TIKVAH-ETHIOPIA
" የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም " - መንግሥት 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ " ወደ ስብሰባው እንዳልገባ የመከልከል ሙከራ ተደርጎብኛል " የሚል ክስ አሰምተዋል። ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ከስብሰባው…
#ኢትዮጵያ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም መግለጫቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ትላንት አዲስ አበባ ሆነው ስለሰጡት መግለጫ ምላሽ ሰጥተዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሰጡት መግለጫ ፤ " ካረፍኩበት ሆቴል እንዳልወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መንገድ ዘጉብኝ ፤ በኃላም ከሌላ ፕሬዜዳንት ጋር (ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢሳማኤል ኦማር ጌሌህ) ጋር ሆነን ወደ ጉባኤው ልንገባ ስንል የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ክልከላ አደረጉብን " የሚል ክስ አሰምተው ነበር።
የሶማልያው ፕሬዜዳንት ለሰጡት መግለጫ አምባሳደር መለስ አለም (ዶ/ር) ምን ምላሽ ሰጡ ?
" እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታቸው ደኅንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት አለባት።
ይሁን እንጂ የሶማሊያ ፕሬዚዳት በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም።
ይህ አሠራር (የአዘጋጅ ሀገር የእንግዶችን ደህንነት ማስጠበቅ) በመላው ዓለም የተለመደ ነው። በሶማሊያ ልዑክ በኩል የሆነው ከዚህ በተቃራኒ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታት መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንትም አድርጓል።
ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደኅንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት ተከልክለዋል።
ይህም የሕብረቱን የፀጥታ አካላት የሚመለከት እንጂ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም።
የኢትዮጵያ መንግስትም ከሕብረቱ ቅጥር ግቢ ደሕነታቸውን ከማስጠበቅ ውጭ በሕብረቱ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡም የመከልከል ኃላፊነት የለውም።
በሶማሊያ በኩል የተሰጠው መግለጫ በሌሎች የሕብረቱ ተሳታፊ ሀገራት መሪዎች ጭምር ተቀባይነት ያለገኘ እና የተሳሳተ ነው። " #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopia

#AU #ETHIOPIA
ትላንትና ምሽት ላይ ለ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመጡ መሪዎች በብሄራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር።
ዛሬ የጠ/ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባሰራጫቸው ምስሎች የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ፣ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በእራት ግብዣው ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የጎረቤት ሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ አልታዩም።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ትላንት እዚሁ አ/አ ሆነው በሰጡት መግለጫ " የኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች ከሆቴል እንዳልወጣ እንዲሁም ከጅቡቲ ፕሬዜዳንት ጋር ሆነን ወደ ጉባኤው እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብናል " የሚል ክስ አሰምተው ነበር።
በትላንት ምሽቱ የብሔራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ላይ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ ከሌሎች ፕሬዜዳንቶች ጋር በመሆን ከፊት መስመር ከፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጎን ተቀምጠው ታይተዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ግን በስፍራው አልታዩም።
ዛሬ እሁድ " አናዱሉ " የዜና ወኪል ባሰራጨው መረጃ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቀውን የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ አቋርጠው ወደ ሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

ይቆጥቡ፤ ይጓዙ!
ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ
==============
ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉዞ ወጪ መሸፈኛ ገንዘብ አስቀድመው መቆጠብ እንዲችሉ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡
ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ ከብር 1,000 ጀምሮ ይከፈታል፡፡
የቁጠባ ሂሳቡ የተለያዩ ጥቅሞች ያስገኛል፡፡
• ቆጣቢዎች በሀገር ወስጥ ጉዟቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ለአየር ትኬት፣ ለቱሪስት መዳረሻዎች መግቢያ፣ ለሆቴል አገልግሎት እና ለመሳሰሉት ክፍያ በሚፈፅሙበት ወቅት ተመላሽ ያገኛሉ፤
• ዳያስፖራ ወይም የውጭ ሀገር ዜጎች የሲቢኢ ቱሪስት ካርድን ሲጠቀሙ እስከ 7 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ ፤
• ለሀይማኖታዊ ጉዳይ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ደንበኞች ከአየር ትኬት ክፍያቸው እስከ 3 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ፤
• ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችንም ያስገኛል፡፡
ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!

" የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣንም ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገው ሌላው የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል ! " - ነዋሪዎች (ከሰሞኑን በሚዛን አማን በነበረ ህዝባዊ ውይይት ላይ የተነሳ) #ቲክቫህኢትዮጵያ @tikvahethiopia
" የሀብታም ልጅ #በገንዘቡ የባለስልጣን ልጅ #በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገዉ ሌላዉን የድሀ ልጅ ከስራ ውጭ አድርጎታል " - ነዋሪዎች
ሰሞኑን በሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።
ይኸው ውይይት በደቡብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደና በቤኒሻንጉል ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የተመራ ነበር።
በህዝብ ወይይቱ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ከነዚህ መካከል ፦
➡ እንደካሮት ቁልቁል የሚሄደዉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ለምን ባለቤት አጣ ? ተመዘበረበት የተባለዉን ገንዘብ ጉዳይ የያዘዉ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወዴት አደረሰው ?
➡ ያለብን የመንገድ ችግር አሁንም እናቶች በህክምና እጦት #ለሞት እየዳረገ ነው። መፍትሄ ለምን አይሰጥም ? የሚሉት ይገኙበታል።
ሌላው የተስፋፋዉ የሙስና ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የሀብታም ልጅ በገንዘቡ ፤ የባለስልጣን ልጅ በስልጣኑ ስራ እንዲቀጠር ሲያደርገዉ ሌላዉን የድሀ ልጅ ከስራ ዉጭ አድርጎታል ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ አሰምተዋል።
ተሳታፊዎቹ መንግስት ቁርጠኛ አመራር በመስጠት ስርአቱን ሊያስተካክለዉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በእለቱ መድረኩን የመሩት የደቡብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ፤ ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመንግሥት በኩል ቀይ መስመር በማለት ያስቀመጠዉ ጉዳይ ነው " ሲሉ ገልጸው ችግሩን በመቅረፉ ሂደት ህዝቡ ከመንግስት ጎን ሊቆምና ሊታገል ይገባል ብለዋል።
መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

ቪድዮ ፦ በጀርመን ፤ #ስቱትጋርት ከተማ ቅዳሜ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሁከቱ የተፈጠረው የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በከተማዋ የባሕል ፌስቲቫል ማዘጋጀታቸውን ተከትሎ ተቃዋሚዎች ሥነ-ስርዓቱን ለማወክ ሁከት ከፈጠሩ በኋላ ነው። ተቃዋሚዎቹ በጀርመን ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት አድርሰው በአጠቃላይ 26 የፖሊስ አባላት የተጎዱ…
ቪድዮ ፦ በትላንትናው ዕለት በኔዘርላንድስ ፤ ሄግ ከተማ የኤርትራን መንግሥት በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ኤርትራውያን ቡድኖች መካከል በተከሰተ ግጭት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል።
የኔዘርላንድስ ፖሊስ ግጭቱን ለመቆጣጠር ሲል አስለቃሽ ጋዝ ለመጠቀም ተገዷል። የኔዘርላንድ ፖሊስ መኪኖችም መቃጠላቸው ተነግሯል።
የአይን እማኞች ግጭቱ በተካሄደበት ስፍራ በርካታ ሰዎች በጎዳና ላይ እንደነበሩ ፤ አንዳንዶች ድንጋይ ሲወረውሩ እንደነበር ፤ በእሳት የተያያዙ መኪኖችም መመልከታቸውን ታናግረዋል።
በግጭቱ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም።
የሄግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ግጭቱ የተከሰተው የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች ስብሰባ እያካሄዱ ሳለ ተቃዋሚዎች ወደ ስብሰባው ስፍራ በመሄድ ጥቃት በመፈጸማቸው ነው።
ሁኔታው አሳሳቢ ሆኖ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን የገለፀው ማዘጋጃ ቤቱ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል።
መሰል ግጭት ከዚህ ቀደምም በኤርትራውያን መካከል አውሮፓ ውስጥ መከሰቱ የሚዘነጋ አይደለም።
መረጃው የትግርኛው የቢቢሲ ክፍልና የኤፒ ነው።
ቪድዮው ፦ ከኔዘርላንድስ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተወሰደ ነው።

#AU #ETHIOPIA ትላንትና ምሽት ላይ ለ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመጡ መሪዎች በብሄራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር። ዛሬ የጠ/ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባሰራጫቸው ምስሎች የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ፣ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በእራት ግብዣው ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የጎረቤት ሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን…
#Update #ተጠናቋል
የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት #መጠናቀቁን ኢትዮጵያ አስታውቃለች።
የሁሉም ሀገራት መሪዎች እና የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ከዚህ ቀደም ከነበረው በደመቀ ሁኔታ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ክብርን እና ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ አቀባበል እንደተደረገላቸው ፤ በአዲስ አበባ ቆይታቸውም በልዩ እንክብካቤ እንደተያዙ በኢትዮጵያ መንግሥት ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ለዚህ ጉባኤ ስኬት ላለፉት 6 ወራት ስትዘጋጅ መቆየቷን የተገለጸ ሲሆን በተለይም ከሰላምና ደህንነት አንፃር በርካታ ባለድርሻ አካላት ሲሳተፉ መቆየታቸውን ተጠቁሟል።
በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች ተሰማርተው እንደነበረም ተመላክቷል።
ለጉባኤው ስኬታማነት በተለይ በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ ከቅድመ ጉባኤው ዝግጅት አንስቶ ስብሰባው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የትራፊክ፣ የመንገድ መዘጋጋት እና ሌሎች ጉዳዮችንም ታግሶ ፤ ከፀጥታ ኃይሉም ጋር በመተባበር እንግዶች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲስተናገዱ ልዩ የእግዳ አቀባበል በማድረጉ መንግሥት ምስጋና አቅርቧል።
በተጨማሪ የፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች ፣ የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች፣ የፕሮቶኮል ሰዎች፣ ሆቴሎች ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን .. ሌሎችም አስተዋፅኦ ያደረጉ ሁሉ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።