TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የህክምና ግብዓት እጥረት በጎንደር!

የጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የህክምና ግብዓት እጥረት እንዳለበት ገልጿል።

የጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ገቢያው አሻግሬ በከተማ አስተደር እና በሆስፒታሉ #ሰፊ የሆነ የህክምና ግብዓቶች እንዲሁም የባለሙያዎች ለህክምና የኮቪድ-19 መከላከያ መሳሪያዎች ዕጥረት እንዳለ ገልጸዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለማከም የግብዓት ችግሩን ለመፍታት የጎንደር ወዳጆች ፣ ተወላጆችና ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ ድርጅቶች በአይነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። እስካሁን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ምንጭ ፦ የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቅርቡ 5 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ በአንድ ባንክ ተልኮ ይዘናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለት ቦታ (ከመንግስት ጋር እና ጫካ መንግስትን ለመጣል ከሚታገሉ ጋር) የሚጫወቱ አንዳንድ ባለሃብቶች አሉ ሲሉ ተናገሩ። ይህን የተናገሩት ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው። ባለሃብቶቹ በምክክር መድረኩ ስለ #ሰላም ጉዳይ ያነሱ ሲሆን ጠ/ሚስትሩም…
" እኛ አንቆይም በ5 እና 6 ወር እንጨርሳለን " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከታማኝ ከፍተኛ  የግብር ከፋዮች / ባለሃብቶች ጋር በነበራቸው ምክክር ወቅት ከሰሞኑን በአዲስ አበባ እየታየ ስላለው ፈረሳ አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

" ብዙ ቦታ እየፈረሰ ነው " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " ለምንድነው? የምትሉ ከሆነ የወደፊት የኢትዮጵያም፣ የአፍሪካም፣ የዓለምም የኢኮኖሚ አቅጣጫ 70 እና 80 ፐርሰንት አይቲ እና ቱሪዝም ነው። ሃብት ያለውም እዛ ነው ቱሪዝም እና አይቲ ደግሞ ኤርጎኖሚክስ በጣም ትልቅ ተፅእኖ ያደርግባቸዋል። የተስተካከለ አካባቢ ካልሆነ ይረበሻሉ " ብለዋል።

አዲስ አበባን መቀየር ካልተቻለ የሚታሰበውን ያህል የውጭ ሀብት ማምጣት አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል።

" ዱባይ እንዴት ገንዘብ እንደሄደ ታውቃላችሁ፤ መሰረተ ልማቶች የሚታዩ ነገሮች በጣም በከፍተኛ ደረጃ ሃብት ይስባሉ " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ" አሁን የሚፈርሰው እንደሚባለው አይደለም። እኛ ብዙ አንቆይም ቢገፋ 5 እና 6 ወር ነው እንጨርሳለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የቦሌው መንገድ እኛ የምናስበው ብዙ ሀገር ሲኬድ እንዳሉት ዎክ ማድረጊያ ያለው መንገድ እንዲሆን ነው " ያሉ ሲሆን የመንገዱ መስፋት አብዛኛው ሰው እግረኛ ስለሆነ እንደሚጠቅም ገልጸዋል። መንገዱ የባይክ ሩትም እንዲጨመርበትና #ሰፊ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ከቦሌው መንገድ በተጨማሪ የሚክሲኮ መንገድ፣ የመገናኛ ጫካ ሲኤምሲ መንገድ ዋና ዋናዎቹ  እንደሆኑም ጠቁመዋል።

" አዲስ አበባ ላይ ትልቁ ድህነትና ችግር ያለው መሃከል ላይ ነው፤ መርካቶ፣ ፒያሳ፣ ሜክሲኮ የሚባለው ነው። ሲኤምሲ፣ ለቡ እንደዛ አይደለም ዋናው ችግር ያለው መሀከል ነው ዋናውን ችግር ደፍረን ካፈረስነው በ5 ዓመት ከተማው ምን እንደሚመስል ታዩታላችሁ " ብለዋል።

" በዚህ ሂደት፦
-በግለሰብ ደረጃ አጥሬ ተነካብኝ ብለው የሚያዝኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ
-ባለስልጣናትም ያስቸግሩናል አጥር ሲነካባቸው የሚፈርስባቸው ብዙ ስለሆነ፣ የመንግስት ቤቶች ስለሚፈርሱ
-የመንግስት ኪራይ ቤቶች የሚያከራየውም ይጮሃል
-የቀበሌ ቤት የሚያከራየውን ይጮሃል... ብዙ ነው ጩኸት ያለው። ጨክነን ካላፈረስን ግን ሀገር አይሰራም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የአዲስ አበባን ለውጥ በአንድ አመት እናየዋለን፤ ያኔ ቱሪስት በደንብ ይመጣል። ያኔ የባላሃብቶች ንብረት ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል " ብለዋል።

እየተካሄደ ያለውን ስራ ባለሃብቶቹ እንኳን በትዕግስት እንዲጠብቁ የጠየቁት ዶ/ር ዐቢይ " ከማማት ውጡ፣ አፈረሱት ምናም የሚለውን ትታችሁ በትዕግስት ጠብቁን በአንድ ውስጥ ከተማውን ካለበት ደረጃ ከፍ እናደርገዋለን የዛኔ ልጆቻችሁን ዱባይ ከምትወስዱ ታቆያላችሁ እዚህ " ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ ጠ/ሚኒስትሩ እየፈረሱ ባሉ ቦታዎች ፋይበር እንደሚቀበር እና ውጭ ላይ የሚታዩት ሽቦዎች እንደሚቀበሩ ተናግረዋል።

" ቦሌ ላይ ይሁን ፒያሳ መንገድ የምናፈርሰው አሮጌ ቤት ብቻ አይደለም። እዛው ላይ ፋበር እንዘረጋለን፣ እዛው ላይ በየቦታው ያለውን ሽቦ እንቀብራለን፣ የውሃ መስመር እንዘረጋለን ዩቲሊቲስ በቢሊዮን እያወጡ ነው ያሉት " ብለዋል።

" አዲስ አበባ ውስጥ ከ4 ኪሎ አንስቶ እስከ ሜክሲኮ ቢነዳ ብርሃን አለ ጨለማ አለ፤ ብርሃን አለ ጨለማ አለ መብራት ዘላቂ ሆኖ አይታይም፥ ይህ መሰረተ ልማቱን ካልቀየርነው በስተቀር ሽቦው የተቀጣጠለ ስለሆነ ኃይል እና ዳታ (ኢንተርኔት) አክሰስ ማድረግ አይቻልም " ሲሉ አስረድተዋል።

አሁን እየፈረሰና እየተሰራ ያለው ስራ የሚቋረጠውን ኃይል እንዲሁም የኢንተርኔት ዳታ ችግርን ለመፍታትም ጭምር እንደሆነ ተናግረዋል።

" ካልፈረሰ ሌላ አማራጭ የለም " ብለዋል።

@tikvahethiopia