TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም

ኩባንያችን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ እቅዱን በላቀ አፈጻጸም ማጠናቀቁን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው !

ኩባንያችን በበጀት አመቱ አጋማሽ የደንበኞቹን ብዛት 74.6 ሚሊዮን በማድረስ የእቅዱን 98.3% እንዲሁም 42.86 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 98% ማሳካት ችሏል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 84.7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 109% ያሳካ ነው፡፡

ኩባንያችን የገቢ አማራጮችን ለማስፋት ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረቶች በተጨማሪ ወጪን በአግባቡ ለመጠቀም ተግባራዊ ባደረገው (DO2SAVE) ስትራቴጂ በግማሽ አመቱ ብቻ ከብር 2 ቢሊዮን በላይ በመቆጠብ የዕቅዱን 113% አሳክቷል፡፡

ይህም ኩባንያችን ትርፋማ እንዲሆን ለምናደርገው የጋራ ጥረት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሠረት ከውጪ ኦዲት ምርመራ በፊት ያልተጣራ ትርፍ (EBITDA) ብር 19.77 ቢሊዮን (46%) በማግኘት የእቅዱን 137% ለማስመዝገብ ችሏል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ብር 11 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ የተመዘገበ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14% እድገት ሲኖረው የትርፋማነት መጠኑን ወደ 26% ያደርሰዋል፡፡

ውድ ደንበኞቻችን እና የስራአጋሮቻችን ለዚህ ስኬት ስላበቃን አብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን!

#Ethiotelecom #telebirr #GSMA #ITU
ኢትዮ ቴሌኮም

የዘመናችንን መጨረሻውን የ5ኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎት በሐረር እና ሀሮማያ ከተሞች በይፋ ማስጀመራችንን ስናበስር እጅግ ደስ ይለናል!

አገልግሎቱን ከትናንት በስቲያ በድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ጂግጂጋ ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል።

የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ወሳኝ ለሆኑ፣ በከፍተኛ ቅጽበት፣ ፍጥነትና በተመሳሳይ ወቅት (real-time) መከወን ላለባቸው ማኑፋክቸሪንግ፣ ጤና ፣ ትምህርት፣ ትራንስፖርት፣ ግብርና፣ ስማርት ሆም፣ ለብሮድካስቲንግ፣ በክላውድ ላይ ለተመሰረቱ የ5ጂ ጌሞች እንዲሁም የIOT ቴክኖሎጂዎች እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የህዝባችንን ኑሮ በእጅጉ የሚያሻሽል፣ የደንበኞችን ምቾት የሚጨምር፣ የቢዝነስ እንቅስቃሴ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ምህዳር በመፍጠር #ዲጂታል_ኢትየጵያን እውን ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!

ለበለጠ መረጃ: https://bit.ly/49uT5WX

#ITU #GSMA
በዲጂታል እና ፋይናንሻል አካታችነት ሴቶችን ማብቃት!

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል ተካታችነት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት “Connected Women” ኢኒሼቲቭ- ከ GSMA ጋር በባርሴሎና ስፔን ተፈራርሟል::

ስምምነቱ በሀገራችን የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት /ቴሌብር/ ተጠቃሚ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ኩባንያው ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አካታች የሞባይል ኢንተርኔት እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ሴቶች በሀገራችን ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ኩባንያችን አሁን የሚታየውን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማጥበብ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚው ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT
#PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችን ይታወቃል።

በማስከተል ምዝገባ በተጀመረባቸው ማዕከላት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተገኝተው አተገባበሩን ተመልክተዋል።

በዚህም ወቅት ለምዝገባው አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸው እና የምዝገባ አገልግሎቱ በላቀ ፍጥነት መስጠት መቻሉን በተግባር መመልከት ችለዋል፡፡

አገልግሎቱ በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት የሚስፋፋ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ተገልጋዮች ስለዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ እንዲረዱ የማድረግ ሥራ በስፋት እንደሚከናወን ተነግሯል።

ዜጎች በአቅራቢያቸው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንበትን የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከል ለማወቅ ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ውስጥ የተካተተውን አዲስ የአቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ ዳታ በማብራት ብቻ በነጻ መጠቀም ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ ፦
https://t.iss.one/telebirr
https://t.iss.one/ethio_telecom

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #NIDP
(ኢትዮ ቴሌኮም)

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

ቴሌብር በዲጂታል ሥነ-ምህዳሩ ላይ በነበረው የላቀ አበርክቶ የስትራይድ አዋርድ 2024 ኢኮሲስተም ሻምፒዮን  (Stride Award 2024 Ecosystem Champion) ተሸላሚ ሆነ!

የሽልማት መርሃግብሩን ያዘጋጀው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሆን ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያን ከመገንባት አንጻር በተለይም ለሀገራችን የዲጂታል ፋይናንስ መነቃቃት ላበረከተው የላቀ አስተዋጽዖ እውቅናው መበርከቱ ተገልጿል፡፡

ለዚህ ሽልማት ላበቃችሁን ለመላው የኩባንያችን ቤተሰቦች፣ ደንበኞቻችን፣ ባለድርሻ አካላት እና አጋሮቻችን ከልብ እናመሰግናለን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU