TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* በውጭ ምንዛሪ እጥረት ስራውን ያቆመው ማምረቻ !

የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ምርት ማቆሙን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ከ20 ዓመታት በላይ ቆርኪና ጣሳ በማምረት የሚታወቀው ይህ ፋብሪካ፣ በጣሳ ምርት ላይ የተሰማሩ 33 ሠራተኞችን ከ2016 ዓ/ም እና ከ2017 ዓ/ም በሚቀነስ የዕረፍት ጊዜ እንዲወስዱ ተደርጎ በቤታቸው እንዲቆዩ መደረጋቸውም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ይደነቅ እልፍነው ምን አሉ ?

* ፋብሪካው ለተወሰነ ጊዜ ነው ሥራ ያቆመው።

* ስራ ያቆመው በውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው።

ሰራተኞች ምን አሉ ?

- ፋብሪካው ሥራውን ሙሉ ለሙሉ አቁሟል። ሠራተኞችንም እየበተነ ነው።

- በፋብሪካው የቆርኪ ምርት ላይ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 15 ሠራተኞች የአገልግሎት ክፍያ ተሰጥቷቸው ተሰናብተዋል።

- የቀጣይ የሥራ ዕጣ ፈንታችን ምን እንደሚሆን ማወቅ አልቻልንም። ግራ ተጋብተናል።

- የቆርኪና የጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ወደ ግለሰብ ከዞረ ጊዜ ጀምሮ የተሻለ ምርት እያመረተ አልነበረም፤ ሠራተኞችንም ቀስ በቀስ ከሥራ ገበታቸው እንዲወጡ ተደርጓል።

- የቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በመንግሥት ሥር እያለ ከ140 በላይ ሠራተኞች ነበሩ።

- የጊዜ ገደብ ሳይሰጠን ነው ከሥራ የተሰናበትነው።

- ጉዳዩን ወደ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሽን (ኢሠማኮ) ለመውሰድ ቀነ ቀጠሮ ይዘናል።

- ከ15 ሠራተኞች ውስጥ ሁለት የሚሆኑት እስካሁን ድረስ የአገልግሎት ክፍያ አልተሰጣቸውም።

- ከዚህ በፊት በመንግሥት ሥር እያለ የተሻለ ምርት በማምረት፦
* ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣
* ለሐበሻ ቢራ፣
* ለሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪና ለሌሎች ድርቶች ምርቶቹን ሲያከፋፍል ነበር።

- በመጀመሪያ አንድ ድርጅት ከስሪያለሁ ካለ ቅድሚያ በመንግሥት ኦዲት እንዲሠራ ከተደረገ በኋላ የ3 ወራት ጊዜ በመስጠት ማባረር አለበት።

- በወቅቱ የኢንዱስትሪው ባለቤት የሆነው ግለሰብ በ2 ቀናት ልዩነት ውስጥ ሠራተኞችን በመጥራት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ኪሳራ ስለደረሰብኝ የቆርኪ ሠራተኞች ልበትን ነው ያለው።

- በድርጅቱ በበርታ ኤጀንሲ ሥር ሆነው የተቀጠሩ 9 ሴት ሠራተኞች የ1 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው ሲሆን " ለምን አትከፍሉንም? " የሚለው ጥያቄ ሲያቀርብ " ኤጀንሲው ይክፈላችሁ " የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን። 

ከዚህ በፊት የቆርኪ ማምረቻ በፈረቃ 700,000 ቆርኪዎች የማምረት አቅም ኖሮት ከጀመረ በኋላ፣ በሒደት 1.4 ሚሊዮን ቆርኪ የማምረት አቅም ከፍ እንዲል ተደርጎ ሲያመርት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

መንግሥት በኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር ላይ የነበረውን የ75 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በ130 ሚሊዮን ብር በመሸጥ ሙሉ በሙሉ ይዞታውን ለኩባንያ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

" ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ ህክምና የምንገለገልባቸው አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው " - አቤኔዘር እጸድንግል (ዶ/ር)

የአምቡላንሶች ቁጥር በጦርነቱ ወቅት መመናመንና፣ ደመወዝ ያልተከፈላቸው የጤና ባለሙያዎች ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ፈተና እንደሆነበት የትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የጤና ቢሮው የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤኔዘር እጸድንግል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

- የድንገተኛ ሕክምና ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ችግር ነበር። ከሁሉ በላይ ደግሞ የወላድ እናቶች በቂ አገልግሎት ሲሰጥ አልነበረም። ዋነኛው፣ አንደኛውና ቀደኛ ምክንያቱ የአምቡላንስ እጥረት ችግር ነው። ያለ አምቡላንሶች ድንገተኛ ሕክምና የለም።

- ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድገተኛ ሕክምና የምንገለገልባቸው፤ አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው። በጣም ጥቂት አምቡላንሶች ናቸው የቀሩን።

- በአስተዳደራዊ፣ በነዳጂ፣ በበጀት ችግሮችና በተለያዩ ምክንያቶች 90ዎቹ አምቡላንሶችም ራሱ ለሁሉም አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

- ኅብረተሰቡ ሊያገኝ የሚገባው አገልግሎት እጅግ በጣም ቀንሶ ነው ያለው። ከዚህ በፊት በአንድ ጊዜ  በኳርተር ኦልሞስት እስከ #500,000 የሚጠጉ ድገተኛ ታካሚዎች ናቸው የነበሩን፤ አሁን በተመሳሳይ ወቅት ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመጡት ድንገተኞች #40,000ም አይሞሉም። በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ታካሚው ቀንሷል።

- የጤና ባለሙያዎችም ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት ላይ ፈተና ሆኗል።

- የጤና ባለሞያዎቹ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሲሉ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ማለትም ወደ መሀል አገር ይሰደዳሉ ፤ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ #በጀት ስለሌለ #በቂ ደመወዝ ስለማያገኙ ነው።

* ይህ ሁሉ ተደማምሮ የአገልግሎት ጥራት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ አድርጓል። ለቀጣይ ይሻሻላል፣ ለመሻሻልም ጊዜያዊው መግሥትም ብዙ እየሰራ ነው።

የአምቡላንሶቹ ቁጥር የቀነሰው በጦርነቱ ወቅት ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቤኔዘር (ዶ/ር) ፦

" አዎ በጦርነቱ ወቅት በርከት ያሉ አምቡላንሶች ተወስድልውብናል። በርከት ያሉ ደግሞ ተቃጥለዋል። በእኛ እጅ ያሉት 90 ብቻ ናቸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት ከ80 በላይ የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎች ላይ ደረሰ የተባለውን ውድመት ተከትሎ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ የተሻለ ቢሆንም የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈተኝ ችግሮች ማጋጠማቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

መረጃው አዘጋጅቶ ያቀረበው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
* Gede'uffa

በገደብ ከተማ የጌደኡፋ (Gede'uffa) ቋንቋን ያልተጠቀሙ የተለያዩ የአገልግሎት ማስታወቂያዎችን የማንሳት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

በጌደኦ ዞን ዉስጥ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የጌደኡፋን (Gede'uffa) ቋንቋ የስራ ቋንቋ እንዲያደርጉና የትኛውም ማስታወቂያ ከላይ በጌደኡፋ እንዲጻፍ መልእክት ተላልፏል።

በዚህ መሰረት በገደብ ከተማ የጌደኡፋን ቋንቋን የማይወክሉ ናቸው የተባሉ የተለያዩ  ማስታወቂያዎችን የማንሳት ስራ እየሰራ መሆኑን የገደብ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ገልጿል።

የገደብ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ አስቴር ምትኬ የጌደኡፋ (Gede'uffa) ቋንቋን የስራ ቋንቋ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ከነዚህም ዉስጥ በአማርኛ ብቻ የተጻፉ ማስታወቂያዎችን በማያነሱ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ እርምጃ  ሳይወሰድ በፊት በመጀመሪያ የቃል ማስጠንቀቂያና ትምህርት በመስጠት ቀጥሎም በአማርኛ ብቻ የተጻፉ ጽሁፎችን  በጌደኡፋ እንዲለወጡ መደረጉን  በተጨማሪም ህግ በማያከብሩ አካላት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመሆን እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የጌደኡፋ ቋንቋ የስራ ቋንቋ መሆኑን በመገንዘብ የትኛውም ቦታ የተጻፉ ጽሁፎች በመጀምሪያ በጌደኡፋ መጻፋቸውን  በማረጋገጥ እና የሚያስችግሩ ጽሁፎችም ካሉ ወደ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በመምጣት እገዛ ማግኘት እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡

ይሁንና በከተማዉ ዉስጥ ያሉ አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች ሳንዘጋጅና የመቀየሪያ በቂ ጊዜ ሳይሰጥን ታፔላችን ተነስቶብናል በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።

ይህን ቅሬታ በተመለከተ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጲያ የሰጡት የገደብ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሮ መስታዉት አብርሃም ፤ ለንግድ ድርጅቶች የመጠሪያ ስማቸዉ ላይ የጌዲዮ ቋንቋን (Gede'uffa) ለመጨመር ከተሰጠዉ ጊዜ በላይ ቋንቋውን ለማይችሉ አካላት በወረዳዉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኩል ተጽፎ እስከመሰጠት መድረሱን አሳዉቀዋል።

አሁን ላይ የከተማዉን የንግድ ምልክቶች የስያሜ ቋንቋ ለመቀየር የተቋቋመ ግብረሀይል ስራ ላይ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ መስታዉት ስራዉ ከማህበረሰቡ ጋር በመግባባት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከጌዲኦፋ ቋንቋ (Gede'uffa) ዉጭ ተከልክሏል የሚባለዉ ዜና ከእዉነት የራቀና ከላይ የጌዲኦፋ ቋንቋ ከተጻፈ ከታች ማንኛዉንም ቋንቋ መጠቀም እንደሚቻል ገልጸዋል።

* አንዳንድ በጌዴኦፋ ቋንቋ የተፃፉ ነገር ግን የፊደል ስህተት ያለባቸውም ማስታወቂያዎች እየተነሱ ስለመሆኑ ታውቋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ።

@tikvahethiopia
የሆድ የሆዳችሁን እያወራችሁ ድንገት ማታ ላይ ካርድ ቢያልቅባችሁስ? ችግር የለም! ወደ *711# ብቻ በመደወል ከሳፋሪኮም የአየር ሰዓት ክሬዲት ማግኘት ይችላሉ።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#TayeDendea

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ ደንደአ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተሰምቷል።

ለሚኒስትር ዴኤታው የተፃፈው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ ፦

" ከመስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነዉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመስገንኩ ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት የተነሱ መሆኑን አስታዉቃለሁ። " ይላል።

ደብዳቤው ከራሳቸው አቶ ታዬ ገፅ የተገኘ ነው።

ይህ ተከትሎ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተችተው ፅፈዋል።

አቶ ታዬ ፤ " ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ " ብለው ባሰራጩት ፅሁፍ " የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት። አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ። " ብለዋል።

" እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር። " ያሉት አቶ ታዬ " ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ። " ብለዋል።

" ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። " ያሉት አቶ ታዬ " ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ። እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል " ሲሉ ፅፈዋል።

ምንም እንኳን አቶ ታዬ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ አያይዘው ብስጭታቸውን ቢገልጹም ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

አቶ ታዬ ደንደአ በተለያየ ጊዜ እሳቸው ያሉበትን መንግሥት በመተቸት ይታወቃሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አቶ ታዬ ከሰሞኑን ምን ሲሉ ነበር ?

ዛሬ ታህሳስ 1/2016 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ባረፈበት ደብዳቤ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታነት መነሳታቸው የተገለፀላቸው አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን አነጋጋሪ ቃለ ምልልሶችን ሲሰጡ ነበር።

ለአብነት ፦

▪️የቲክቫህ - ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባልን ጨምሮ ፤ ለተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች በአዳማ በነበረ አንድ ፕሮግራም በሰጡት ቃለ ምልልስ ተከታዮቹን ብለው ነበር ፦

* እንደ ሰላም ሚኒስቴር የሚገባንን ሁሉ #ሥልጣን ተሰጥቶናል ብለን አናምንም። በሀገሪቱ የሰላም ችግር ሲፈጠር፣ #ሰው ሲፈናቀል ያንን የማስቆም ስልጣን ለእኛ አልተሰጠንም። ይሄ #የአወቃቀር ችግር ነው።

* የአደጋ ሥጋት እንኳን #ለእኛ አይደለም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ነው። #ፓሊስ ለእኛ ተጠሪ አይደለም። መሆን የነበረበት እዚህ ነው። #የግጭት ሥጋት ሲኖር የምናዘው አንድም #ሚሊሻ የለንም። ስለዚህም ለሚፈጠሩ ግጭቶች የሰላም ሚኒስቴር #ሊወቀስ_አይገባም

* የስልጣን ፣ የኢኮኖሚ ፣ የፍትህ ችግሮች አሉብን። ሥልጣን ካልተገደበ፣ ተጠያቂነት ካልተረጋገጠ፣ ኢኮኖሚው በፍትሃዊነት ካልተሰራጨና ሌቦች ከተቆጣጠሩት …በፍፁም ሰላም ሊመጣ አይችልም።

* ተጠያቂነትን መስፈን አለበት። ከተጠያቂነት አኳያ ደግሞ ሥልጣን የተሰጣቸው አሉ። ለምሳሌ የፍትህ ሚኒስቴሩ ሥራው ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ መሆን ነበረበት #ድርድር ከመሄድ ይልቅ።

* በኦሮሚያ ክልል #ለ5_ዓመታት ጦርነት እየተካሄደ በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው ችግር አለ። የትግራይ ክልሉም በጣም ይጸጽተናል። ግን ይህንን የሚያደርገው ከጀርባ ያለው ማነው ? እሱን ነው ማወቅ የሚያስፈልገው።

* መከላከያ ሰራዊት ወንድሞቹን መግደል የለበትም ፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም።

▪️ከቀናት በፊት ከ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ደግሞ ተከታዮቹን ብለው ነበር ፦

- በአሁኑ ወቅት በመንግስት ወስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራር በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋ ነው።

- ድሮ መሬት ይዘረፋል ከሚባለው በላይ አሁን ሕጋዊ ሆኖ በቃላት መግለጽ በሚከብድ መልክ እየተንሰራፋ የአስተዳደር ቀውስ ተፈጥሯል።

- የኑሮ ውድነት ሰማይ ደርሶ የመንግሥት ሠራተኛ ቤት ኪራይ መክፈል አቅቶት ከዚህ ቀደም ዘመዶቹን ይረዳ የነበረው ሠራተኛ አሁን በቤተሰቦቹ ይደጎማል።

- በኦሮሚያ ያለው ሕዝባችን ባለፉት 5 ዓመታት ይሞት ነበር። ስንት እንደሞተም በቁጥር አይታወቅም። በጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በእስራኤል ስንት አንደሞተ፣ ከፍልስጤም ስንት አንደሞተ በቁጥር ይታወቃል። በኦሮምያ ያለው እልቂት ግን የሚታወቅ ነገር የለም።

- ስንት የደሃ ሰው ቤት ተቃጠለ፣ ስንት ሰላማዊ ዜጋ ሞተ፣ ምን ያህል ንብረት ተዘረፈ፣ ስንት ሰው አካሉ ጎደለ፣ የሚለውን የሚያውቀው ሰው የለም።

- በኦሮሚያ ከየትኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ነው ያለው ፤ ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ መልኩ ነው አሁን እየሆነ ያለው።

-  በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል የነበረው የሰላም ድርድር እንዲደናቀፍ ያደረገው እኔ ያለሁበት መንግሥት ነው።

- #እኔ_ያለሁበት_መንግሥት ‘ ችግር ውስጥ ነን ፤ ተወያይተን መፍትሄ እናመጣለን ’ ብዬ ስጠይቅ ቤቱ ለውይይት ክፍት አይደለም በማምታታትና በማደናገር ማለፍ ነው የሚፈለገው፤ የእኔ መንግሥት እንዲህ ዓይነት ጸባይ ነው ያለው።

- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን (OLA) የሚመራው ጃል መሮ ፣ መንግሥት ከፈለገ ይግደለኝ ብሎ ፣ መንግሥት በሚቆጣጠረው የአየር ክልል አልፎ፣ ወደ ታንዛኒያ በአውሮፕላን መሄዱ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ነው የሚያሳየው ብዬ አምናለሁ።

- በታንዛኒያ ፣ የዳሬሰላሙ የሰላም ድርድር ተጀምሮ በ2ኛው ቀን ፣ ከመንግሥት ወገን ፕሮፓጋንዳ መንዛት ነው የተጀመረው " ሸኔን አጥፍተናል፣ አከርካሪውን ሰብረናል " የሚል ፕሮፓጋንዳ ተጀመረ። ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን ጦር ከያለበት ተንቀሳቅሶ በ5 ዓመት ውስጥ ያላለቀው ጦርነት በድርድሩ ጊዜ ለመጨረስ፣ እንቅስቃሴ ተደርጓል። ይህ ከመንግሥት ወገን ለሰላም ፍላጎት አለመኖሩን ያሳያል።

▪️የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም. የ3 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ካቀረበ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለምልልስ ይህንን ብለዋል ፦

° በአማራ ክልል ጉዳይ ፤ የተ / ም / ቤት ጭምር ሄዶ ህዝብ ባነገረትበ ጊዜ እንደዚህ አይነት አዝማሚያዎች መኖራቸው ቀድም ብሎ ተለይቶ ነበር፤ ግን ችግሮችን ከመፍታትና አፋጣኝ የሆነ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነትና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል። እኛ ፖሊስ / ፀጥታ ኃይል #የማዘዝ_ስልጣን አልተሰጠንም።

° መንግሥት ከሕወሓት ጋር የፈታውም እና ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት ጥሩ ነው። በአማራ ክልል ያለውም በዚያው መንገድ ሊታይ የሚችል ነው።

ዛሬ ከስልጣን እንደተነሱ የተነገረው አቶ ታዬ ደንደአ ፤
- የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባል፤
- አገሪቷን በሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው።

@tikvahethiopia