞች እንዲሁም ምርጫ 2013 የቃልኪዳን ሰነድ ማየት ይቻላል'' ሲል ገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#EZEMA : በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ጉባዔው በዛሬ ውሎው ፦

1. የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ የተጠየቀባቸው አንቀፆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል።

2. በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል።

3. ከግጭት ቀጠና የመጡ የጉባዔ አባላት በአካባቢያቸው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለጉባዔ ተሣታፊዎች ግንዝቤ እንዲረዳ ያቀርባሉ።

ጉባዔው ነገ እሑድ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ·ም ተጨማሪ ውሳኔዎችን አሳልፎ እንደሚጠናቀቅ ፓርቲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። ጉባዔው በዛሬ ውሎው ፦ 1. የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ የተጠየቀባቸው አንቀፆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል። 2. በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል። 3. ከግጭት ቀጠና የመጡ…
#EZEMA : የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል።

በዛሬው መርሃ ግብር ጉባኤው በፓርቲው መሪ [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ] ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ቀርቦለት ካዳመጠ በኋላ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበው «የአብረን እንሥራ» ጥያቄ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ውይይቱን ተከትሎ ፓርቲው የሚወስነው ውሳኔ እየተጠበቀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል። በዛሬው መርሃ ግብር ጉባኤው በፓርቲው መሪ [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ] ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ቀርቦለት ካዳመጠ በኋላ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበው «የአብረን እንሥራ» ጥያቄ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል። ውይይቱን ተከትሎ ፓርቲው የሚወስነው ውሳኔ እየተጠበቀ…
#EZEMA : ኢዜማ ከገዢው ፓርቲ ብልፅግና የቀረበለትን "የአብረን እንስራ" ጥያቄ ተቀብሏል።

ጉባዔው ውይይት ካደረገ በኃላ አሁን ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት በ536 ድጋፍ፣ 79 ተቃውሞ እና 25 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : ኢዜማ ከገዢው ፓርቲ ብልፅግና የቀረበለትን "የአብረን እንስራ" ጥያቄ ተቀብሏል። ጉባዔው ውይይት ካደረገ በኃላ አሁን ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት በ536 ድጋፍ፣ 79 ተቃውሞ እና 25 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት…
#EZEMA : የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፥ ፓርቲያቸው ከከፍተኛ የፌዴራል ቦታዎች ጀምሮ እስከ ወረዳ መዋቅር ድረስ በመግባት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ያሳወቁት ዛሬ በተጠናቀቀው የፓርታያቸው ጠቅላላይ ጉባኤ የመጀመሪያ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ነው።

" ብልፅግና ፓርቲ ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለን ወደ ተግባር ስንሄድ ብዙ ክርክር ይኖራል" ያሉት የፓርቲው መሪ ፥ " አብሮ መሥራት ከተቻለ እነሱ ውስጥ ካሉ ከጥቂቶቹም ጋር ቢኾን በመተባበር ሰንኮፉን መንቀል ይቻላል" ብለዋል። አክለውም " አሁን ላይ ያለውን ችግር ለማስተካከል ጊዜ ይፈጃል፣ ሁኔታውን ዓይተን የማይስተካከል ከሆነ ለቀን እንወጣለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ኢዜማ ከከፍተኛ የፌዴራል ቦታዎች ጀምሮ እስከ ወረዳ መዋቅር ድረስ ባሉት በመግባት እንደሚሰራም መሪው አክለው ገልጸዋል።

የኢዜማ አባል የሆኑ ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በደቡብ ክልል ካቢኔ ውስጥ ሹመት ተሰጥቷቸዋል፤ ሹመታቸውም ፀድቆላቸዋል።

* ኢዜማ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበለትን የአብረን እንስራ ጥያቄ ሲቀበል ሰባት የጋራ መግባቢያ የሚጠይቁ መሠረታዊ ጉዳዮችን አቅርቦ ተቀባይነት እንዳገኘ ገልጿል ፤ ፓርቲው የጋራ መግባቢያ ብሎ ያቀረባቸው ጉዳዮች ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#EZEMA : ዛሬ በኮንሶ ዞን የሽግግር ምክር ቤት እንዲሁም በጋሞ ዞን ምክር ቤት በነበረው ጉባኤ ላይ 2 የኢዜማ አባላት በዞን ስራ አስፈፃሚነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

በኮንሶ ዞን የኢዜማ ፓለቲካ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አቤል ለሚታ የኮንሶ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በጋሞ ዞን አስተዳደር ደግሞ አቶ መለሰ ጮራ የዞኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( #ኢዜማ ) በመጪው ሰኔ 11 እና 12 / 2014 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል በዚህም ፓርቲውን በመሪነት እና በሊቀመንበርነት የሚመሩ አመራሮችን እንደሚመርጥ አስታውቋል።

ፓርቲው ይህን ያሳውቀው ዛሬ በዋና ፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።

ዕጩ አመራሮቹ ከጠቅላላ ጉባኤው መዳረሻ በፊት ለ19 ቀናት የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ፓርቲው ገልጿል።

ኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ የጠራው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በሚደነግገው መሰረት በሶስት ዓመት አንዴ መደበኛ ጉባኤ ማከናወን ስለሚገባው መሆኑን አመልክቷል።

በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው የኢዜማ መሪ፣ ምክትል መሪ፣ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሐፊ እና የፓርቲው የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ እንደሚመረጡ ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

በግንቦት 2011 የተመሰረተው ኢዜማን ላለፉት ሶስት ዓመታት በመሪነት እያገለገሉ የሚገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሲሆኑ የምክትል መሪነት ስልጣን ያላቸው ደግሞ አቶ አንዷለም አራጌ ናቸው።

የኢዜማን የዕለት ተዕለት ስራ በሙሉ ጊዜ የመምራት ኃላፊነት የተሰጠው ለፓርቲው ሊቀመንበር ነው።

አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢዜማ ሊቀመንበርነት ኃላፊነትን ተረክበው ፓርቲውን እየመሩ የሚገኙ ሲሆን ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው የምክትል ሊቀመንበርነት ቦታውን ይዘው ቆይተዋል።

ኢዜማን በአሁኑ ወቅት በዋና ጸሐፊነት በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል ብሎ የተጠረጠራቸውን የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ 4 አባላቱን አገደ፡፡

በፓርቲው የሥራ ኃላፊዎችና በአባላቱ ላይ እግድ የጣለው የኢዜማ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነው፡፡

ግለሰቦቹ የሳምንት ሥራ መከታተያ ቅፅ በሚል ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው ግንቦት 2፣ 2014 በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የዋትስ አፕ ግሩፕ ላይ በመላክ ተጠናክረው መታገዳቸው ተገልጿል።

የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ከትናንት በስትያ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ሰነዱ ፍፁም ስህተትና የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሂደት ዲሞክራሲያዊነትን የሚያቀጭጭ ብሎታል በውሳኔው፡፡

በመሆኑም ሰነዱን አዘጋጅተዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 የፓርቲው አባላት በሰነዱ ላይ ያላቸውን ተሳትፎና የህግ ጥሰታቸው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለፓርቲው ህገ ደንብ ትርጉምና ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተመርቷል ተብሏል፡፡

ጉዳዩ በኮሚቴው ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስም ፡-

• የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ
• የፋይናንስ መምሪያ ሀላፊው አቶ አንድነት ሽፈራሁ
• የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደና
• አባል የሆኑት አቶ ኢዮብ መሳፍንት ከሀላፊነታቸው ለጊዜው እንዲታገዱ ፓርቲው ወስኗል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( #ኢዜማ ) በመጪው ሰኔ 11 እና 12 / 2014 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል በዚህም ፓርቲውን በመሪነት እና በሊቀመንበርነት የሚመሩ አመራሮችን እንደሚመርጥ አስታውቋል። ፓርቲው ይህን ያሳውቀው ዛሬ በዋና ፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው። ዕጩ አመራሮቹ ከጠቅላላ ጉባኤው መዳረሻ በፊት ለ19 ቀናት የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ፓርቲው ገልጿል።…
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሰኔ ወር ላይ በሚያካሄደው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለፓርቲው ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች የሚወዳደሩ እጩዎችን የአስመራጭ ኮሚቴውን ዛሬ ይፋ አደርገ።

ፓርቲው የምርጫ አመልካቾችን ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ሲቀበል ቆይቷል።

ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ውጤታቸው በየግላቸው እንደተገለፀላቸው የጠቆመው አስመራጭ ኮሚቴው የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ በመጠናቀቁ የዕጩዎች አጠቃላይ ውጤትን ይፋ አድርጓል።

ለፓርቲው #መሪነት ለመጨረሻ ውድድር ያለፉ የጣንራ ተወዳዳሪዎች ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ / አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን→ 99 ፤ አቶ አንዱአለም አራጌ / ሀብታሙ ኪታባ → 84 ፤ ፀጋው ታደለ / አየለ ዳመነ → 80 ናቸው።

[ ተጨማሪ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን መረጃ ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ ]

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ፕ/ር…
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ነው አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት ፣ ትዕግስት ማጣት የሚመጣ ነው " - ኢዜማ

በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያለውን ግምገማ በተመለከተ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። 

Q. በተለያየ ጊዜ ዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት እንደማይችሉ ይገለጸል። ከሰው ሕይወት የሚበልጥ ነገር ደግሞ የለም። እንደ ፓርቲ ለመፍትሄ ምን እየሰራችሁ ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" ችግሮችን በየትኛውም ወገን በኃይል ለማስፈጸም ከመሞከር በፊት በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጠይቀናል።

ነገር ግን በየትኛውን አካል ተሰሚነት አላገኙም። ላለማግኘታቸው ማስረጃዎቹ አሁን ያሉት ግጭቶች ናቸው።

ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ሂደው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት፣ ትዕግስት ማጣትም ጭምር የሚመጣ ነው። የግጭቶቹን መንስኤ በማየት እንዲፈቱ ማሳሰቢያዎችን እየሰጠን ነው። "

Q. አንዳንዶች " መንግስት በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን ግጭት ስለሚፈልገው እንጂ ማስቆም አቅቶት አይደለም " የሚሉ ትችቶች ሲያቀርቡ ይስተዋላል። በዚህ ጉዳይ ፓርቲዎ ምን ይላል ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" አንድ መንግስት የተረጋጋ ሰላም ሲኖር ነው ሊጠቀም የሚችለው ብለን እናምናለን።

ችግሮች ባሉበት መንግስት ዘላቂ የስልጣን ማራዘም፣ የልማት ውጤት ማምጣት አይችልም። ስለዚህ ግጭቶቹ እንዲባባሱ ፍላጎት አለው ብለን አናምንም።

ግን ለ5 ዓመታት መንግስት ለምን ችግሮቹን ማስቆም አልቻለም ? ብለን ካየን አንደኛ የግጭቶቹን ባሕሪ መውሰድ ያስፈልጋል።

ቀውሶቹ ውጫዊና ውስጣዊ ብለን ብንከፍል እንኳ ግጭቶች እየተነሱ ያሉት ብልጽግና ውስጥ ባሉ ኃይሎች ነው። 

የክልል ልዩ ኃይልን ትጥቅ ከማስፈታት፣ ተፈናቃዮችን ከማስመለስ ጋር ተያይዞ መንግስት ይወስዳቸው የነበሩ እርምጃዎች ፓለቲካዊ ጉዳዮች ፓለቲካዊ የሆነ መፍትሄ ማግኘት ሲገባቸው ያንን ላለማድረግ እየተፈጠረ ያለ ግጭት ነው። "

Q. ፓርቲያችሁ ኢዜማ “ የመንግስት ተለጣፊ ” የሚል ስያሜ / አስተያዬት ሲሰጠው ይስተዋላል። ምላሽዎ ምንድን ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" መንግስት እየሰራቸው ያሉ ግድፈቶችን እያስቀመጥን ነው። እንደዛ የሚባለው በምን መስፈርት እንደሆነ አይገባኝም። እኛ በአግባቡ ስራችንን እየሰራን ነው።

ለሚነሱ አሉቧልታዎች ምላሽ መስጠት አንችልም ፤ ጊዜ የለንም ፤ እኛ ሥራ ላይ ነን።

እንደዚህ የሚሉት መስራት የማይችሉ ሰነፎች ናቸው። "

Q. በኢትዮጵያ ስላለው የጸጥታ እና የደኀንነት ሁኔታ የፓርቲዎን ግምገማ ቢያጋሩ ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ በተለይ ባለፉት 3 ዓመታት እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

መጠኑ በተለያየ ደረጃ ይሁን እንጂ በተለያዩ ክልሎችና ወረዳዎች ላይ ያሉ ግጭቶች የጸጥታ ሁኔታውን እያወኩት ይገኛሉ።

የሚታዩት የጸጥታና ደህንነት ችግሮች ዜጎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ጉዳያቸውን እንዳይፈጽሙ ፤ የፓለቲካ ፓርቲዎችም #በነፃነት_ተንቀሳቅሰን የምንፈልገውን የፓለቲካ ሥራ እንዳንሰራ እንቅፋት እየፈጠረ ነው። "

Q. የኑሮ ወድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ ፈትኖታል። ለዚህም  “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም  ” የሚሉ ቅሬታዎች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል። መንግስት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" ኑሮ ውድነቱ በተለይም #መካከለኛ_ገቢ የሚኖረው ህብረተሰብ ተመግቦ ማደር የማይችልበት፣ ልጆቹን የማያስተምርበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የኑሮ ውድነቱ በየቀኑ ከቁጥጥር ውጪ እየወጣ ነው ያለው።

በዚህ ሁኔታ እንኳ ሠራተኞች የወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው እየሰሩ ነው።

በተቃራኒው ደግሞ መንግስት ለቅንጡ ፕሮጀክቶች የሚያወጣቸው በጀቶች አሉ። መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ ኑሮ ውድነቱን የዘነጋ ነው። "

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ? ለቀጣዩ ምርጫስ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" የጸጥታው ችግር የፓለቲካ ፓርቲዎች በሚፈለገው ደረጃ ተንቃሳቅሰው አባሎቻቸውን እንዳይቀሰቅሱ፣ ደጋፊዎቻቸውን እንዳያገኙ አድርጓል። እኛም ያንን እያደረግን አይደለም።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመንግስት ሚዲያዎችን እንኳ መጠቀም አይችሉም።

የመንግስት ሚዲያዎች የብልጽግና ልሳን ሆነዋል። የብልጽግና እንጂ የመንግስት ሚዲያ ሊባሉ አይችሉም። 

ስለዚህ የፓለቲካ ምህዳሩ ከቀን ቀን እየጠበበ ነው። ይሄ ደግሞ መድብለ ፓርቲ በታወጀበት አገር ላይ አይጠቅምም።

የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን እያራመድን ነው እንላለን፤ መሬት ላይ ያለው ሀቅ ግን አንድ አውራ ፓርቲ ብቻ ኖሮ (ብልጽግና) እሱን ብቻ እያሞገስን እንድንኖር ነው።

ብልጽግና በቀጥታ እየሄደ ያለው ራሱን ወደ አውራ ፓርቲ ለመቀየር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።

‘ 13 ሚሊዮን ፣ 14 ሚሊዮን #አባላትን_አፍርቻለሁ ’ ይላል፤ ከመራጩ ሕዝብ ግማሹን አባል አድርጌአለሁ የሚል ከሆነ ምርጫ ቢመጣም ትርጉም የለውም። ለይስሙላ የሚደረግ ምርጫ ነው። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#EZEMA #የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ?

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" ... የመንግስት መገናኛ ብዙኃን የአንድን ወገን ሀሳብ ብቻ ወደ ሕዝብ ከማድረስ አልፈው ይኽን ከፍተኛ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል የሚችል ውሳኔ እንደ ምስራች በ ' እንኳን ደስ አላችሁ ! ' አጅበው ማቅረባቸው ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ፤ አሁንም ከገዢው ፓርቲ ጥገኝነት ወጥተው ሙያቸውን የሚያስከብሩ የመረጃ ብዝሃነትን እና ፍትሃዊነት የሚያረጋግጡ ዘገባዎችን ለመሥራት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ያረጋገጡበት ነው። " - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ " ፖሊሲ የማውጣት ሉዓላዊነትን የሚገድብ ማሻሻያ ውጤቱ ቀውስ ጋባዥ ትርፉም ሀገራዊ ዕዳ ነው " በሚል የላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። #EZEMA

@tikvahethiopia
#EZEMA

" የህዝባዊ በዓላት የፖለቲካ መድረክ ሊሆን አይገባም " ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ ገለጸ።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ " ኢሬቻ " በዓልን በማክበር ሒደት በመንግሥት መዋቅሮች እና በመንግሥታዊ ኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ባለሥልጣናት ባሕሉ ካለው ሕዝባዊ እሴት ባፈነገጠ መልኩ ባሕሉን ከሕዝቡ ባለቤትነት ነጥቆ ፖለቲከኞቹ ዋነኛ አጋፋሪ ሆነው መጥተዋል ብሏል።

ይህ በሌሎች ዘንድ የመገለል እና የስጋት ስሜት ይፈጥራል ሲል አመልክቷል።

" ገዢው ፓርቲም በዚህ መልኩ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚመስል መልኩ መንቀሳቀሱ ተገቢ አይደለም ብለን እናምናለን " ብሏል።

ፓርቲው ፤ በተለይ ለባሕሉ ተብሎ በተለያዩ አካባቢዎች ከተቋማት እና ከንግዱ ማኅበረሠብ በድጋፍ ስም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ የንግድ ማኅበረሠቡን በሚያስጨንቅ እና ከአቅም በላይ የሆነ ከፍተኛ አስገዳጅ የገንዘብ መዋጮ የመጠየቅ እንቅስቃሴ እንዳለ ጠቁሟል።

ይህ ተግባር " ማኅበረሠቡን ከፍተኛ ምሬት ውስጥ በመክተት ባሕሉን በስጋት  እንዲመለከተው እያደረገ ይገኛል " ብሏል።

" የባሕሉ ባለቤት የሆነው ሕዝብ ' ተቋማትን እና ግለሰቦችን አስጨንቃችሁ መዋጮ በመሰብሰብ በዓሉን አድምቁልኝ ' አይልም ፤ ይህንንም ሕገወጥ ተግባር የሚጠየፈው መሆኑን አንዳች ጥርጥር የለንም " ሲል ገልጿል።

" የየትኛውንም ማኅበረሠብ ባሕላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ በዓል ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ባሕሉን መበረዝ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል " ያለው ፓርቲው " ይህን መሰል የአደባባይ ክብረ በዓላት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃነት መጠቀምን ፍፁም እናወግዛለን " ብሏል።

በንግዱ ማኅበረሠብ ላይ እየተደረገ ያለውን ተጠያቂነት የሌለበት ሕገወጥ ጫናን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ ድርጊቶችን መንግሥት በቶሎ እንዲያቆም አሳስቧል።

መንግሥት ባሕሎችን ጠንቅቆ ለሚያውቀው ማኅበረሠብ እንዲመልስ መሠረታዊ ኃላፊነቶቹን ብቻ በቅጡ እንዲወጣም ጠይቋል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia