TIKVAH-ETHIOPIA
ለተማሪዎች መውደቅ ማነው ተጠያቂው ? በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦ " ... ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል…
" የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተናን በብዛት #የሚወድቁበትን_ምክንያት ጥናት እንዲጠና ባዘዝኩት መሠረት አጥንተህ አላቀረብክም " ሲል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፤ የትምህርት ሚኒስቴርን ወቀሰ፡፡
በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር መጀመሪያ የትምህርት ሚኒስቴር የሩብ ዓመት አፈጻጸሙንና የዓመቱን ዕቅድ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረበበት ወቅት፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በከፍተኛ ቁጥር ፈተና የመድወቅ ጉዳይ ተነስቶ እንደነበር ይታወሳል።
የምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴም ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ በብዛት የሚወድቁበትን ምክንያት በሰፊው አስጠንቶ ለም/ቤቱ እንዲያቀርብ ሐሳብ አመንጭቶና አዞት ነበር።
ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ዕለት #የስድስት_ወራት አፈጻጸሙን ባቀረበበት ወቅት፣ " የታዘዘውን ትዕዛዝ አላዘጋጀህም " በሚል በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተወቅሷል።
በሐሙስ መድረክ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ወራት ስለሰራቸው ስራዎች፣ ስለፈተናዎች ጥያቄ አስተማማኝነት እና መሰል ጉዳዮችን ሲያብራራ ነበር።
የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በመድረኩ ላይ የቀረበው ሪፖርት ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን ጥያቄ የሚመልስ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
ኮሚቴያቸው ፤ ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ማዕቀፍ ያለው ሰፊ ጥናት በአንድ ወር እንዲቀርብ መጠየቁን እንዲሁም ይህን በተመለከተ ደብዳቤም እንደተፃፈለት አመልክተዋል።
ደብዳቤው ፤ በ2014 እና በ2015 የታየውን ዝቅተኛ ውጤት በሚመለከት (ከ96% በላይ ተማሪዎች ከ50% በታች ውጤት ማምጣታቸውን በሚመለከት) የዘርፉ ባለሙያዎች የተካተቱበት አጥኚ ቡድን በማቋቋም ፣ የችግሩን ዋነኛ መንስዔና መፍትሔዎችን ሊያመለክት የሚችል ጥናት እንዲቀርብ የሚያዝ እንደሆነ አስረድተዋል።
ነገር ግን በቋሚ ኮሚቴው የታዘዘው ጥናት ተጠንቶ እንዳልቀረበ ፤ ኮሚቴው የተፈለገው ጥናት ከ1 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አሁንም እንዲቀርብለት እንደሚፈልግ ገልጸዋል።
የከዚህ ቀደም ጥያቄያቸው እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥናቱን በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።
ባለፈው " #ይጠና " በሚባልበት ጊዜ አንዱ ተነስቶ የነበረው የፈተና አሰጣጡና የፈተናው ምንነት ተቀይሮ እንደሆነ መጠየቃቸውንና እነሱም ያደረጉት ፈተናው በእርግጥ ተቀይሮ ከሆነ በገለልተኛ ይጠና ብለው እንዳከናወኑት ገልጸዋል፡፡
በአንድ ወር ውስጥ ተጠናቆ ይቅረብ ለተባለው ጥናት ደግሞ ፤ " የኢትዮጵያን የትምህርት ችግርና እዚህ ደረጃ የደረሰበትን ምክንያት አሁን በተሰጠ 1 ወር በገለልተኛ አካል አጥንቶ ማቅረብ አይቻልም፤ ይህ ይሁን ከተባለም የችኮላ ችኮላ ሥራ ነው የሚሆነው " ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በራሱ ይህ አይነት ውጤት ለምን እየመጣ እንደሆነና ለምንድን 1,328 ትምህርት ቤቶች ፈተና እንዳላሳለፉ በተወሰነ ደረጃ በራሳቸው ለማጥናት እየሞከሩ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ግን ም/ቤቱ አሁንም ከዚህ ሰፋ ያለ በገለልተኛ አካል ይጠና የሚል ከሆነ፣ ፓርላማው እንዲያግዛቸው ገለልተኛ በሆነ አካል የተሻለ ጥናት ቢያስጠኑ እነሱም እንደሚመርጡ ገልጸዋል፡፡
" በጋራ ብናደርገው ጊዜውን ለመወሰን ይጠቅማል፡፡ እንዲህ ዓይነት ጥናት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል ? " የሚለውን ለማወቅ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ነገሪ ፤ ምክር ቤቱ ፈተናው ችግር አለበት እና ፈተናው ይገምገም እንዳላላ፣ እንዲሁም እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ጊዜ ተሰጥቷቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
" ይህንን አዳምጠው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ ሊቀርብ ይችል ነበር ጥናቱ። ዛሬ ላይ ባይደርስ እንኳን ግዴታ አይደለም፣ እየተሠራ ነው ሲጠናቀቅ እናቀርባለን ማለት ይቻል ነበር " በማለት ነገሪ (ዶ/ር) መልሰዋል፡፡
አክለውም " የተከበረው ምክር ቤት ሕዝብን ወክሎ ነው ጥያቄ የሚያነሳው፡፡ አስፈጻሚው ደግሞ ሕዝብን የማክበር ግዴታ አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
በ2014ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 / 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015ቱ ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 / 3.2 በመቶ ብቻ እንደሆኑ ይታወሳል።
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-19
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia