TIKVAH-ETHIOPIA
" ያለ ውጤት ተበትኗል " የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን) ጋር በሁለት ዙር ሲካሄድ የነበረው ንግግር ያለ ውጤት መቋጨቱን አሳውቋል። (የመግለጫው ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል) @Tikvahethiopia
#OROMIA
" ' መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ ' የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት አልቻለም " - የኢፌዴሪ መንግሥት
የፌዴራል መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ ከሚጠራው እና በአሸባሪ ድርጅትነት ከፈረጀው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሲካሄድ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት መጠናቀቁን እና መበተኑን አሳውቋል።
ይህ ያሳወቀው ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው።
በመግለጫው ምን አለ ?
በታንዛንያ ዛንዚባር ከወራት በፊት ውይይት ተካሂዶ ሳይቋጭ መቅረቱ አስታውሷል።
በዚሁ ውይይት ወቅት ከ60 ዓመታት በፊት የኦሮሞም የሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ሁሉ ጥያቄዎች የነበሩና ተመልሰው ያደሩ ጥያቄዎችን አንሥቷል ብሏል።
ከለውጥ በኋላ በሥራ ላይ የዋሉ ጉዳዮችን ከማነብነብ ውጭ የሚቆጠርና የሚቋጠር አጀንዳ ማምጣት ስላልቻለ ተንጠልጥሎ እንዲቆይ መደረጉን አመልክቷል።
ባለፉት 2 ሳምንታት ደግሞ ሁለተኛ ዙር ውይይት ታንዛንያ ዳሬ ሰላም ላይ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጿል።
በዚህኛው ዙርም ቡድኑ " መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ " የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት አልቻለም ብሏል።
መንግሥት በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት መሞከሩን አመልክቷል።
ነገር ግን ሸኔ / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት OLF-OLA/ በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል፤ በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል ሲል ገልጿል።
በመሆኑንም ውይይቱ በዛሬው ዕለት ያለ ውጤት ተበትኗል ሲል አሳውቋል።
መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሔ ያለው አቋም አሁንም እንደተጠበቀ እንደሆነ ገልጾ ሕግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማስከበር ተልዕኮውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
በድርድሩ ላይ ተካፋይ ከነበሩት መካከል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ) ምን አሉ ?
- ድርድሩ ካለስምምነት በመጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዘኑን ገልጸዋል።
- መንግሥት ጦርነት ቆሞ በዚህ ሳቢያ ሲደርስ የቆየው ጉዳትና ውድመት እንዲቆም ጽኑ ፍላጎት እንደነበረው ገልጸው በሌላኛው ወገን ግትር ፍላጎት ከስምምነት ሳይደረስ መቅረቱን አመልክተዋል።
- ሌላኛው ወገን / የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት OLF-OLA ተጨባጭ ሁኔታን መሠረት ያላደረገ ፍላጎቶችን በማቅረቡ እና አደናቃፊ አካሄድን በመከተሉ ምክንያት ንግግሩ ከስኬት ሳይደርስ ለመቋጨቱ ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል።
- የኢትዮጵያ መንግሥት የሠላም ስምምነቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እና ሕገ መንግሥትን ባከበረ ሁኔታ ከስምምነት እንዲደረስ ጽኑ ፍላጎትን ይዞ ከስምምነት ለመድረስ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ጥረት ማድረጉን ነገር ግን ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በድርድሩ ስምምነት ላይ እንዳይደረስ ያደረጉ ጉዳዮች የትኞቹ እንደሆኑ በዝርዝር ይፋ አላደረጉም።
በሌላ በኩል ፤ የድርድሩን ያለውጤት መጠናቀቅ በተመለከተ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLF-OLA) እስካሁን ያለው ነገር የለም።
የታጣቂ ቡድኑ አመራሮች የሆኑት ጃል መሮ (ከወለጋ ጫካ) እና ጃል ገመቹ አቦዬ (ከቦረና አካባቢ) በኢጋድ፣ በአሜሪካ፣ በኖርዌይ መንግሥታት አስተባባሪነት በአውሮፕላን ወደ #ኬንያ ከዛም ታንዛኒያ፤ ዳሬ ሰላም እንዲገቡ ተደርገው ድርድሩ ላይ ሲካፈሉ እንደነበር አይዘነጋም።
@tikvahethiopia

#OROMIA " ' መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ ' የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት አልቻለም " - የኢፌዴሪ መንግሥት የፌዴራል መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ ከሚጠራው እና በአሸባሪ ድርጅትነት ከፈረጀው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሲካሄድ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት መጠናቀቁን እና መበተኑን አሳውቋል። ይህ ያሳወቀው ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። በመግለጫው…
#Update
" ታሪካዊ ዕድል ጠፍቷል " - የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLF-OLA)
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLF-OLA) በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ በቅርቡ የተካሄደው የሰላም ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን አሳውቋል።
ለድርድሩ መክሸፍ የኢትዮጵያን መንግሥት ተጠያቂ አድርጓል።
ቡድኑ ይፋ ባደረገው መግለጫ ፤ " የህዝባችንን ዋና ዋና ጥያቄዎች ለመመለስና መንገዱን ለመክፈት በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት ከዛንዚባር እስከ ዳሬሰላም ተከታታይ አካታች ሀሳቦችን አቅርበናል " ሲል ገልጿል።
እነዚህ ሃሳቦች ምን እነደሆኑ ግን በግልፅ አላብራራም።
ታጣቂ ቡድኑ ፤ በሰሞኑን ድርድር ከስምምነት መድረስ ያልተቻለው የኢትዮጵያ መንግሥት አገሪቱን የደኅንነት እና የፖለቲካ ፈተና ውስጥ ለከተቱ መሠረታዊ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ፍላጎት ባለማሳየቱ ነው ብሏል።
" የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱ ውስጥ የማይፈቱ ለሚመስሉ የፀጥታ እና የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ከታጣቂ ቡድኑ አመራሮች ጋር ትብብር ለመፍጠር ብቻ ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል " ሲል በመግለጫው ላይ ገልጿል።
ለኢትዮጵያ ገለልተኛ ተቋማት እንደሚያስፈልጉ ያመለከተው ታጣቂ ቡድኑ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ወደሚፈለገው ውጤት ለመሄድ ሁኔታዎች ለማስተካከል ባለመቻሉ " ታሪካዊ እድል ጠፍቷል " ብሏል።
መንግሥት ከደኅንነት እና ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ መሠረታዊ ለሆኑ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ፍላጎት ባለማሳየቱም ድርድሩ ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ገልጿል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመግለጫው በዚህኛው የሰላም ድርድር ላይ በከፍተኛ አመራሮቹ አማካኝነት ተሳትፎ ማድረጉን አመልክቷል።
የድርድሩን መካሄድ በተመለከተ ሰጥቶ በነበረው መግለጫ ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ታንዛኒያ እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየመሩ መሆኑን መግለፁ አይዘነጋም።
የኢፌዴሩ መንግሥት የድርድሩን አለስምምነት መጠናቀቅ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / OLF-OLA " መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ " የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት እንዳልቻለ ገልጿል።
መንግሥት በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት መሞከሩን አመልክቷል።
ነገር ግን ሸኔ / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት OLF-OLA/ በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት መታየቱንና በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መምረጡን ገልጿል።
በዚህ ምክንያት ውይይቱ ያለ ውጤት መበተኑን ይፋ አድርጓል።

ለብርቱ ክንዶች ፤ ብርቱ አጋር ነን !!
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!
#globalbankethiopia #GBE #banksinethiopia #fintech #bank #finance #ethiopia #ethiopian #digitalbanking #Globaldigital

አዲስ አበባ ሥራ አጦች📈
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ።
በመዲናዋ የሥራ አጦች ቁጥር በመቶኛ እየጨመረ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱትሪ ልማት ቢሮ የሥራ ዕድልና የሥነ ምግብ ዋስት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ ሰምቷል።
ለሥራ አጦች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ እንዲያስረዱ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው ተከታዮችን ነጥቦች አንስተዋል።
- ሥራ አጡ በጣም ሰፊ ነው።
- አዲስ አበባ የአገሪቱ ዋና ከተማ እደመሆኗ መጠንና አጎራባች አካባቢ ካለው የጸጥታ ችግርም አንፃር በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ከተማ ውስጥ በሰፊው የሚገቡ አሉ። እዚህም የከተማውን ማህበረሰብ ከሥራ ዕድልም አንፃር የሚሻሙ ናቸው።
- የከተማው ወጣት አለ። የከተማው ሥራ አጥ የሥራ ዕድል በጥራትም በስፋት እዲፈጠርለት ይፈልጋል፤ በዚህ መካከል እኛ መፍጠር የምንችለው የሥራ እድል እና ከተማ ውስጥ ያለው የሥራ አጦች ቁጥር አይጣጣምም።
- የራሱ የከተማው ነዋሪ አለ፣ በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማ ውስጥ የሚገባም አለ። እነዚህን ሁለቱን አጣጥሞ የሚጠበቀውን ያክል የሥራ ዕድል መፍጠር በጣም ፈታኝ ነው።
- የሥራ አጥ ቁጥሩ አምና ስንጀምር ስብጥሩ በጣም ዝቅተኛ ነበር። ወደ 17 በመቶ አካባቢ የነበረው አሁን አድጎ ወደ 22 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል የሥራ አጥ ቁጥር ምጣኔው።
- እኛ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ወደ አንድ ድርጅት እናወርዳለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን እየጨመረ ነው የሚያሳየው። የዚህ መጨመር ምክንያቱ የተለያየ ቢሆንም አንደኛው ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ያለመቻልን ያሳያል።
- እኛ እየፈጠርን ያለነውና የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚገባው ሥራ አጥ ቁጥሩ ሰፊ ነው ይሄ አልተመጣጠነም።
- የሰው ሀይላችን እስኪልድ ማን ፓወር አይደለም በጣም የሰለጠነ ብቁ ሞያተኛ የሆነ የሰው ሀይል እጃችን ላይ የለም።
- የሰው ሀይላችን ሥራ አጡ በተለይ የትምህርት ደረጃው ዝቅተኛ ነው፤ ይህን ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያለው የሰው ኃይል አሰልጥኖ የክህሎትና የሙያ ባለቤት አድርጎ ወደ ኢንስትሪዎቹ ማስተሳሰርን ይጠይቃል።
በሌላ በኩል ፤ ሥራ ያገኙ ሰዎች ቀጣሪ ኢንዱስትሪዎች የሚከፈላቸው #ደመወዝ_በጣም_አነስተኛ በመሆኑ የቤትና ኪራይና አስቤዛ እንኳ ማሟላት እንደማይችል በተደጋጋሚ ቢገልጹም መፍትሄ እያገኙ እንዳልሆነ፣ ሥራ አጥ የሆኑትም የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ይደመጣል።
ይህንን በተመለከተ አቶ ፍስሃ ምን አሉ ?
" ኢንዱስትሪዎቹ የሚከፍሉት ደመወዝ ዝቅተኛ ነው የእነርሱ ምክንያት ደግሞ እምታቀርቧቸው ሰዎች ሙያቸው ከዚህ በላይ አያስከፍልም የሚል ጥያቄ ያነሳሉ " ብለዋል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ማብራሪያ ያገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኅዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ለተገኙት አቶ ፍስሃ ጥበቡ ጥያቄ አቅርቦ ነው)
ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

Photo
#Update
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሌላ አዲስ ዙር ውይይት ይጀምራሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገለፁ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድርን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።
ዶ/ር ወርቅነህ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ውይይት እና ድርድር ያለውን ወሳኝ ሚና እንደሚገነዘቡ ገልጸዋል።
ኢጋድ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) የሰላም ውይይት ላይ በቅርበት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ በማንኛውም የድርድር ሂደት ውስጥ የማይቀር የፈተናና ውስብስብ ጊዜያት እንዳሉ እንደሚገነዘቡ የከዚህ ቀደም የኢጋድ መሰል ተመሳሳይ ሁኔታዎችን የሽምግልና ሂደቶችን ልምድ በመንተራስ ገልጸዋል።
ዶ/ር ወርቅነህ የሁለቱም ተደራዳሪ ቡድኖች አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰላማዊ ውይይት ማድረጋቸውን አመስግነው ለኢጋድ የቴክኒክ ቡድን እና ታዛቢዎች በተለይ ደግሞ የአሜሪካ እና የኖርዌይ ተወካዮች በውይይቱ ላይ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ውይይቱን በማዘጋጀት ረገድ ለታንዛኒያ ሪፐብሊክ መንግስት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ስራ አስፈፃሚው ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም በማስጠበቅ ለሰላሙ ሂደት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ፤ ቀሪ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱም ወገኖች ሌላ አዲስ ዙር ውይይት ይጀምራሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢጋድ በመንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል ያለው ችግር ተፈቶ ሰላም እንዲሰፍን አሁ እንደሚሰራ የገለፀ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ሁኔታውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የማያቋርጥ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።
ኢጋድ በታንዛኒያው ድርድር መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምን በምን ጉዳዮች እንዳልተስማሙ እንዲሁም አሉ ያላቸውን ቀሪ ችግሮች በይፋ አላብራራም።
በኦሮሚያ ያለው ግጭት እልባት እንዲያገኝ የሰላም ድርድር በማማቻቸትና በመምራት ረገድ ኢጋድ ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጣ ነው።

#SafaricomEthiopia
እንዳጓጓን አልቀርም... በናፍቆት እንደጠበቅነው 07 ቅምሻ የሙዚቃ ኮንሰርት አንድ ቀን ብቻ ቀረው! ሐሙስ ህዳር 13 ቀን ጊዮን ሆቴል አይቀርም።
የ07 ቅምሻ ኮንሰርት መግቢያውን በ250 ብር በM-PESA ሳፋሪኮም አፕ ፤ በአጭር የጥሪ ኮድ *733# ወይም ከM-PESA ሳፋሪኮም ሱቆች ሲገዙ የከፈሉት 250 ወደ M-PESA አካውንትዎ ተመላሽ ከመሆኑም በተጨማሪ ነፃ የ5GB የሳፋሪኮም ዳታ ጉርሻ ያገኛሉ።
መግቢያውን በM-PESA ሳፋሪኮም ሱቆች ማግኘት ይችላሉ። በዕለቱ የ07 ቅምሻ ኮንሰርት መግቢያ በር ላይ 500 ብር ነው።
ፕለይ ስቶር/ አፕ ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ወስኖ የነበረው ፍርድ፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ መሻሩን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው የሦስተኛ ዓመት የአንደኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ በወሰነው መሠረት፣ ፍርድ ቤቶች ያስተላለፉትን ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ቤቶች እንዲሰጡ የሚለው ውሳኔ የተወሰኑ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎችን የሚጥሱና ተቀባይነት የላቸውም በማለት በሙሉ ድምፅ ሽሮታል።
በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተፈርሞ ኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተጻፈው ደብዳቤ፣ በ2005 ዓ.ም ወጥቶ የነበረውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የዕጣ ድልድል ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ቅድሚያ የሚሰጠው መመርያ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንደሚያስፈልገው በምክር ቤቱ ታምኖ እንዲታይ ይገልጻል፡፡
" ሕገ መንግሥታዊ የአካታችነትና የፍትሐዊነት መርህን የጣሰ " ሲል የመመርያውን አንድ አንቀጽ የገለጸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ፣ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቁጠባ ቤቶች ዋነኛ ዓላማ 40 በመቶ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ከባንክ በተመቻቸ 60 በመቶ ክፍያ በመደገፍ እንዲያገኙ ማስቻል እንደሆነ ነው የሚያስረዳው፡፡
ሆኖም አንደኛው የመመርያ አንቀጽ ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የሚያደርግ ሲሆን፣ ይህም ድንጋጌ መግባቱ ‹
" የመመርያውን ግልጽ ዓላማና መንፈስ ያልተከተለ " ሲል ደብዳቤው ያስረዳል፡፡
" ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ቅድሚያ መስጠት በመርሐ ግብሩ ለተመዝጋቢዎች እኩል ዕድል ለማሰጠት የታለመውን መሠረታዊ ዓላማ የጣሰ ነው፤ " ሲል ደብዳቤው ያብራራል፡፡
የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሐ ግብርን የሚያስፈጽመው መመርያ በሰጣቸው መብት መሠረት ሙሉ ለሙሉ የሚጠበቅባቸውን ቁጠባ ከቆጠቡ በኋላ፣ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው የጠበቁ 761 ቆጣቢዎች በዕጣ ማውጣት መርሐ ግብሩ ላይ ቅድሚያ ሳይሰጣቸው 40 በመቶ ከቆጠቡት ጋር እኩል ነበር የተሳተፉት፡፡
ለዚህም ነበር 761 ተመዝጋቢዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝን በመክሰስና እስከ ሰበር ድረስ በመድረስ ሊፈረድላቸው የቻለው፡፡
በፍርድ ቤቶች ተወስኖ የነበረው እየተገነቡ ያሉና ዕጣ ያልወጣላቸውን ቤቶች፣ ከዚህ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ተመዝጋቢዎች እንዲተላለፉ ነበር፡፡
በውሳኔው ቅር ተሰኝቶ የነበረው የከተማ አስተዳደሩ የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ከአንድ ዓመት በፊት ለሕገ መንግሥታዊው ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አቤቱታ አቅርቦ፣ ጉባዔው ጉዳዩን በመመርመር በዚህ ዓመት መስከረም ወር ምክር ቤቱ ሲከፈት ውሳውን አሳልፏል፡፡
የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መርሐ ግብር ለማስፈጸም ወጥቶ በነበረው መመርያ ሙሉ ለሙሉ ለቆጠቡ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ የሚያሰጠውን አንቀጽ፣ ከመስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ " ኢሕገ መንግሥታዊ " በመባሉ እንደማይሠራ ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርም አውጥቶት የነበረው የዚህ መመርያ ድንጋጌ፣ ደብዳቤው ከደረሰው ከኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ እንዲያሻሽልና ውጤቱን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቅ ያሳስባል፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤውን በግልባጭ ለሁሉም የክልልና የከተማ አስተዳደሮች አሳውቋል።
#ሪፖርተር_ጋዜጣ

#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በማዕከል ደረጃ ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ከፍተኛ የሥራ ጫና ወደ አለባቸው ወረዳ እና ተቋማት #ስርጭት እንዲደረግ ወስኗል። ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ እና ለህብረተሰብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ የተወሰነ እንደሆነ ነው የተገለጸው።…
#AddisAbaba #Update
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውክልና ሰጥቶ የሚያሰራቸው የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶች የትኞቹ ናቸው ?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሰኞ ዕለት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ የአስተዳደሩ ተቋማትን አገልግሎቶችን ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የሚለው እንደሆነ ይታወሳል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ፤ በካቢኔው ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶቻቸውን በውክልና ለግል ተቋማት እንዲያስተላልፉ ውሳኔ ላይ የተደረሰባቸው የከተማ አስተዳደሩ 5 መሥሪያ ቤቶች እና ሆስፒታሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከእነዚህ የከተማ አስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የንግድ፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮዎች ይገኙበታል ብለዋል።
የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲሁም አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን አገልግሎቶቻቸውን በከፊል ለግሉ ዘርፍ ከሚያስተላልፉት ውስጥ መካተታቸውን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙት የካቲት 12 እና የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሎችም የዚህ ዕቅድ አካል ናቸውም ብለዋል።
ተቋማቱ ለግሉ ዘርፍ እንዲያስተላልፏቸው የተመረጡት የመንግሥት አገልግሎቶች 46 እንደሆኑ የገለፁት ወ/ሮ ሂክማ ከእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና እድሳት እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩን የግብይት ማዕከላት የማስተዳደር አገልግሎቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።
አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን ማስተለለፍ ለምን ተፈለገ ?
ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ፦
- የተመረጡ አገልግሎቶችን ለግል ተቋማት ለማስተላለፍ የተወሰነው የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፍጥነት፣ ጥራት እና ውጤታማነት የተሻለ ለማድረግ ሲባል ነው።
- ሕብረተሰቡ ከአገልግሎት ውጤታማነት፣ ከአገልግሎት ተደራሽነት ጋር የሚያነሳቸው ጥያቄዎች አሉ። እነዚህን የአገልግሎት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አንዱ መፍትሄ አውትሶርስ አድርገን የግሉ ዘርፍ እንዲሰራቸው ማድረግ ነው።
- ይሄንን ሥራ የሚወስደው የግል ዘርፍ ለትርፍ የሚሰራ አካል ነው። ለትርፉ ሲል ሕብረተሰቡ ጋር የበለጠ ተደራሽ ይሆናል።
- መንግሥት ሁሉም ነገር ላይ ትኩረት አድርጎ ላይሰራ ይችላል ፤ እነዚህ አገልግሎቶች ወደ ግል ተቋማት ሲተላለፉ የመንግሥትን የመቆጣጠር እንዲሁም ሕግ እና ሥርዓትን ተግባራዊ የማድረግ አቅምን ጠንካራ ያደርጋል የሚል እምነት አለ።
- የተመረጡ አገልግሎቶች ከሚተላለፍላቸው አካላት መካከል #የግል_ባለሀብቶች ይገኙበታል። ባለሀብቶች አገልግሎቱን ተረክበው እንዲሰሩ የሚመረጡት #በጨረታ ነው።
- በተጨማሪ አገልግሎቶች ከሚተላለፉላቸው አካላት መካከል ተደራጅተው የሚሰሩ የንግድ ዘርፍ ማኅበራት፤ የተለያዩ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። እነሱም ሥራውን ወስደው መሥራት የሚችሉበት ዕድል ይኖራል። ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ለሚሳተፉም ዕድል አለ።
- የከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን አካላት የሚያስተላልፍ ቢሆንም አገልግሎት አሰጣጡን ይቆጣጠራል።
ለምሳሌ ፦ የንግድ ፈቃድ ስታንዳርዶችን የሚያወጣው መንግሥት ነው። የግሉ ዘርፍ ይህንን ስታንዳርድ አሟልቶ ለመጣ ሰው ፈቃዱን ይሰጣል። አውትሶርስ አድርገው አገልግሎቱን ለመስጠት የወሰዱ ተቋማት በስታንዳርዱ መሠረት ‘ሰሩ አልሰሩም’ የሚለውን ቁጥጥር የሚያደርገው እና ፈቃዶችን ቼክ የሚያደርገው መንግሥት ነው።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

እጥፍ ወለድ ያግኙ!
የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ
=================
ደንበኞች ከውጭ ሀገራት የተላከላቸውን ገንዘብ ወይም በባንኩ የሚመነዝሩትን የውጭ ሀገር ገንዘብ የሚያስቀምጡበት የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡
የቁጠባ ሂሳቡ በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡
• ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል፤
• ደንበኞች ገንዘብ ከውጭ ሀገራት ሲላክላቸው ወይም በባንኩ ሲመነዝሩ የአየር ሰዓት ስጦታ ያገኛሉ፤
• የሂሳቡ ባለቤቶች ለውጭ ሀገር ጉዞ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎታቸው ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፤
• ደንበኞች ከባንኩ ጋር ከሚሠሩ ድርጅቶች ለሚያገኙት አገልግሎት ወይም ለሚገዙት እቃ በፖስ ሲከፍሉ ቅናሽ ያገኛሉ፤
• ሌሎችንም በርካታ ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡
ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!
ይቆጥቡ፤ የበለጠ ያግኙ!

#ትግራይ
በትግራይ ክልል ፤ ማንኛውም የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪ በጫነው ትርፍ ልክ በአንድ ሰው ብር 200 እንዲቀጣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ወስኗል።
የክልሉ የመጓጓዣና መገናኛ ቢሮ ትላንት ህዳር 12/2016 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው ፤ ውሳኔው ይፋ ከሆነበት ሰአትና ቀን ጀምሮ (ማለትም ህዳር 12) የከተማ ታክሲ ፣ ባጃጅና ከከተማ ወደ ከተማ የሚያገለግሉ የህዝብ መጓጓዣዎች ትርፍ ጭነው ከተገኙ በጫኑት ልክ በአንድ ሰው ብር 200 ፣ ከመደበኛ መቀመጫ ውጪ በእቃ መጫና ጭነው የተገኙ በአንድ ሰው ብር 1000 እንዲቀጡ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ በተፈረመ መመሪያ ውሳኔ ማፅደቁ አስታውቋል።
ከዚህ ባለፈ በመመሪያው ፤ ከመደበኛ መቀመጫ ውጪ ሲጓጓዝ የተገኘ ተገልጋይ በተገኘበት ቦታ እንዲወርድ ይደረጋል ተብሏል።

" በድርቁ ምክንያት በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ከ4,000 በላይ የዳልጋ ከብቶች ሞተዋል " - አቶ ምህረት መላኩ
" የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ከተለዩ 180,580 ሰዎች መካከል ድጋፍ ያገኙት ከ50 በመቶ በታች ናቸው " ሲሉ የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አክለውም፣ በመኖ እጥረት በማጋጠሙ በድርቁ ሳቢያ በተለይ የእንስሳት ሞት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን አስረድተዋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኃልፊው በገለጹት መሠረት ፦
- በድርቁ ምክንያት በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ብቻ ከ4,000 በላይ የዳልጋ ከብቶች ሞተዋል።
- 171,000 እንስሳት ወደ አጎራባች ወረዳዎች ተሰደዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተከትበዋል። ቀሪዎቹ የክትባት እጥረት ስላለ አልተከተቡም።
- በአጠቃላይ በወረዳው ከ300,000 በላይ እንስሳት ይገኙ ነበር፣ ከሞቱት ከተሰደዱት ውጭ ያሉትም ከፍተኛ ረሃብ ተጋርጦባቸዋል።
ድጋፉን በተመለከተስ ኃላፊው ምን አሉ ?
➜ ጠቅላላ እንደ ዞን ተጋላጭ ብለን የለየናቸው ወደ 435,000 ማኅበረሰቦች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ በ26 ቀበሌዎች በሦስቱ የድርቅ ተጋላጭ ወረዳዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለን የለየናቸው 180,580 አካባቢ ናቸው። ከእነዚህ መካከል ድጋፍ ያገኙት ከ50 በመቶ በታች ናቸው።
➜ ከክልሉ፣ ከፌደራሉ መንግሥትና ከተለያዩ በጎ ፈቃደኛ አካላት በተገኘ የምግብና የካሽ ድጋፍ በሦስቱም ወረዳዎች ወደ 10,000 ኩንታል፣ ለ35,000 ያህል ተጠጋሚዎችን የአንድ ወር የእህል ሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል። በዚህ ወር በምግብ እጥረት የሞተ ሰው የለም።
➜ በካሽ 5 ዓመታት በሴፍቲኔት ፕሮግራም የታቀፉ ወረዳዎች ስለሆኑ፣ ከሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ጎን በጎን የቀውስ ጊዜ ምላሽ (Shock response) የሚባል የበጀት ድጋፍ ተደርጎ፣ በክልልና በፌደራል መንግሥታት፣ ተጨማሪ በህፃናት ፈንድ ድርጅት፣ ዩኒሴፍና ዳን ቸርች በሚባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ርብርብ 93 ሚሊዮን ብር አግኝተናል።
በዚህም ወደ 11,000 ለሚሆኑ የቤተሰብ መሪዎች የአንድ ዙር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርገናል። (አሁን ባለው የገበያ ስታንዳርድ መሠረት ለአንድ እማውራ ወይም አባውራ በሦስት ዙር ሆኖ የ7,000 ብር ካሽ ነው የሚሰጠው።)
➜ በድምሩ ለ46,000 አካባቢ ማኅበረሰብ ድጋፉን ለማዳረስ ሞክረናል። ነገር ግን የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለን ከለየናቸው ከ180,580ዎቹ ድጋፍ ፈላጊ ማኅበረሰቦች መካከል ድጋፍ ያገኙት ሲሰላ ከ50 በመቶ በታች ነው።
ተማሪዎችን በተመለከተ አቶ ምህረት ምን አሉ ?
🔹 በእንስሳት መሰደድ ምክንያት ወደ ሌላ ወረዳዎች ስለሄዱ ከጠቅላላው መግባት ከነበረበት 47 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ትምህርት ላይ ያሉት። ቀሪዎቹ 53 በመቶ ተማሪዎች ከድርቁ ጋር በተያያዘ ችግር ትምህርት እንዳቋረጡ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።
🔹ተማሪዎቹም እንስሳቱን እንስሳቱን ለመጠበቅ ወደ ደሀና፣ ዝቋላ…. አጎራባች ወረዳዎች ነው የሄዱት።
🔹መኖ ባለመኖሩ የእንስሳት ሞት እየጨመረ መሆኑን ያስረዱት አቶ ምህረት፣ በአጠቃላይ ከችግሩ ስፋትና ካለው ውስብስብነት አኳያ (#የተከዜ ድልድይ በመሰበሩ፣ በጸጥታው ችግር፣ የመኸር ምርት በመቋረጡ)፣ በጣም ተከታታይ ድጋፍ የሚያስፈልግና የክልሉ፣ የፌደራሉ መንግሥታት የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የትግራይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ፤ ሁሉም የወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤቶች የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ እንዲያካሂዱ አዘዘ።
የ12ኛ ክልፍ ፈተና በጥር ወር ውስጥ እንደሚሰጥም አሳውቋል።
ኤጀንሲው ህዳር 12/2016 ዓ.ም ለሁሉም የክልሉ የወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤቶች በላከው ሰርኩላር ደብዳቤ እንደስታወቀው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ከመላ አገር በትግራይ ዘግይቶ የተሰጠው ፈተና በተማሪዎቹ ላይ የፈጠረው ጫና እንዳይደገም የትምህርት ፅህፈት ቤቶቹ በጥር ወር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ጨምሮ ሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያጠናቅቁ ሲል አስገንዝቧል።
ኤጀንሲው በምዝገባው ሂደት እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ ፦
✔ የ8ኛ ክፍል ክልለዊ ፈተና የወሰደበት የምስክር ወረቀት
✔ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ክፍል የተማረበት ውጤት የያዘ ትራንስክሪፕት
✔ በ2011 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰደበት የምስክር ወረቀት፣
✔ የምሽት ትምህርት ተማሪዎች የ10ኛ ክፍል የምስክር ወረቀትና ተያያዥ ጉዳዮች በሟሟላት ለፈተና ሊዘጋጁ ይገባል ተብሏል።
ኤጀንሲው የተጠቀሱት መስፈርቶች ያላሟላ ተማሪ ጥር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መቀመጥ አይችልም ማለቱ ሰርኩላር ደብዳቤው ጠቅሶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
በትግራይ ክልል በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሦስት ዙር ይሰጣል መባሉ አይዘነጋም።
በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡
በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ተማሪ ለነበሩ ተማሪዎች በጥር 2016 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል የተባለ ሲሆን፣ በግንቦት 2016 ዓ.ም መጨረሻ ደግሞ ሦስተኛው ዙር ፈተናን በ2012 ዓ.ም 10ኛ ክፍል ለነበሩ ተማሪዎች ይሰጣል፡፡
Via @tikvahethiopiaTigrigna & @tikvahuniversity