TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
መጤ-ጠል ጥቃት በደቡብ አፍሪካ‼️

በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ አካባቢ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች የገቡና እዚያው የሚኖሩ ሰዎችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት #ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዪቱ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተናግረዋል።

ባለፈው ሣምንት በጀመረው በዚህ ጥቃት ማንዲኒ በምትባል ቦታ ያሉ የኢትዮጵያዊያን ሱቆች መዘረፋቸውን ገልፀዋል። ፕሪቶሪያ የሚገኘው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

#ቪኦኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ከአለም ሀገራት ቀዳሚ ተባለች! በምን ያላችሁ እንደሆነ፦ ኢትዮጵያ ከአለም ሀገራት ቀዳሚ የተባለችው #በተፈናቃይ ቁጥር ነው!!
.
.
/BBC/

በባለፈው የፈረንጆች ዓመት በዓለም ዙሪያ አዲስ ከተፈናቀሉ ሰዎች መካከል #ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው መረጃ አመልክቷል።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር 1.5 ሚሊዮን ሲሆን ከእነዚህም መካከል 98 በመቶዎቹ እዚያው ሃገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው። ይህ አሃዝ ቀደም ሲል ከነበረው ከእጥፍ በሚበልጥ ቁጥር የጨመረ ሲሆን ከዚያም በኋላ ቁጥሩ ጨምሯል።

ለዚህ መጠኑ ከፍተኛ ለሆነው የሃገር ውስጥ መፈናቀል ተጎራብተው በሚኖሩ የተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል ባለፈው ዓመት ባጋጠሙ ግጭቶች ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert “ኢትዮጵያ ውስጥ #ጥላቻና ብጥብጥ ከሚቀሰቅሱ የዳያስፖራ አባላት የተወሰኑት ዩናየትድ ስቴትስ የሚገኙ ናቸው” ሲሉ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ አምባሳደር ተናግረዋል።

“ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙበት ምቾትና ደኅንነት ውስጥ ሆነው እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻና ብጥብጥ ያነሳሳሉ” ብለዋል አምባሳደር ማይክ ራይነር።

ሰሞኑን በተመሣሣይ ጉዳይ ላይ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ጥላቻና ብጥብጥ ያነሳሳሉ” ያሏቸውን “አንዳንድ” የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት “የእውነት አምላክ ይፍረድባቸው” ሲሉ አማርረዋል።

የሚባሉትን #ኢትዮጵያዊያን አስመልክቶ በሁለቱ ሃገሮች መካከል የተደረገ ንግግር ስለመኖር አለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
”የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ለእኛ #ኢትዮጵያዊያን ክብራችን ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ #ETH

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07-14
#ኢሬቻ2012

"አዲስ አበባ የሁሉም #ኢትዮጵያዊያን ከተማ እንደመሆኗ መጠን የኦሮሞ ህዝብም በከተማው የኢሬቻን በዓል ለማክበር በመቻሉ የተሰማኝ ደስታ ከፍ ያለ ነው፡፡ በቀጣይነትም ከተማችን አዲስ አበባ ኃላፊነት ወስዳ የኢሬቻን በዓልን ጨምሮ ሌሎችን የሃገራችን በዓላት እና እሴቶች በሃገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እና በዓለም መድረኮች ሁነቶችን በመጠቀም ታስተዋውቃለች። ከተማ አስተዳደራችን እና ነዋሪዎቿ በታሪክ አጋጣሚ የዚህ ታሪካዊ ኃላፊነት አስተናጋጅ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል፡፡ በመጨረሻም የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በዚህ ደረጃ በተቀናጀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ የከተማችን ነዋሪወች እና ባለሃብቶች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡" ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን"በቤይሩት ነዋሪ ኢትዮጵያውያን
.
.
ባለፉት ሰባት ወራት ለሥራ ወደ ሌባኖስ ካቀኑ #ኢትዮጵያዊያን መካከል ሰላሳ አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን እንዳጡ በሊባኖስ ያሉ የኢትዮጵያዊያንና ሌሎች የበጎ አድራጎት ማህበራት ይፋ አደረጉ።

ለኢትዮጵያዊያኑ ህይወት መጥፋት በአብዛኛው እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው በአሰሪዎቻቸው በሚፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍና ጥቃት ሳቢያ ራሳቸውን በማጥፋት እንዲሁም ካሉበት ኢሰብዓዊ የስቃይ ኑሮ ለማምለጥ በሚደርጉት ትግልና ጥረት እንደሆነም ተገልጿል።

ይህ ይፋ የሆነው በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እየገጠማቸው ያለውን አስከፊ ችግር በተመለከተ "መንግሥት የኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችን ሞትና ስቃይን ለማስቆም" አፋጣኝ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በጠየቁበት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ላይ ነው።

"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን"

"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩት ኢትዮጵያዊያኑ በአገሪቱ ያለው ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለዜጎቹ ደህንነትና መብት እየሰራ ባለመሆኑ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ በአጽንኦት ጠይቀዋል። "በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ስላለው ግፍና ሰቆቃ በይገባኛል ስሜት አገርን ወክሎ በመንቀሳቀስ ረገድ በሌባኖስ ያለው የኢትዮጵያ ቆንስላ ሙሉ ኃላፊነትም ሆነ ግዴታ ቢኖረውም፤ እውነታው ግን ፍጹም ከዚህ የራቀ ነው" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በለይቶ ማቆያ የነበሩ 3 ሰዎች ነጻ ሆነዋል!

ከጅቡቲ ከተመለሱ 814 #ኢትዮጵያዊያን መካከል በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ የነበሩ 3 ሰዎች ነጻ መሆናቸው መረጋገጡን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል አዋሳኝ ከሆነው የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ጋር በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#LIVE

የሴቶች ማራቶን መካሄድ ጀምሯል !

#ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በጉጉት የሚጠበቁበት የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ ጀመረ ጥቂት ደቂቃዎችን ተቆጠርዋል።

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን!

@tikvahethsport
#Ethiopia

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፣ ጳጉሜ 3/2013 ዓ. ም. ያቀረቡትን ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ሲያጠቃልሉ፣ #ኢትዮጵያዊያን በሙሉ መስከረም 1/2014 ዓ. ም. የሚያከብሩት አዲሱ ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን በመመኘት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ መከሰቱን አስታውሰው፣ አዲሱ ዓመት፣ የተመኙትን ሰላም አግኝተው የወንድማማችነት እና የአንድነት ሕይወት የሚኖሩበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በምታስተዳድራቸው ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በሙሉ ከጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ሰለኢትዮጵያ ሰላም በመጸለይ ላይ እንደሚገኙ ቤተክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቃለች።

በተለይ የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሠራተኞች ሰኞ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት በእንድ ላይ በመሰብሰብ ልዩ ጸሎት እና ምህልላ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሀገራችን የተለያዩ እካባቢዎች በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ያሉበት ስፍራ ድረስ ሄዶ በመጎብኘት እና ፈጥኖ ደራሽ እርዳታ በማድረግ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆኗን ገልፃለች።

በጳጳሳት ሳይቀር የተመሩ የተለያዩ የልዑካን ቡድኖችን በመላክ ጉብኝት ካደረገችባቸው አካባቢዎች መካከል ፦
- የደቡብ፣
- የኦሮሚያ፣
- የትግራይ
- የአፋር እና የአማራ ክልሎች ይገኙባቸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የእርቅ እና የሰላም ግንባታ ተግባራትን በማከናወን የተሳካ ውጤት ማስመዝገቧን ቤተክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከችው መልዕክት ገልፃለች።

@tikvahethiopia
#GudafTsegay #TigistAssefa

የዓለም አትሌቲክስ የአመቱ ምርጥ ሴት አትሌት ዘርፍ የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ተደርገው ድምፅ እየተሰጠ ይገኛል።

ሁለት #ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከምርጥ አስራ አንድ እጩዎች ውስጥ ይገኙበታል።

እጩዎቹም ፤ በቅርቡ የአለም የማራቶን ሪከርድን መስበር የቻለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ትዕግስት አሰፋ እንዲሁም የ5000ሜ የዓለም ክብረወሰን የሰበረችው ጉዳፍ ፀጋይ ናቸው።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ አመት የ5000 ሜትር የአለም ክብረወሰን ከመስበሯም በተጨማሪ የ10,000ሜ የዓለም ሻምፒዮን እንደነበረች ይታወሳል።

ምርጫው እንዴት ይካሄዳል ?

የዓለም አትሌቲክስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የአሸናፊዎች ምርጫ ለዓለም አትሌቲክስ ኮሚቴ እና ለዓለም አትሌቲክስ ቤተሰቦች ድምፅ በኢሜል መስጠት እንደሚቻል ተገልጿል።

ደጋፊዎች እንዴት መምረጥ ይችላሉ ?

ሁሉም የአትሌቲክስ ደጋፊዎች የሚመርጧቸውን አትሌቶች ፎቶ በአለም አትሌቲክስ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በመፈለግ በፌስቡክ ፣ ዩቲዩብ እና ኢንስታግራም ላይክ በማድረግ እንዲሁም በ " X " ሪፖስት በማድረግ መምረጥ ይችላሉ።

ጉዳፍ ፀጋይን #ላይክ / #ሪትዊት ለማድረግ ፦

ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/100064391421386/posts/pfbid0hS68YYaTusAL2g6TrYMbMuuW1pDFv2KBQbfcD4piPiJc3XU1iDyb45k6CKCf3bgYl/?app=fbl

X / የቀድሞ ትዊተር ላይ ሪትዊት ለማድረግ ፦ https://twitter.com/WorldAthletics/status/1712082175250563508?t=rpGi0sYnnozLQvDtN4RTKQ&s=19

ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/p/CyQkhc9Mry7/?igshid=NjIwNzIyMDk2Mg==

ትዕግስት አሰፋን #ላይክ / #ሪትዊት ለማድረግ ፦

ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/100064391421386/posts/pfbid01BPvP9Vb4sF7tRxmX2Lb5BqWDgXjFB17Agijp9vWQWsJufvbrkXL3yH7PZbidcaTl/?app=fbl

X / የቀድሞ ትዊተር ሪትዊት ለማድረግ ፦ https://twitter.com/WorldAthletics/status/1712082042391802157?t=xlF0PNgzEhsBxSb56pANlw&s=19

ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/p/CyQjzyRM8Iv/?igshid=NjIwNzIyMDk2Mg==

(ሼር ያድርጉ)

@tikvahethiopia
" የ11 ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን ነው የተገኘው " - አይ ኦ ኤም

" ፍልሰተኞችን የጫነ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ መስጠሙን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መሞተዋል ፤ አልያም ጠፍተዋል " ሲል የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አሳውቋል።

አደጋው የበርካቶችን ህይወት ከቀጠፉና በተደጋጋሚ ከደረሱ የጀልባ መስጠም አደጋዎች የቅርብ ጊዜው ነው።

በታይዝ ግዛት ጀልባው ለአደጋ በተዳረገበት ወቅት 25 #ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን እና ሁለት የመናዊ መረከብ ዘዋሪዎችን ጭኖ እንደነበረ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም (አይ ኦ ኤም) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እስካሁን ድረስ የ11ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን የኤደን ባህረሰላጤ እና ቀይ ባህርን በሚያገናኘው በባበል ኤል መንደብ መተላለፊያ ባህር ዳርቻ መገኘቱን እና ሁለቱን የመናዊያን ጨምሮ 14 ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል።

ፍልሰተኞች ከጂቡቲ የተነሱ እንደነበሩ አይ ኦ ኤም አስታውቋል ።

እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየመን የሚደርሱት ስደተኞች በሦስት እጥፍ አድጓል።

በ2021 27,000 ገደማ የነበረው የፍልሰተኞች ቁጥር ባለፈው አመት ከ97,200 በላይ ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 380,000 የሚጠጉ ስደተኞች ግጭት ባየለባት ሀገር ውስጥ ይገኛሉ።

የመን ለመድረስ ፣ፍልሰተኞቹ ቀይ ባህርን ወይም በኤደን ባህረ ሰላጤ ለማቋረጥ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት አደገኛ በሆኑና በተጨናነቁ ጀልባዎች ይወሰዳሉ።

ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 2,082 ስደተኞች የገቡበት አልታወቀም ከእነዚህ መካከል 693 ያህሉ ሰጥመው ቀርተዋል።

በሰኔ ወር ቢያንስ 49 ስደተኞች በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ጀልባቸው በመስጠሙ ሞተዋል።

140 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንዳልታወቀ ድርጅቱ አስታውሷል።

ተጨማሪ 62 ስደተኞች ባለፈው ሚያዝያ ወር የመን ለመድረስ ሲሞክሩ በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ላይ በተከሰቱት ሁለት የጀልባ መገልበጥ አደጋዎች ህይወታቸው አልፏል። #IOM #VOA

@tikvahethiopia