TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል። ገቢ ማሰባሰቢያው…
#Update
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን ፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።
በመርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም ፤ " የመርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማ ባለን አቅም ሁሉ ለወገን መድረስ ነው " ብለዋል።
" ረሃብ ጊዜ አይሰጥም " ያሉት የማህበሩ ሰብሳቢ " በውጭ ድርጅቶች ፣ በመንግስትና በሌሎችም የተለያዩ አካላት ብዙ እርዳታዎች ይደረጋሉ (የምግብም የአይነትም) በተለይ ግን ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ብዙ ጊዜ ትኩረት አያገኙም " ብለዋል።
" እነዚህን ክፍተቶች እና ጉድለቶች መሙላት አለብን " ሲሉ አስገንዝበዋል።
" አሁን ላይ በየቦታው ያሉት መፈናቀሎች ፣ በየቦታው ያሉ የረሃብ ችግሮችን በማሰብ ማህበረ ቅዱሳን ሌሎች አገልግሎቶችን ገቶ መጀመሪያ ነፍስን የማዳን፤ ህይወትን የመታደግ ስራ ይቀድማል ብሎ እየሰራ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሁሉን ማድረግ የምንችለው ስንኖር ነው " ያሉት ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ " እኛ በልተን እያደርን ሌሎች ወገኖቻችን በረሃብ እና ጥማት መሞት ስለሌለባቸው ' ኑ ቸርነትን እናድርግ ! ' በሚል በዚህ በታላቁ ዐብይ ጾም ወቅት ዝግጅቱ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
ዛሬ ሚሊኒየም አዳራሽ መገኘት ያልቻሉ ምዕመናን በየቤታቸው ሆነው በማህበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የሂሳብ ቁጥሮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000309803648 ፣ አሃዱ ባንክ 0025393810901 ፣ ወጋገን ባንክ 0837331610101 ፣ አቢሲንያ ባንክ 37235458 ፣ አዋሽ ባንክ 01329817420400 ድጋፍ ማድረግ ይቻላሉ ተብሏል።
ፎቶ ፦ ከማኅበረ ቅዱሳ ቴሌቪዥን
#TikvahFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተለያዩ ምርጥ የልጆች ቻናሎችን እና ሌሎች መዝናኛዎችን ከ290 ብር ጀምሮ በዲኤሲቲቪ
የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።
የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

" በቅርቡ 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ በአንድ ባንክ ተልኮ ይዘናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለት ቦታ (ከመንግስት ጋር እና ጫካ መንግስትን ለመጣል ከሚታገሉ ጋር) የሚጫወቱ አንዳንድ ባለሃብቶች አሉ ሲሉ ተናገሩ። ይህን የተናገሩት ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው። ባለሃብቶቹ በምክክር መድረኩ ስለ #ሰላም ጉዳይ ያነሱ ሲሆን ጠ/ሚስትሩም…
" እኛ አንቆይም በ5 እና 6 ወር እንጨርሳለን " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከታማኝ ከፍተኛ የግብር ከፋዮች / ባለሃብቶች ጋር በነበራቸው ምክክር ወቅት ከሰሞኑን በአዲስ አበባ እየታየ ስላለው ፈረሳ አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
" ብዙ ቦታ እየፈረሰ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " ለምንድነው? የምትሉ ከሆነ የወደፊት የኢትዮጵያም፣ የአፍሪካም፣ የዓለምም የኢኮኖሚ አቅጣጫ 70 እና 80 ፐርሰንት አይቲ እና ቱሪዝም ነው። ሃብት ያለውም እዛ ነው ቱሪዝም እና አይቲ ደግሞ ኤርጎኖሚክስ በጣም ትልቅ ተፅእኖ ያደርግባቸዋል። የተስተካከለ አካባቢ ካልሆነ ይረበሻሉ " ብለዋል።
አዲስ አበባን መቀየር ካልተቻለ የሚታሰበውን ያህል የውጭ ሀብት ማምጣት አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል።
" ዱባይ እንዴት ገንዘብ እንደሄደ ታውቃላችሁ፤ መሰረተ ልማቶች የሚታዩ ነገሮች በጣም በከፍተኛ ደረጃ ሃብት ይስባሉ " ብለዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ" አሁን የሚፈርሰው እንደሚባለው አይደለም። እኛ ብዙ አንቆይም ቢገፋ 5 እና 6 ወር ነው እንጨርሳለን " ሲሉ ገልጸዋል።
" የቦሌው መንገድ እኛ የምናስበው ብዙ ሀገር ሲኬድ እንዳሉት ዎክ ማድረጊያ ያለው መንገድ እንዲሆን ነው " ያሉ ሲሆን የመንገዱ መስፋት አብዛኛው ሰው እግረኛ ስለሆነ እንደሚጠቅም ገልጸዋል። መንገዱ የባይክ ሩትም እንዲጨመርበትና #ሰፊ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ከቦሌው መንገድ በተጨማሪ የሚክሲኮ መንገድ፣ የመገናኛ ጫካ ሲኤምሲ መንገድ ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑም ጠቁመዋል።
" አዲስ አበባ ላይ ትልቁ ድህነትና ችግር ያለው መሃከል ላይ ነው፤ መርካቶ፣ ፒያሳ፣ ሜክሲኮ የሚባለው ነው። ሲኤምሲ፣ ለቡ እንደዛ አይደለም ዋናው ችግር ያለው መሀከል ነው ዋናውን ችግር ደፍረን ካፈረስነው በ5 ዓመት ከተማው ምን እንደሚመስል ታዩታላችሁ " ብለዋል።
" በዚህ ሂደት፦
-በግለሰብ ደረጃ አጥሬ ተነካብኝ ብለው የሚያዝኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ
-ባለስልጣናትም ያስቸግሩናል አጥር ሲነካባቸው የሚፈርስባቸው ብዙ ስለሆነ፣ የመንግስት ቤቶች ስለሚፈርሱ
-የመንግስት ኪራይ ቤቶች የሚያከራየውም ይጮሃል
-የቀበሌ ቤት የሚያከራየውን ይጮሃል... ብዙ ነው ጩኸት ያለው። ጨክነን ካላፈረስን ግን ሀገር አይሰራም " ሲሉ ገልጸዋል።
" የአዲስ አበባን ለውጥ በአንድ አመት እናየዋለን፤ ያኔ ቱሪስት በደንብ ይመጣል። ያኔ የባላሃብቶች ንብረት ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል " ብለዋል።
እየተካሄደ ያለውን ስራ ባለሃብቶቹ እንኳን በትዕግስት እንዲጠብቁ የጠየቁት ዶ/ር ዐቢይ " ከማማት ውጡ፣ አፈረሱት ምናም የሚለውን ትታችሁ በትዕግስት ጠብቁን በአንድ ውስጥ ከተማውን ካለበት ደረጃ ከፍ እናደርገዋለን የዛኔ ልጆቻችሁን ዱባይ ከምትወስዱ ታቆያላችሁ እዚህ " ብለዋል።
በሌላ በኩል፤ ጠ/ሚኒስትሩ እየፈረሱ ባሉ ቦታዎች ፋይበር እንደሚቀበር እና ውጭ ላይ የሚታዩት ሽቦዎች እንደሚቀበሩ ተናግረዋል።
" ቦሌ ላይ ይሁን ፒያሳ መንገድ የምናፈርሰው አሮጌ ቤት ብቻ አይደለም። እዛው ላይ ፋበር እንዘረጋለን፣ እዛው ላይ በየቦታው ያለውን ሽቦ እንቀብራለን፣ የውሃ መስመር እንዘረጋለን ዩቲሊቲስ በቢሊዮን እያወጡ ነው ያሉት " ብለዋል።
" አዲስ አበባ ውስጥ ከ4 ኪሎ አንስቶ እስከ ሜክሲኮ ቢነዳ ብርሃን አለ ጨለማ አለ፤ ብርሃን አለ ጨለማ አለ መብራት ዘላቂ ሆኖ አይታይም፥ ይህ መሰረተ ልማቱን ካልቀየርነው በስተቀር ሽቦው የተቀጣጠለ ስለሆነ ኃይል እና ዳታ (ኢንተርኔት) አክሰስ ማድረግ አይቻልም " ሲሉ አስረድተዋል።
አሁን እየፈረሰና እየተሰራ ያለው ስራ የሚቋረጠውን ኃይል እንዲሁም የኢንተርኔት ዳታ ችግርን ለመፍታትም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።
" ካልፈረሰ ሌላ አማራጭ የለም " ብለዋል።

ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጠንከር ያለ ዝናብ ዘንቦ ነበር።
በተለይ በዳውሮ ዞን በ " ቶጫ ወረዳ " በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከቀኑ 7:30 እስከ 8:10 ድረስ በረዶና ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብልና በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱ ተሰምያል።
ወቅቱን ካልጠበቀ ከፍተኛ ዝናብ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ከሚችለው አደጋ የወረዳው ህዝብ እራሱንና ወገኑን እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።
ዝናቡ ቀጣይነት ልኖረው ስለሚችል ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ተብሏል።
በሌላ በኩል፤ ላለፉት ሳምንታት ከፍ ያለ ሙቀት ስታስተናግድ የነበረችው የሀገራችን መዲና አዲስ አበባ ዛሬ ጠንከር ያለ ዝናብ አግኝታለች።

#Adwa
በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታፈነች / የታገተች ታዳጊን ተማሪ ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባታል። አፈናው ከተፈፀመ 5 ቀናት ሆኖታል።
የአፈናው ድርጊት አፈፃፀም እና የጉዳዩ አሳሳቢነት ምን ይመስላል ?
እሮብ መጋቢ 11 ቀን 2016 ዓ/ም የ16 አመት ታዳጊ ተማሪዋ ማህሌት ተኽላይ ቀን ትምህርት ውላ አመሻሽ ቋንቋ ወደ ምትማርበት ማእከል ብቻዋ በመጓዝ ሳለች ባጃጅ ይዘው በመጡ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች አፍነው ወሰድዋታል።
ተማሪ ማህሌት ከቋንቋ ት/ቤት እንደልማድዋ በሰአትዋ አለመመለስዋ ቤተሰቦችዋ ተጨንቀው እያለ ወላጅ አባትዋ የልጃቸው የሞባይል ስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል።
በልጃቸው የሞባይል ቁጥር የተደወለባቸው አባት በወላጅ በስስት ' ልጄ ' ብለው ሞባይላቸው ያነሳሉ።
በሞባይል የሰሙት ድምፅ ግን ከዚህ በፊት ሰምተውት የማያውቁ የወንድ ድምፅ ነበር። ድምፁ በመሃል የልጃቸው ለቅሶ ፣ ፍርሃትና የ 'አስለቅቁኝ ' ልመና አሰማቸው።
ቀጥሎ የልጃቸው ድምፅ በማራቅ " ልጃችሁ በቁጥጥራችን ስር ናት፤ መልሳችሁ በህይወት ልታገኙዋት ከፈለጋችሁ 3 ሚሊዮን ብር ክፈሉ ፤አለበለዚያ እንገድላታለን " የሚል የማስፈራርያ ድምፅ ካሰሙ በኃላ ስልኩን ይዘጋሉ።
የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተማሪ ማህሌት ተኽላይ የመጥፋት ጉዳይ ወደ አባትዋ ደውሎ ይህ መረጃ እስካዘጋጀበት ቀንና ሰዓት ድረስ ታዳጊዋ ማህሌት ከቤት ወጥታ ከቀረች 5 ቀናት ተቆጥረዋል።
የታዳጊዋን ማህሌት ቤተሰቦች እንባ ለማበስና እንቅልፋቸውን ለመመለስ የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ታዳጊዋን አፍነው የወሰዱ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፍለጋ እያካሄደ ነው።
ጉዳዩ እጅግ ያሳሰባቸው የተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፥ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ጉዳይ በማንሳት እየተወያዩበት ይገኛሉ።
" ልጆች አፍኖ ገንዘብ የመጠይቅ ፋሽን መቼ ነው የሚቆመው ? " የሚል ጥያቄ አንስተዋል።
ባለፈው ጥቅምት 2016 ዓ.ም ሚልክያስ ፋኑስ የተባለ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ ህፃን ታግቶ ለማስለቀቅ 4 ሚሊዮን ብር ተጠይቆበት ፤ በፓሊስ ክትትል ከ12 ቀናት ፍለጋ በኋላ ሊገኝ ችሏል።
በመቐለ ከተማ የዓይደር ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ9 አመቱ ሳሚኤል መሓሪ ከበደ ደግሞ ባለፈው ወርሃ የካቲት 2016 ዓ.ም በጠላፊዎች ታግቶ ከተወሰደ በኃላ እንደዲመለስ 4 ሚሊዮን ተጠይቆበታል ቢሆንም ፓሊስና ህብረተሰብ ባደረጉት የተቀናጀ እልህ አስጨራሽ ጥረት ከአንድ ሳምንት በኃላ ተገኝቷል። በድርጊቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

እናንተ ፈንዲሻችሁን ብቻ አዘጋጁ፤ የካናል ፕላስ ክፍያውን በM-PESA ላይ ጣሉት!
M-PESA ላይ ተመዝግበን፣ በM-PESA እንክፈል!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether

" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው " ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት…
" ... ሌላዉ ቢቀር እንዴት እግሯን አጎንብሰዉ ያጠቧት ሴት ፖሊሶች ይረሳሉ ? " - የሀዋሳ ፖሊስ
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ስሜን የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ይታቀቡ ሲል አሳሰበ።
ፖሊስ ፤ " የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ በመጠቀም የሀዋሳ ከተማን ገጽታ ለማጠልሸት የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸዉ ሊታቀቡ ይገባል " ብሏል።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ከሰሞኑ በተደጋጋሚ እንደሚታየዉ ለሰላም ሌት ተቀን እየደከመ ያለዉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በመጥቀስ ስም የማጠልሸት አካሄዶች ውስጥ የገቡ አካላት መኖራቸዉን እየተመለከትን ነው " ብለዋል።
ድርጊቱ አስነዋሪ መሆኑንና የሀዋሳ ከተማን የጸጥታ አካላት ያሳዘነ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንስፔክተር መልካሙ ፥ " በቅርቡ ' ቲክቶክ 'ን ተጠቅሞ የንግድ ድርጅቴ (የውስኪ ቤቴ) ተዘጋ በማለት ሲከስ የነበረዉ ግለሰብ ልክ አይደለም " ብለዋል።
" ጠጥቶ አልከፍልም ያለዉን አካል ለህግ ማቅረብ ሲቻል የተከበረውን የፖሊስ ስም ማጥፋቱ በፍፁም ልክ አልነበረም ፤ አሁንም ቅሬታ ካለ የቆምነው ህግ ለማስከበር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፥ ወይዘሪት ጸጋ በላቸዉ ከተጠለፈችበት ቀን ጀምሮ እሷን ለማግኘት የተንከራቱዉው ወደ ሀዋሳ በመጣችበት ወቅትም ጥበቃና ድጋፍ ባደረገላት የፖሊስ ሀይል ላይ የሰነዘረችዉ ሀሳብ ልክ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
" እሷና ቤተሰቦቿ እንዲያርፉበት ለተፈቀደላቸው ቤትና ለተሰጣቸዉ ጥበቃ ማመስገን ሲገባት እንደእስር ተቆጥሮ ለሚዲያ መጮህ ልክ አይደለም " ብለዋል።
" ሌላዉ ቢቀር እንዴት እግሯን አጎንብሰዉ ያጠቧት ሴት ፖሊሶች ይረሳሉ ? በማለት ለፖሊስ በጎ አድራጎት ምላሹ ይህ ሊሆን አይገባም " በማለት ተችተዋል።
ጨለማ ብርድና ቁር ሳይል በትጋት የሀዋሳ ከተማን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ በሚተጋዉ የጸጥታ ሀይል ላይ የተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚሰነዘሩ የስም ማጥፋቶች ልክ አለመሆናቸዉን በመግለጽ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።
በቅርቡ በፀጋ በላቸው በቲክቶክ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ አግቶ ጠልፎ ወስዶ ባሰቃያት ግለሰብ ላይ በሚዲያዎች የተገለጸው ፍትህ ከእውቅናዋ ውጭ በሆነ መልኩ የእስራት ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መቀነሱን እንደሰማች ተናግራ ያደረባትን ሀዘን መግለጿ ይታወሳል።
ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዲል በተደረገው ፍርድ እጅግ እንዳዘነች የገለጸችው ፀጋ ፤ ካሳለፈችው የስቃይ ሁኔታ ጋር በፍፁም እየሚገባ እንዳልሆነ በእምባ ታጅባ ገልጻ ነበር።
በዚህም ወቅት ህዝብ የማያውቀው ብዙ ነገር እንደተፈፀመ ፤ ከጠለፋው እገታ ከተለቀቀች በኃላ በማታውቀው ምክንያት በፖሊስ ታስራ እንደነበር አሳውቃ ነበር።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከዉ የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

" ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ምን አለ
?
" የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ከሰሰ።
" ክልሉ የትግራይ መሬት በሚመለከት በስርዓተ ትምህርቱ ያሰፈረው ካርታ ኃላፍነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ከፋፍሎ ለማጥፋት ያወጀው ዘመቻ በማስቀጠል በከፋ መልኩ እየሰራበት እንደሚገኝ ማረጋገጫ መሆኑ ተገንዝበናል " ብሏል።
" የአማራ ክልል መንግስት በህዝባችን ላይ አየፈፀመው የቆየውና አሁንም በሃይል በያዛቸው የትግራይ አከባቢዎች እየፈፀመ የሚገኘው ግፍና መከራ ተሰሞቶት በመፀፀት ፈንታ ወደ ባሰ ታሪካዊ ስህተት መግባቱ በቀጣይነት ዋጋ እንደሚያስከፍለው በማወቅ በአስቸኳይ እርምት ማድረግ አለበት " ሲል አስስቧል።
ካቢኔው ፤ " የፌደራል መንግስት ከአሁን በፊት የፌደራል ተቋማት ዛሬ ደግሞ በአማራ ክልል እየተዘጋጁ ያሉ ኃላፊነት የጎደላቸው ካርታዎች እንዲያርማቸውና በጥፋት ፈፃሚዎች ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰድ እየተገባው በዝምታ ማለፉ የጥፋቱ አካል መሆኑ የሚያመላክት ነው " ብሏል።
" የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመፈፀም ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ በሚሰሩበት ወቅት ፤ የአማራ ክልል የሰላም ሂደቱ ለማወክ ይህ መሰል ነገር ጫሪ ጥፋት ሆን ብሎ መፈፀሙ ሊሰመርበት ይገባል " ሲልም ገልጿል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ፥ " የአማራ ህዝብም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በአማራ ክልል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ የቆየውና አሁንም የቀጠለው ግፍና በደል ይቁም ብሎ ከትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎኑ እንዲቆሙ " ብሏል።
" ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል መሉውን ኃላፊነት እንደሚወስድ ለማስታወቅ እንፈልጋለን " ሲል ገልጿል።
በአማራ ክልል በኩል በጉዳዩ ላይ የተሰጠ መግለጫ እስካሁን የለም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ክልሉ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።

#AddisAbaba
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ፕሮጀክት እና ተያያዥ የልማት ሥራዎች ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መስመር የማዛወር ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
በዚህም ሥራው ሲከናወን ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም አደጋ እንዳይከስት ሲባል ሥራው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ ወይም አልፎ አልፎ ለተወሰኑ ሰዓታት #እየተቋረጠ እንደሚገኝ አመልክቷል።
" የመስመር ማዛወር ሥራዎቹ በጥንቃቄና በፍጥነት ለማከናወንና አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው " ያለ ሲሆን ነዋሪዎች ይህን ተረድተው በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።
በዚህ ምክንያት ለሚፈጠሩ ለአገልግሎት መስተጓጎሎችም #ይቅርታ ጠይቋል።
በሌላ በኩል፥ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ በተለይ በስራ መግቢያ እና መውጪያ ሰዓት አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።
በዚህም፦
➡ ከ4 ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
➡ ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
➡ ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ እና ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዝበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።