TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HibretBank

የሕብረት ባንክ አጠቃላይ ካፒታል 9.3 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገለጸ።

የባንኩ የሀብት አጠቃላይ ካፒታል 9.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፣ ባንኩ 1.3 ቢሊዮን ዶላር እሴት፣ ከ8,800 በላይ ሠራተኞች፣ ከ475 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት፣ እንዲሁም ብድሩ 60 ቢሊዮን መሆኑን አስረድተዋል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ከ40 ቢሊዮን ወደ ከ60 ቢሊዮን በላይ መድረሱን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ አጠቃላይ የሀብት መጠኑም 83 ቢሊዮን ብር ነው ብለዋል።

ባንኩ የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን እያከበረ የሚገኝ ሲሆን፣ አቶ መላኩ ይህን ያሉትም በዚሁ መርሀ ግብር ተገኝተው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ነው።

አቶ መላኩ የባንኩን የየዓመቱ ጉዞ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ "በየ ዓመቱ ከ25 እስከ 30 በመቶ እያደገ የመጣ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም፣ "ብዙ የማኔጅመንት ሠራተኞች ተቀያይረዋል ሥራው ላይ ግን አንድም የተስተጓጎለ ነገር የለም" ሲሉ የሥራ ሂደቱን በተመለከት ተናግረዋል።

ሕብረት ባንክ የተመሠረተው በ1991 ዓ.ም ሲሆን፣ ዛሬ (ማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም) የ25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በመንግሥት መስሪያ ቤቶች " ያለ አላግባብ ወጪ ተድርጓል " ተብሎ በሂሳብ ምርመራ ከተረጋገጠው ገንዘብ እስካሁን 1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ተመላሽ ተደርጓል ተብሏል።

ይህ የተሰማው ከኦዲት ባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም የ2015 ዓ/ም የአፈፃፀም ሪፖርት ነው።

እንደዚህ ሪፖርት መረጃ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ህግ ተጥሶ ወጪ በመደረጉ እንዲመለስ ያለው በአጠቃላይ 7.7 ቢሊዮን ብር በላይ ነው።

ከዚህ ውስጥ 1.3 ቢሊዮን ብር ተመላሽ እንደሆነ ተገልጿል።

- የጥሬ ገንዘብ ጉድትለት የተገኘባቸው፤

- መስሪያ ቤቱን ጭምር ለለቀቁ ሰዎች በደመወዝ መልኩ ወጪ የተደረገ ገንዘብ፤

- በሚሊዮኖች ብር ወጪ ተደርጎ ግዥ ተፈፅሟል ከተባለ በኃላ ደረሰኝ ቢገኝም ተገዝቷል የተባለው እቃ ለሂሳብ መርማሪ አካል ማቅረብ ያልቻሉ፤

- መክፈል ካለባቸው በሚሊዮን ብልጫ ያለው ገንዘብ ከፍለው የተገኙ መ/ቤቶች በርካታ እንደሆኑ ተነግሯል።

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተደረገ የሂሳብ ምርመራ ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች መንገዶች ህግ ተጥሶ ወጭ የተደረገው ገንዘብ ተመላሽ እንዲደረግ ለመስሪያ ቤቶቹ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ነበር።

በዚህ መሰረት መ/ቤቱ በ2013 ዓ/ም ባቀረበው የኦዲት ግኝት ላይ ያለ አግባብ ወጪ ያደረጉ ገንዘቡን እንዲመልሱ ከጠየቀው ገንዘብ እካሁን የተመለሰው 1.3 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ታውቋል።

ሪፖርቱ ተመላሽ ይደረግ ካለው 7.7 ቢሊዮን ብር የተሟላ ሰነድ በማቅረብ የድምር ስህተት መኖሩን በማረጋገጥና በሌሎች ምክንያቶች 3.2 ቢሊዮን ብር ላይ ማስተካከያ መደረጉን ያሳያል።

ይህ ማስተካከያ ተደርጎ ከ4.4 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግሥት ተመላሽ እንዲሆን ቢጠበቅም እስካሁን የተገኘው 1.3 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው።

ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ የሂሳብ አያያዝ ችግር እንዳለባቸው በሂሳብ ምርመራ የተደረሰባቸው መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎቻቸው ከገንዘብ ቅጣት እስከ ማባረር የደረሰ እርምጃ መወሰዱ ተነግሯል።

የመስሪያ ቤቶቹ የበላይ ኃላፊዎች እና የፋይናንስ ኃላፊዎች በድምሩ 76 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው የተገለፀ ሲሆን ከመካከላቸው የሁለት ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

በሂሳብ አያያዝ ከፍተኛ ችግር አለባቸው የተባሉና እርምጃም ከተወሰደባቸው መካከል #ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች መስሪያ ቤቶች ይገኙበታል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🔹" ችግር ላይ ላለዉ መምህር ተገቢ ያልሆነ መልስ ነው የተሰጠን " - መምህራን 🔸 " ችግሩን ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሶ ወደስራ የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች አሉ ፤  ከሰኞ ጀምሮ ወደአካባቢዉ እናቀናለን " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በማዕከላዊ ኢትዮጰያ ክልል ሃዲያ ዞን የባዳዋቾ ወረዳና የሾኔ ከተማ ትምህርት ቤቶች አሁንም አለመከፈታቸዉ ተሰምቷል። በባዳቾች ወረዳና ሾኔ ከተማ…
#ጠምባሮ

" መምህራን ኑሮ አቅቷቸው አብዛኞቹ ንብረታቸውን፣ ሞባይላቸውን እየሸጡ ነው " - የ3 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህር

መምህራን ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ሥራ በማቆማቸው ምክንያት እስከዛሬ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ትምህርት አልተጀመረም።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኘው ጠምባሮ ልዩ ወረዳ፣ ለተከታታይ 3 ወራት ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን ሥራ እንዳቆሙና የዘመኑ የመማር ማስተማር ሒደትም እስከ አሁን እንዳልተጀመረ ገልጸዋል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህር ፤ የ3 ወር ደመወዝ አላገኘንም መምህራን ኑሮ አቅቷቸው አብዛኞቹ ንብረታቸውን፣ ሞባይላቸውን እየሸጡ ነው፤ ትምህርት እስካሁን ያልጀመረበት ዋናው ምክንያት ደመወዝ አለመከፈሉ ነው ብለዋል።

እኚሁ መምር ደመወዝ ሊከፈል ያልቻለው ወረዳው ውስጥ ያሉ አስተባባሪዎች መምራት ስላልቻሉ ነው ብለዋል።

" ከክልል ደመወዝ ይላካል ከክልል የሚላከውን ገንዘብ በአንድ ቀን በውሎ አበል ያወጡታል በዚህም እኛን ችግር ውስጥ ጥለውናል ተማሪ ፣ ወላጆች ፣ ህፃናትም እንዲቸገሩ ሆኗል ፤ ተማሪዎች ትምህርት ባለመማራቸው አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንስከመውደቅ እና ስደትን እንስከመምረጥ ድርሰዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔም ከመምህርነት ውጭ ሌላ ስራ የለኝም ደመወዝ ስላልተከፈለኝ የምበላውን እየምጠጣውን አጥቻለሁ " ብለዋል።

ሌላው ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህር መሰረታዊው የትምህርት ስራ እንዳይጀመር ያደረገው የደመወዝ ችግር ነው ብለዋል። ተጓዳኝ የልማት ችግሮች ፣ የፖለቲካ ምላሽ ከሚፈልጉ ጉዳዮችም መኖራቸውን አንስተዋል።

ተማሪዎች በበኩላቸው ፤ ወደ ትምህርት ሳይመለሱ ከ2 ወር በላይ እንደባከነ ገልጸዋል። ይህም ከፍተኛ የመደበል ስሜት እንዳሳደረ ጠቁመዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ተማሪ ሌሎች በባከነው ጊዜ ምክንያት ሌሎች የሀገሪቱ ተማሪዎች ላይ መድረስ እንደሚያስቸግር ተናግሯል። ዕጣ ፋንታችንም አናውቅም ብሏል።

አንድ ወላጅ በበኩላቸው ለችግሩ መፍትሄ የሚሰጥ ጠፍቷል ሲሉ ተናግረዋል። ትውልዱ ወደ ጭለማ እየሄደነው ሲሉ አክለዋል።

የማዕከላዊ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ በፈቃዱ፣ በደመወዝ አለመከፈል የተነሳ የጠንባሮ ልዩ ወረዳን ጨምሮ እንደ ሀዲያ ዞን ባሉ አካባቢዎች የዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ እንደተቋረጠ አምነዋል።

የችግሩ መንስኤ በበጀት እጥረት እና በተያያዥ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል። ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በአዲስ አመት እንዴት የበጀት እጥረት ይከሰታል ተብለው ሲጠየቁ ፤ በዋናነት ከማዳበሪያ እዳ ጋር በተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል።

እዳው 5 ፣6 ፣ 7 ፣ 8 ዓመት የነበረ እንደሆነ ጠቁመው ያ እዳ መቆረጥና በየጊዜው በሚከሰተው የበጀት እጥረት ወረዳዎች ስለሚበደሩ ብድሩ ተከማችቶ ዛሬ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ኃላፊው ለመፍትሔው፣ ከዞኖቹ የሥራ ኃላፊዎች ጋራ እየመከሩ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

በቴሌብር ትዊተር ገጽ በተደረገው የ2ኛ ዙር የ#ንቁ_ተሳታፊ ውድድር 10 ጊ.ባ ወርኃዊ የኢንተርኔት ጥቅል አሸናፊዎች የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

አሸናፊዎች በተወዳደራችሁት የቴሌብር ትዊተር ገጽ በውስጥ መልዕክት እየሰራ ያለ (Active) የስልክ ቁጥር በ 24 ሰዓት ውስጥ ላኩልን።

አብሮነታችን በሽልማት ደምቆ ይቀጥላል!

ለመሳተፍ https://twitter.com/telebirr ይቀላቀሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#ኬኬ_ሕትመት_ማሽን

EPSON L3250 PRINTER

COPY - PRINT - SCAN የሚያደርግ ፣ Wi-Fi አካቶ የያዘ ፣ አንዴ በመሙላት እስከ 7,500 ገፆች ማተም የሚችል ፣ ከፍተኛ የህትመት ጥራት ያለዉ ነጻ ዴሊቨሪ ጋር 🚚
እንዲሁም Epson L3210 & L3110 አለን

ይደዉሉ - 0955937183
ቴሌግራም - https://t.iss.one/KKAY01
አድራሻ - ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ አጠገብ አይመን ህንጻ ቁ-203
TIKVAH-ETHIOPIA
" በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተሰቃየን ነው " - ነዋሪዎች በመተከል የተለያየ ወረዳ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው ገለፁ። በመተከል ዞን ቡለን፣ ድባጤ እና ወንበራ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት በቋሚነት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው በመግለፅ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።…
#Update

የመተከል ዞን እና የወረዳው መንግስት ከታጠቁ  ሀይሎች ጋር ያደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በተሰራ የጥገና ሥራ ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረው የድባጢ ከተማ መብራት አገልግሎት ማግኘቱ ተገልጿል።

የድባጢ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ተወካይ አቶ ቀረብህ ቀለሙ የድባጢ ከተማ ከግልገል በለስ  -  ዳኋዝ ባጉና-  ገስስ በሚመጣው መስመር የመብራት ተጠቃሚ እንደነበር አንስተው በአከባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከአመት በላይ አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

በመተከል ዞን ቡለን፣ ድባጤ እና ወንበራ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት በቋሚነት ካገኙ ከ2 ዓመት በላይ እንደሆናቸውና በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተቸገሩ መሆናቸውን ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች በውይይት እና በስምምነት እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቀረበች። ይህ ጥሪ የቀረበው ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት 2016 ዓ/ም ጉባኤውን ካጠናቀቀ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን…
#EOTC

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም መወሰኑ አይዘነጋም።

ይህንን በተመለከተ ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ፤ ቤተክርስቲያን ሰላም ያሳጡን ጦርነቶችና ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙና በአጭሩ እንዲቋጩ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ፤ እምቢ ባዮችንም ታወግዛለች ዘላቂ መፍትሄ የሚገኝባቸውን ሂደቶችንም ትቀይሳለች ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ቅድስት ቤተክርስቲያን የጥላቻና ሀሰተኛ ትርክቶችን እንደምታወግዝ አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " የአሁኑ ጸሎተ ምኅላ የሚደረገው ፦
- አለመግባባት በምክክር፣  በውይይት፣ በመደማመጥ እንዲፈታ፤
- መከራን በመረዳዳት እንድንሻገር፣ እንደየ ኃላፊነታችን የሚጠበቅብንን ለመወጣትና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ እንድንችል፣ ችግራችን ሁሉ ተፈትቶ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሃሊው አምላክ እንዲያግዘን በአንድነት ለመጮኽ ነው፡፡ " ብሏል።

የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ አዋጁ ዓለማው መንፈሳዊ ብቻ እንደሆነ ያስገነዝበው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ የሚድያ፣ የትምህርትና የፍትሕ፣ መሰል ተቋማት ይህንን በመረዳት በሚያስፈልገው ሁሉ እንዲተባበሩ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም አሳስቧል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ በሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም መወሰኑ አይዘነጋም። ይህንን በተመለከተ ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ፤ ቤተክርስቲያን ሰላም ያሳጡን ጦርነቶችና ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ…
" የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል "

የጾምና የጸሎተ ምኅላ አፈጻጸም እንዴት ነው ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላለፈች።

ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀው የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸምንም ይፋ አድርጋለች።

ቤተክርስቲያን ፤ ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ተዘግቶ ሁሉም በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንዲቀርብ በዜጎች መካከል ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላልፋለች።

በዚህም ቋሚ ሲኖዶስ በኅዳር ወር 2016 ዓ/ም የሚከተለውን የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸም አውጥቷል፡፡ 

አፈፃፀም ፦

- የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር 15 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤
 
- በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤ 

- በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

- በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር 15 ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር 21 ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

- በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

- በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

- ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤ 
 
- አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia