TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በድርቁ ምክንያት በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ከ4,000 በላይ የዳልጋ ከብቶች ሞተዋል " - አቶ ምህረት መላኩ

" የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ከተለዩ 180,580 ሰዎች መካከል ድጋፍ ያገኙት ከ50 በመቶ በታች ናቸው " ሲሉ የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

አክለውም፣ በመኖ እጥረት በማጋጠሙ በድርቁ ሳቢያ በተለይ የእንስሳት ሞት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን አስረድተዋል።

የጽሕፈት ቤቱ ኃልፊው በገለጹት መሠረት ፦

- በድርቁ ምክንያት በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ብቻ ከ4,000 በላይ የዳልጋ ከብቶች ሞተዋል።

- 171,000 እንስሳት ወደ አጎራባች ወረዳዎች ተሰደዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተከትበዋል። ቀሪዎቹ የክትባት እጥረት ስላለ አልተከተቡም። 

- በአጠቃላይ በወረዳው ከ300,000 በላይ እንስሳት ይገኙ ነበር፣ ከሞቱት ከተሰደዱት ውጭ ያሉትም ከፍተኛ ረሃብ ተጋርጦባቸዋል።

ድጋፉን በተመለከተስ ኃላፊው ምን አሉ ?

➜ ጠቅላላ እንደ ዞን ተጋላጭ ብለን የለየናቸው ወደ 435,000 ማኅበረሰቦች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ በ26 ቀበሌዎች በሦስቱ የድርቅ ተጋላጭ ወረዳዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለን የለየናቸው 180,580 አካባቢ ናቸው። ከእነዚህ  መካከል ድጋፍ ያገኙት ከ50 በመቶ በታች ናቸው። 

➜ ከክልሉ፣ ከፌደራሉ መንግሥትና ከተለያዩ በጎ ፈቃደኛ አካላት በተገኘ የምግብና የካሽ ድጋፍ በሦስቱም ወረዳዎች ወደ 10,000 ኩንታል፣ ለ35,000 ያህል ተጠጋሚዎችን የአንድ ወር የእህል ሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል። በዚህ ወር በምግብ እጥረት የሞተ ሰው የለም።

➜ በካሽ 5 ዓመታት በሴፍቲኔት ፕሮግራም የታቀፉ ወረዳዎች ስለሆኑ፣ ከሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ጎን በጎን የቀውስ ጊዜ ምላሽ (Shock response) የሚባል የበጀት ድጋፍ ተደርጎ፣ በክልልና በፌደራል መንግሥታት፣ ተጨማሪ በህፃናት ፈንድ ድርጅት፣ ዩኒሴፍና ዳን ቸርች በሚባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ርብርብ 93 ሚሊዮን ብር አግኝተናል።

በዚህም ወደ 11,000 ለሚሆኑ የቤተሰብ መሪዎች የአንድ ዙር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርገናል። (አሁን ባለው የገበያ ስታንዳርድ መሠረት ለአንድ እማውራ ወይም አባውራ በሦስት ዙር ሆኖ የ7,000 ብር ካሽ ነው የሚሰጠው።)

➜ በድምሩ ለ46,000 አካባቢ ማኅበረሰብ ድጋፉን ለማዳረስ ሞክረናል። ነገር ግን የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለን ከለየናቸው ከ180,580ዎቹ ድጋፍ ፈላጊ ማኅበረሰቦች መካከል ድጋፍ ያገኙት ሲሰላ ከ50 በመቶ በታች ነው።

ተማሪዎችን በተመለከተ አቶ ምህረት ምን አሉ ?

🔹 በእንስሳት መሰደድ ምክንያት ወደ ሌላ ወረዳዎች ስለሄዱ ከጠቅላላው መግባት ከነበረበት 47 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ትምህርት ላይ ያሉት። ቀሪዎቹ 53 በመቶ ተማሪዎች ከድርቁ ጋር በተያያዘ ችግር ትምህርት እንዳቋረጡ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

🔹ተማሪዎቹም እንስሳቱን እንስሳቱን ለመጠበቅ ወደ ደሀና፣ ዝቋላ…. አጎራባች ወረዳዎች ነው የሄዱት።

🔹መኖ ባለመኖሩ የእንስሳት ሞት እየጨመረ መሆኑን ያስረዱት አቶ ምህረት፣ በአጠቃላይ ከችግሩ ስፋትና ካለው ውስብስብነት አኳያ (#የተከዜ ድልድይ በመሰበሩ፣ በጸጥታው ችግር፣ የመኸር ምርት በመቋረጡ)፣ በጣም ተከታታይ ድጋፍ የሚያስፈልግና የክልሉ፣ የፌደራሉ መንግሥታት የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia