TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ለጉምሩክ ሰራተኞች ' ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቃለሁ ' በሚል 1 ሚሊዮን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ ትራንዚተር እጅ ከፍንጅ ተይዟል " - ፌዴራል ፖሊስ

" ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " ብሎ ከባለ ጉዳይ የ1 ሚሊየን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ አንድ ትራንዚተር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

" ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " ብሎ ከባለ ጉዳይ የ1 ሚሊየን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ አንድ #አስተላላፊ (ትራንዚተር) ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከነ-ኤግዚቢቱ በአዲስ አበበ ከተማ አቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ትራንዚተሩ የተያዘው " #ለጉምሩከ_ሠራተኞች ጉቦ ሰጥቼ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተያዙ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " በማለት ጉቦ እንደሚሰጥ አስመስሎና አታሎ ከባለጉዳይ የ1 ሚልየን ብር ቼክ ሲቀበል የኢትዮጵያ ፌዳራል ፓሊስ ወንጃል ምርመራ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አባላት ጋር በመሆን ባደረጉት ክትትል እጅ ከፈንጅ ከነ-ቼኩ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ሊውሉ ችለዋል።

ኅብረተሰቡ በመሠል ግለሰቦች እንዳይታለል ጥንቃቄ እንዲያደርግና በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችንም ሲያገኝ ጥቆማ እንዲሰጥ የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳወቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫው በምን ጉዳይ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ባይገለፅም #በወቅታዊ_ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነ ተነግሯል። ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ለሚሰጠው መግለጫ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ላልሆኑና በቤተክርስቲያኗ…
#EOTC

ዛሬ ቋሚ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሠጥቶ ነበር።

በዚህም መግለጫ ፤ በአርሲ ዞን ሹርካ ወረዳ ስለተፈፀመው የበርካታ ምዕመናን ግድያ ፣ በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት የቋቋም መምህር የሆኑት የመምህር ፍሥሃ አለምነው ባልታወቁ አካላት የተፈፀመው ግድያ ተነስቷል።

በተጨማሪ፤ በወለጋ፣ በጎንደር፣ በጎጃም ፣ በወሎ ፣ በሰሜን ሸዋ በመሳሰሉት እየተፈፀመ ስላለው የመጠፋፋት፣ የሃይማኖት ጥላቻ፣ የንፁሃን መቀጠፍ ድርጊት ተነስቷል።

ቋሚ ሲኖዶስ ግድያ፣ ስደት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል የዕለት ዜናችን ከሆነ ሰንብቷል ብሏል። 

ይኽ እንዳለ ሆኖ ረሀብ፣ ድርቅ፣ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነት በተጨማሪ በየቦታው በተፈጠሩ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች ምክንያት በርካቶች ቀያቸውን ለቀው፣ መነኰሳት ገዳማትን ትተው ተሰደዋል፤ ወላድ እናቶች፣ ሕሙማንና አረጋውያን በሕክምና እጦት እያለቁ ነው፣ ሕፃናትና ወጣቶች ከጤናማ እድገትና ከትምህርት ገበታ ተደናቅፈዋል ብሏል።

በመሆኑም ፦

- ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ከግጭትና ከጦርነት፣ ከርስ በርስ መገዳደል ወጥተው በውይይትና በምክክር፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት ስሜት የታላቋን ሀገር መልካም ስምና ክብር እንዲሁም የዜጎቿን ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ተግባር ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳስቧል። 

- በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንፁሐን ምእመናንና ተቋማት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች  በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ መንግሥትና የሚመለከታቸው ሁሉ ዋስትና እንዲሰጡ፣ ወንጀል ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ድርጊቱንም መላው ዓለም እንዲያወግዘው ጠይቋል።

- የሀገርና የዓለም ሀብት የሆኑ ቅዱሳን መካናት፣ እንደ ፦
° ዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣
° ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም፣
° አሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም እና አካባቢው፣
° ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳምና አካባቢው የመሳሰሉ ሁሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት አደጋ የተጋረጠባቸው በመሆኑ ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ቋሚ ሲኖዶስ አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Grap. Tikvah Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ታዬ ከሰሞኑን ምን ሲሉ ነበር ? ዛሬ ታህሳስ 1/2016 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ባረፈበት ደብዳቤ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታነት መነሳታቸው የተገለፀላቸው አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን አነጋጋሪ ቃለ ምልልሶችን ሲሰጡ ነበር። ለአብነት ፦ ▪️የቲክቫህ - ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባልን ጨምሮ ፤ ለተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች በአዳማ በነበረ አንድ ፕሮግራም በሰጡት ቃለ ምልልስ ተከታዮቹን…
አቶ ታዬ #በሕግ የሚያስጠይቃቸው ጉዳይ ይኖር ይሆን ?

" በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው፤ ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ " - አቶ ታዬ ደንደአ

አቶ ታዬ ደንደአ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታነት መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ከደረሳቸው እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጠንካራ ትችት ከሰነዘሩ በኃላ ማምሻውን ለ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አቶ ታዬ ደንደአ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሥልጣን የተሰናበቱት በአገሪቱ ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ በማቅረባቸው እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል።

" ስለእርቅ ስለተናገርኩ ጦርነት ይቁም ስላልኩ እንጂ ሌላ ምክንያት የለም " ያሉት አቶ ታዬ፣ " በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ፣ ሲያበረታቱኝ ነበር። ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው። ጠርተው አላናገሩኝም። በአካል አልተገናኘንም " ሲሉ ተናግረዋል።

ስንብታቸውን በተመለከተ #በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩትን ጠንካራ ቃላትን የተጠቀሙት ትችትን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ታዬ ደንደአ ፤ " ይሄ እውነት ነው። ለሰው አያዝኑም። የሰው ልጅ ሞቶ አውሬ እየበላው ስለ ፓርክ ያወራሉ። ሰው የሚበላው አጥቶ እየሞተ በብዙ ገንዘብ ቤተ መንግሥት ያስገነባሉ " በማለት ወቅሰዋል።

በማህበራዊ ገፃቸው በፃፉት ትችት በሕግ ሊያስጠይቃቸው የሚችል ነገር ይኖር እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ታዬ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ፤ ነገር ግን ይህ የሚሆንበት ዕድል እንደሌለ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

" በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው ታዲያ። ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ። " ብለዋል።

የመንግሥትና የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነው በጠንካራ ትችታቸው የሚታወቁት አቶ ታዬ ሰሞኑን በተከታታይ የሰነዘሯቸው አስተያያቶች ለስንብታቸው ምክንያት ይሆናል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ፤ " ከዚህ ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም። ከፓርቲያችን መርሆች ውስጥ ነጻነት አንዱ ነው። ከዚህ መርህ በተቃራኒ መቆም ተገቢ አይደለም። እኔ ስናገር የነበረው ይህንን መርህ መሠረት በማድረግ ነው " ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሆነ ሰላም ሚኒስቴር እስካሁን ስለጉዳዩ ያሉት ነገር የለም። ነገር ግን አቶ ታዬ ከስልጣን መሰናበታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አትሌት ለተሰንበት ግደይ አሸናፊ ሆነች። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አትሌቲክስ ኢንተርናሽናል ፌርፕሌይ (ስፖርታዊ ጨዋነት) ሽልማት አሸናፊ ሆናለች። አትሌቷ የሽልማቱ አሸናፊ የሆነችው በቡዳፔሽቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ከትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር በነበራት ቅፅበት መሆኑ ተገልጿል። አትሌት ሲፋን በውድድሩ ላይ መውደቋን ተከትሎ አትሌት ለተሰንበት…
#TigistAssefa👏

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ከስቴዲየም ውጭ ባሉ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባሳየችው ድንቅ የሆነ ብቃት የዓመቱ ምርጥ አትሌት መባሏን የዓለም አትሌቲክስ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጓል።

አትሌት ትዕግስት የሴቶች ማራቶንን ከሁለት ደቂቃ በላይ በማሻሻል (2:11:53 በመግባት) የዓለም ክብረወሰን ባለቤት እንደሆነች ይታወቃል።

ከቀናት በፊት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ኢንተርናሽናል ፌርፕለይ (በስፖርታዊ ጨዋነት) ማሸነፏ የሚታወስ ነው።

More - @tikvahethsport

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

2ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ታህሳስ 4 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

ሊንክ፡ https://t.iss.one/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ታዬ ደንደአ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ  ታዬ ደንደአ በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፀጥታ እና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update

የአቶ ታዬ ደንአደን በቁጥጥር ስር መዋል በተመለከተ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ምን አለ ?

ግብረ ኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአ፥ ከለውጡ በፊት የኦነግ አባል የነበሩና በእስር ቤት የቆዩ መሆኑን ገልጿል።

የለውጡ መንግስት ባደረገላቸው ምህረት ከማረሚያ ቤት ተለቀው በተሰጣቸው እድል በተለያዩ የክልል እና የፌደራል መንግስት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲሰሩ ነበር ብሏል።

ይሁን እንጂ አቶ ታዬ ከህዝብና የመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተለይም ደግሞ የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ሆነው ሰላምን ለማስፈን መሥራት ሲገባቸው በተቃራኒዉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረሰላም ኃይሎች ጋር በመተሳሰር ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ እንደተደረሰባቸው ገልጿል።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ #ከእገታ_ጋር በተያያዘ እጃቸው እንደአለበት ተደርሶበታል ብሏል።

አቶ ታዬ ደንደአ፤ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚችሉ ሲገምቱ ታጋይ ለመምሰል በራሳቸውና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች አፍራሽና ፀረ ሰላም ፅሁፎችን፣ ንግግሮችንና መግላጫዎችን በማን አለብኝነት ሲያስተላልፉና ሲሰጡ ቢቆዩም ከተጠያቂነት ማምለጥ ባለመቻላቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል።

ግብረኃይሉ አቶ ታዬ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን ተቀብለው እየሰሩ በነበረበት ወቅት መንግስታዊና የፓርቲ መዋቅሩን በሴራ ለመናድ በህቡእ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውና ጥናትና ክትትል ሲደረግበት እንደነበር አመልክቷል።

በተደረገው ክትትልም አቶ ታዬ " ከኦነግ ሸኔ " አመራሮችና በሽብር ወንጀል ከተጠረጠሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር ትስስር በመፍጠር መንግስትን በአመጽ፣ በሽብርና፣ በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲያሴሩ እንደ ተደረሰበት ገልጿል።

ተጠርጣሪ ታዬ በህግ ቁጥጥር ሥር ሲውሉ በመኖሪያ ቤታቸው ዉስጥ በተደረገ ፍተሻ ፦
* በህቡዕ ለሚያደርጓቸው ፀረ-ሰላም እንቅስቃሴ ሲገለገልባቸዉ የነበሩ የተለያዩ 9 ሞባይሎች፣
* 4 ላፕቶፖች፣ 3 አይፖዶች፣ በርካታ ፍላሾች፣
* 4 የተለያዩ ተሸከርካሪ ሰሌዳዎች
* ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣
* ክላሽንኮቭ ጠመንጃና ሽጉጦች ከመሰል ጥይቶች ጋር
* የኦነግ ሸኔ አርማዎችና በተለያዩ ግለሰቦች ስም የተዘጋጁ የኦነግ ሸኔ መታወቂያዎች፣ ሰነዶችና ማስታወሻዎች ተገኝተዋል ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በብርበራ ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በ3 መታወቂያዎች የሚጠቀም አንድ " የኦነግ ሸኔ " አባል ተደብቆ መገኘቱንና በቁጥጥር ሥር መዋሉንም ገልጿል።

ግብረኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአ በተመደቡባቸው ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ሆነው በተደጋጋሚ መንግስትን #ገዳይ እና #ጨፍጫፊ እያሉ ሲወቅሱ የሚደመጥ ቢሆንም፤ በተግባር ግን ከሽብርተኞች፣ ጽንፈኛችና ነፍሰ ገዳዮች ጋር የጥፋት ትስስር የነበራቸው ራሳቸው መሆኑ በተደረገ ክትትል ተረጋግጧል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TayeDendea

አቶ ታዬ ደንደአ ትላንት በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ የስንብት ደብዳቤ አያይዘው ከለጠፉ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጠንካራ ቃላትን ተጠቅመው ትችት ከሰነዘሩ በኃላ #በሕግ_ሊያስጠይቃቸው የሚችል ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ተጠይቀው ነበር።

አቶ ታዬ ፤ " በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው ፣ ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

በሕግ ሊጠየቁ የሚችልበት እድልም እንደሌለ ተናግረው ነበር።

ዛሬ የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረኃይል አቶ ታዬን ደንደአን በሕግ ቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው ላይም ብርበራ አድርጓል።

ግብረ ኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአን ፦

- በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ #ከእገታ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት አሳውቋል።

(አቶ ታዬ ደንደአ በ #ሰላም_ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው በተለያዩ ጊዜ በሚፈፀሙ የእግታ ጉዳዮች እጃቸው እንዳለበት የታወቀው መቼ ነው ? ከዚህ ቀደም ታውቆ ከሆነ ለምን እስከዛሬ ዝም ተባሉ ለሚለው ጉዳይ የተብራራ ነገር የለም)

- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰላምን ለማስፈን ከመስራት ይልቅ ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ተሳስረው ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግስት እና የፓርቲ መዋቅሩን በሴራ ለመናድ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግሥት በሽብርተኝነት ከፈረጀው ከኦነግ ሸኔ አመራሮች እና በሽብር ወንጀል ከሚጠረጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ትስስር ፈጥረው መንግስትን በአመፅ፣ በሽብርና በትጥቅ ለመጣል ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን እና በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ትላንት ታሕሳስ 1 በኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተፃፈ ደብዳቤ ከስልጣን እንዲነሱ ተደርገዋል።

አቶ ታዬ ከስልጣን ለመነሳታቸው ምክንያቱ ጦርነት ተቃውመው ስለእርቅ ስለተናገሩ እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል። " በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ ሲያበረታቱኝ ነበር ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው " ያሉት አቶ ታዬ ሰላምን በመደገፌ ነው ከስልጣን የተነሳሁት ብለዋል።

ግብረ ኃይሉ ግን አቶ ታዬ ስልጣን ላይ ቁጭ ብለው እራሳቸው ያሉበትን #መንግስት እና #ፓርቲ ለመናድ መንግስትንም በሽብር ትጥቅ ለመጣል ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ሲሰሩ እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

ልክ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ሲያውቁ ደግሞ #ታጋይ ለመምሰል በየማህበራዊ ትስስር ገፆች ፀረ-ሰላም ፅሁፎችን እና ንግግሮችን ሲያስተላልፉ ነበር ብሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የክፍያ መንገዶች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በሚያስተዳድራቸውን የአዲስ አበባ - አዳማ፣ የድሬዳዋ - ዳዋሌ እና የሞጆ - ባቱ የክፍያ መንገድ ከታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የታሪፍ ጭማሪ አድርጓል፡፡

ኢንተርፕራይዙ ባለፉት 9 ዓመታት ለ2 ጊዜ ያህል ብቻ ነው የታሪፍ ጭማሪ / ማሻሻያ የተገበረው።

የመጀመሪያው በመጋቢት 2011 ዓ.ም በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ላይ የተተገበረ ነው።

በኮቪድ ወረርሽኝ እና ሃገራዊ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ለ4 አመታት የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ ሳይደረግ ቆይቶ በህዳር 2015 ዓ.ም. የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ መተግበሩን አመልክቷል።

የአሁኑ የታሪፍ ጭማሪ ለምን ተደረገ ?

1ኛ. የስራ ማስኬጃና መደበኛ ጥገና ወጪዎች የዋጋ ግሽበትን በመቋቋም ተቋማዊ የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ፤

2ኛ. ለወቅታዊ ጥገና (Periodic Maintenance) መጠባበቂያ ፈንድ ዓመታዊ ተቀማጭን በማረጋገጥ የክፍያ መንገዶችን የአገልግሎት ደረጃ ለማስጠበቅ፤

3ኛ. ምክንያታዊ ትርፍ በማስመዝገብ የመንግስት የትርፍ ድርሻ አስተዋጽዖን ለመወጣት የሚያበቃ የፋይናንስ አቋምን ለማረጋገጥ ዓመታዊ የክፍያ መንገዶች የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ተመን መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብሏል።

የአዲስ-አዳማ እና የሞጆ-ባቱ የፍጥነት መንገዶች የአገልግሎት ደረጃቸው በፍጥነት መንገድ ደረጃ ያሉ እና ተመጋጋቢ የክፍያ መንገዶች በመሆናቸው በአንድ ዓይነት የታሪፍ ተመን የሚተዳደሩ ሲሆን በዚህም ለአዲስ-አዳማ እና የሞጆ-ባቱ የፍጥነት መንገዶች በተመሳሳይ 31% የታሪፍ ዕድገት እንዲኖረው ተደርጓል።

ለድሬደዋ - ዳዋሌ የክፍያ መንገድ ደግሞ 42% የታሪፍ ዕድገት እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

በድሬዳዋ - ደዋሌ የክፍያ መንገድ " ባለሶስት እግር " ተሸከርካሪ ይከፍሉ የነበረው ታሪፍ ብር 10 ተቋማዊ ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንጻር ታይቶ ማህበረሰቡ ለተጋነነ ትራንስፖርት ወጪ ጫና እንዳይዳረግ በሚል የአገልግሎት ክፍያ ታሪፉ በልዩ ሁኔታ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።

(የተደረገው የታሪፍ ጭማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia