TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም መግለጫቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ትላንት አዲስ አበባ ሆነው ስለሰጡት መግለጫ ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሰጡት መግለጫ ፤ " ካረፍኩበት ሆቴል እንዳልወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መንገድ ዘጉብኝ ፤ በኃላም ከሌላ ፕሬዜዳንት ጋር (ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት…
" የሶማሊያ ድርጊት ትኩረት ለመሳብና ያልተገባ ወቀሳን ለመሰንዘር ባለመ መልኩ የተሰራ ነው " - ኢትዮጵያ

ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጋር በተያያዘ የሶማሊያ መንግሥት ያሰማው ክስ ትኩረት ለመሳብ እና ያልተገባ ወቀሳን ለመሰንዘር ባለመ መልኩ ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ኢትዮጵያ ገልጻለች።

የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በስኬት ማለቁን ተከትሎ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸው የሶማሊያን ክስ ጉዳይ አንስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ፤ " ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ያሰማችው ክስ ኢትዮጵያ ለእንግዶቿ ያደረገችውን አቀባበል እና እንክብካቤ በፍፁም የሚመጥን አይደለም " ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለጉባኤው የመጡትን የሁሉንም ሀገራት መሪዎች ያለ ልዩነት በጣም በታላቅ አክብሮት እንደተቀበለችና በአዲስ አበባ ቆይታቸው ምንም የደህንነት እክል እንዳይገጥማቸው እንደ አዘጋጅ ሀገር ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዳ እንዳስተናገደች አመልክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ በዚሁ መግለጫቸው ፤ ሶማሊያ የዲፕሎማሲ ባህል ከሚፈቅደው ውጭ እንዲሁም ለየትኛውም ሀገር መሪ ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የጦር መሳሪያ ይዞ / ታጥቆ ወደ ህብረቱ ቅጥር ግቢ ለመግባት ፤ " ለእኛ ብቻ ካልተፈቀደልን " በሚልም " የጦር መሳሪያ ይዘን እንገባለን " የሚል ጥያቄ ማንሳቷን ገልጸዋል።

ይህ የሶማሊያ ድርጊት ትኩረት ለመሳብና ያልተገባ ወቀሳን ለመሰንዘር ባለመ መልኩ መሰራቱን አስረድተዋል።

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበችውን ክስ " አስገራሚ ክስተት ነበር " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ፤ " ክስተቱ በበሳል የሕብረቱ የፀጥታ እና ደህንነት አባላት ስራ ወዲያው መፍትሄ አግኝቷል " ብለዋል።

" የሶማሊያ እንቅስቃሴ ጉዳዩ በተለየ ሁኔታ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንዲስብና የጉባኤው ዋና አጀንዳ ላይ ጥላ እንዲያጠላባት የተፈለገበት ይመስል ነበር ፤ ይህ አሁን ተከስቷል የተባለው ጉዳይ ባይፈፀም ኖሮ ሌላ ሰበብ ተፈልጎ የጉባኤውን መንፈስ ለመረበሽ ሙከራ መደረጉ አይቀርም ነበር ብለን እንድናስብ አድርጎናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወጋገን ሞባይል

በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ወጋገን ሞባይል መተግበሪያን ከፕለይስቶር ወይም ከአፕስቶር በማውረድ ምቾትዎ ተጠብቆ ሂሳብዎን ያንቀሳቅሱ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ::

Download now:
Android:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.act.wegagen&hl

IOS:https://apps.apple.com/in/app/wegagen-mobile/id6472656143
#WegagenBank #WegagenMobile #MobileBanking

Follow us and get more information...
https://linktr.ee/WegagenBank
#JASIRI: ታለንት ኢንቨስተር

- ለፈጣን ዕድገት አቅም ካላችሁ እና አዲስ ቢዝነስ ለመፍጠር ከቆረጣችሁ፤

- በማንኛናውም ዘርፍ ውስጥ ክፍተቶችን መለየት እና እድሎችን ማወቅ ከቻሉ፤

- ትኩረት ባደረጋቹበት ቦታ ሁሉ የስኬት፣ የችግር አፈታት እና ዋጋ የመፍጠር ልምድ ካላቹ፤

- በሙያዊ መስካችሁ ከፍተኛ መረጃ እና እውቀት ያላቹ ከሆነ፤

- በቡድናቹ ውስጥ ካሉ ተመሳሳይ ትልቅ ፍላጎት ካላቸው መስራቾች ጋር ለመገናኘት እና ከመሰረቱ ቬንቸር ለመገንባት እና በቡድን ለመስራት ዝግጁ ከሆናችሁ፤

- ስራዎን በሙሉ ጊዜ ለመገንባት ቃል ገብታቹ እና በሁሉም ታለንት ኢንቬስተር ደረጃዎች ለ14ወራት እንዲሁም በሩዋንዳ ባለው ፕሮግራም ለ3 ወር ተገኝታቹ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ ከሆናቹ፤

አሁኑኑ በ jasiri.org/application ላይ ይመዝገቡ

ሴት ስራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ በጣም እናበረታታለን!
#ኢሠማኮ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) " ኮንቬንሽን 189፣ 190፣ 97 እና 143 ለተጋላጭ የቤት ሠራተኞች፣ ፍልሰተኞች ሠራተኞች፣ እና በሥራ ቦታ ጥቃት እና ትንኮሳ ሰለባዎች ኑሮ ለሚኖረው አዎንታዊ ለውጥ ይደግፉ!ያግዙ ! ያጽድቁ ! " በሚል መሪ ቃል ኮንቬንሽኖቹ ጸድቀው የአገሪቱ የሕግ አካል እንዲሆኑ እና ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚያስችል የግንዛቤ ፈጠራ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሕግ አውጪዎች ፣የዓለም ሥራ ድርጅት ተወካይ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የአሠሪ ተወካዮች ሚዲያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እንደሚያደርግ አሳውቆናል።

ኢሠማኮ የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለተማሪዎች መውደቅ ማነው ተጠያቂው ? በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦ " ... ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል…
" የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተናን በብዛት #የሚወድቁበትን_ምክንያት ጥናት እንዲጠና ባዘዝኩት መሠረት አጥንተህ አላቀረብክም " ሲል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፤ የትምህርት ሚኒስቴርን ወቀሰ፡፡

በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር መጀመሪያ የትምህርት ሚኒስቴር የሩብ ዓመት አፈጻጸሙንና የዓመቱን ዕቅድ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረበበት ወቅት፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በከፍተኛ ቁጥር ፈተና የመድወቅ ጉዳይ ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል።

የምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴም ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ በብዛት የሚወድቁበትን ምክንያት በሰፊው አስጠንቶ ለም/ቤቱ እንዲያቀርብ ሐሳብ አመንጭቶና አዞት ነበር።

ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ዕለት #የስድስት_ወራት አፈጻጸሙን ባቀረበበት ወቅት፣ " የታዘዘውን ትዕዛዝ አላዘጋጀህም " በሚል በተወካዮች ምክር ቤት አባላት  ተወቅሷል።

በሐሙስ መድረክ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ወራት ስለሰራቸው ስራዎች፣  ስለፈተናዎች ጥያቄ አስተማማኝነት እና መሰል ጉዳዮችን ሲያብራራ ነበር።

የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በመድረኩ ላይ የቀረበው ሪፖርት ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን ጥያቄ የሚመልስ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ኮሚቴያቸው ፤ ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ማዕቀፍ ያለው ሰፊ ጥናት በአንድ ወር እንዲቀርብ መጠየቁን እንዲሁም ይህን በተመለከተ ደብዳቤም እንደተፃፈለት አመልክተዋል።

ደብዳቤው ፤ በ2014 እና በ2015 የታየውን ዝቅተኛ ውጤት በሚመለከት (ከ96% በላይ ተማሪዎች ከ50% በታች ውጤት ማምጣታቸውን በሚመለከት) የዘርፉ ባለሙያዎች የተካተቱበት አጥኚ ቡድን በማቋቋም ፣ የችግሩን ዋነኛ መንስዔና መፍትሔዎችን ሊያመለክት የሚችል ጥናት እንዲቀርብ የሚያዝ እንደሆነ አስረድተዋል።

ነገር ግን በቋሚ ኮሚቴው የታዘዘው ጥናት ተጠንቶ እንዳልቀረበ ፤ ኮሚቴው የተፈለገው ጥናት ከ1 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አሁንም እንዲቀርብለት እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

የከዚህ ቀደም ጥያቄያቸው እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ተናግረዋል፡፡  

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥናቱን በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።

ባለፈው " #ይጠና " በሚባልበት ጊዜ አንዱ ተነስቶ የነበረው የፈተና አሰጣጡና የፈተናው ምንነት ተቀይሮ እንደሆነ መጠየቃቸውንና እነሱም ያደረጉት ፈተናው በእርግጥ ተቀይሮ ከሆነ በገለልተኛ ይጠና ብለው እንዳከናወኑት ገልጸዋል፡፡

በአንድ ወር ውስጥ ተጠናቆ ይቅረብ ለተባለው ጥናት ደግሞ ፤ " የኢትዮጵያን የትምህርት ችግርና እዚህ ደረጃ የደረሰበትን ምክንያት አሁን በተሰጠ 1 ወር በገለልተኛ አካል አጥንቶ ማቅረብ አይቻልም፤ ይህ ይሁን ከተባለም የችኮላ ችኮላ ሥራ ነው  የሚሆነው " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በራሱ ይህ አይነት ውጤት ለምን እየመጣ እንደሆነና ለምንድን 1,328 ትምህርት ቤቶች ፈተና እንዳላሳለፉ በተወሰነ ደረጃ በራሳቸው ለማጥናት እየሞከሩ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ግን ም/ቤቱ አሁንም ከዚህ ሰፋ ያለ በገለልተኛ አካል ይጠና የሚል ከሆነ፣ ፓርላማው እንዲያግዛቸው ገለልተኛ በሆነ አካል የተሻለ ጥናት ቢያስጠኑ እነሱም እንደሚመርጡ ገልጸዋል፡፡  

" በጋራ ብናደርገው ጊዜውን ለመወሰን ይጠቅማል፡፡ እንዲህ ዓይነት ጥናት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ? " የሚለውን ለማወቅ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ነገሪ ፤ ምክር ቤቱ ፈተናው ችግር አለበት እና ፈተናው ይገምገም እንዳላላ፣ እንዲሁም እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ጊዜ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡  

" ይህንን አዳምጠው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ ሊቀርብ ይችል ነበር ጥናቱ። ዛሬ ላይ ባይደርስ እንኳን ግዴታ አይደለም፣ እየተሠራ ነው ሲጠናቀቅ እናቀርባለን ማለት ይቻል ነበር " በማለት ነገሪ (ዶ/ር) መልሰዋል፡፡

አክለውም " የተከበረው ምክር ቤት ሕዝብን ወክሎ ነው ጥያቄ የሚያነሳው፡፡ አስፈጻሚው ደግሞ ሕዝብን የማክበር ግዴታ አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

በ2014ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና  896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 / 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015ቱ ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 / 3.2 በመቶ ብቻ እንደሆኑ ይታወሳል።

https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-19

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
ዕጣው እስካሁን አልደረሰንም ነዉ የምትሉት?
ቀላል ነው!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!
ቀጣዩን እድለኛ ለመሸለም ጓጉተናል ነዉ 'ምንላችሁ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም የቻት ግሩፕ @SafaricomETForum እንዲሁም @SafaricomETCare
24/7 መጠየቅ ይቻላል!

#SafaricomET
#FurtherAheadTogether
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫና የሙያ ፈቃድ ፈተና ከወሰዱት የህክምናና ጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎቹ 99% ተፈታኞች ፈተናውን አልፈው ለመመረቅ ብቁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ተቋሙ ይፋ ባደረገው ዳታ ፤ በ ' ዶክተር ኦፍ ሜዲስን ' ካስፈተናቸው 190 ተመራቂዎች 189 ተመራቂዎች የተሰጣቸውን ፈተና አልፈዋል።

More 👉 @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ አቅርቧል። ኮርፖሬሽኑ ፤ " ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው #የተጠናቀቁ ፦ ➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን ➡️ 306 የንግድ…
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል።

ኮርፖሬሽኑ ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ ፦
➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን
➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ነው በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ የፈለገው።

የዚሁ የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ጨረታ ሰነድ እየተሸጠ ሲሆን #ቀነገደቡ በቀን 20/06/2016 ዓ/ም ያበቃል።

ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ የመኖሪያና የንግድ ቤቶቹን በጨረታ ለሽያጭ ያቀረብኩት ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ነው ብሏል።

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታዎችን በዚህ ሊንክ መመልከት ይቻላል👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/84877

ከመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ጨረታ መውጣት ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉና ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ምንም እንኳን ለሽያጭ የቀረቡት ቤቶች በካፒታል በጀት የተሰሩ ቢሆንም እኛ ለዓመታት ከምንበላው ቀንሰን ስንቆጥብ የቆየን እና ቤት ለማግኘት ተመዝግበን በስንት ተስፋ እየጠበቅን የምንገኝ ነዋሪዎችን ያላማከለ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ቀናት በመንግሥት አማካኝነት የቤቶች ጨረታ ማውጣት ላይ ቅሬታ አለን የሚሉ ወገኖችን እንዲሁም ለቅሬታው በሚመለከተው አካል የሚሰጥ ምላሽ ካለ የሚያቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ከአፖሎ መበደር ከእናት ኪስ እንደመበደር ነው።

አፖሎን በመጠቀም አነስተኛ ብድር ያለምንም ማስያዣ በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ይውሰዱ። መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። 

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628 #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
Addis Ababa University- Cisco Networking Academy,
@CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com

Online Live class - Cisco CCNA Professional Networking Course Training & Certification Preparation.

Registration Date: Feb.12 to March 8, 2024
Class start date: March 9, 2024.

Course Recognitions: CCNA trainees will receive 3 Certificate of Completion, 3 Letter of Merit, 3 Digital Badge that recognized and accepted in USA, Canada, and Europe, and you will award 58% CCNA certification exam discount voucher.

Mobile #: 0902-340070/0935-602563/ 0945-039478/
Office : 011-1-260194

Follow our telegram channel: @CiscoExams