TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚኒስትሮች ም/ቤት 👆 የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ 'ሕወሓት' እና 'ሸኔ' ድርጅቶች በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ከላይ ያለውን ዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል። በተጨማሪም መንግለጫውን በዚህ ማስፈንጠሪያ ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/PM-Office-05-01 @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'ሸኔ' እና 'ህወሓት'

የህግ ምሁራንና ባለሞያዎች አስተያየት እና የህ.ተ.ም/ቤት ጥሪ ፦

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባስተላለፈው ማስታወቂያ "ህወሓት" እና "ሸኔ" የሚባሉት ድርጅቶች በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበው ውሳኔ ሃሳብ ላይ የተቃውሞ ማስረጃ ካላቸው በአካል እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።

የምዑራን አስተያየት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ላይ ፦

• የህግ ጠበቃ እና አማካሪው አቶ አመሃ መኮንን ፡

"እነዚህ ድርጅቶች በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ስጋት፣ ለህዝቡ ፀጥታ ስጋት ፣ለሀገር ሰላም ስጋት የሚሆኑበት መንገድ በእጅጉ ይቀንሳል ብዬ ገምታለሁ።
በሽብረትኝነት የመሰየሙ ውጤት ፦
- እነዚህን ድርጅቶች መምራት የሚያስጠይቅ ይሆናል።
- የድርጅቶቹ አባል መሆን ያስጠይቃል።
- ድርጅቶቹን ባማቸውም ሁኔታ መደገፍ እና መተባበር የሚያስጠይቅ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ በእጅጉ አቅም የሚያሳጣቸው ነው የሚሆነው።"

• በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ሚኪያስ በቀለ :

"...አሁን አጠያያቂ የሆነው አንዱ ጉዳይ ፥ ሸኔ የሚባል ድርጅት አለ ወይ ? የሚለው ነገር ነው። እራሱን "ሸኔ" ብሎ የሚጠራ ቡድን አይታወቅም። ስለዚህ መንግስት ማለት የፈለገው የኦነግ የወታደራዊ ክንፉን ለማለት ይመስለኛል። 

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደንብ አድርጎ መርምሮ እነዚህን ድርጅቶች እራሳቸውን እንዲከላከሉ እድል ሰጥቶ ሽብርተኛ ድርጅት ነው የሚለውን ስያሜ ሊሰጥ ይችላል።

ውሳኔው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚፀድቅ ከሆነ በተለይ ህወሓት በትግራይ ፣ ሸኔ በኦሮሚያ መሰረታቸውን ያደረጉበት ህዝብ ላይ እንግልት እንዳይኖር ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል።"

• ስማቸውን ያልተገለፀ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር :

“በሽብርተኝነት ሊፈረጅ የሚችል አካል ለቁጥጥር ያስቸገረ ጠንካራ መዋቅር ያለው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያው ጭምር ህወሓት ስጋት ሊሆን በማይችልበት ደረጃ መመታቱን እና መዳከሙን ደጋግመው በአደባባይ በተናገሩ ማግስት እንዲህ መባሉ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

‘አጥፍተነዋል’ በሚል ሲነገር የነበረው ፕሮፓጋንዳ እንደነበር እና ህወሓት አሁንም ስጋት እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የመንግስትን ተዓማኒነት 'ይበልጥኑ የሚጎዳ' ነው።

• የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና ፌደራሊዝም መምህሩ ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ :

“ውሳኔ እንዲያውም ቢዘገይ እንጂ የሚጎዳ አይደለም።

ህወሓትን ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰው ጉዳት ብቻ በቂ ነው።

ህወሓት ባለፉት 3 ዓመታት በግልጽና በስውር በርካታ ጥፋቶችን አድርሷል። የዘገየ ግን ትክክለኛ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።

መንግስት በውሳኔ ሃሳቡ ኦነግ ሸኔ ከማለት ይልቅ ‘ሸኔ’ ማለቱ ምናልባት ለሌላ ትርጉም እንዳይጋለጥ በማሰብ ሊሆን ይችላል እንጂ ‘ሸኔ’ በሚል በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩ ማንኛውንም ማህበረሰብ እንደፈለገ እየገደለ ነው ይሄንን የሚያደርገው ደግሞ "ኦነግ ሸኔ" ነው።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/SHANE--TPLF-05-03

#AL_AIN #Deutsche_Welle #SolomonMuchie #HoPR
#HoPR #MoE

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ2013 ዓ.ም አገር ዐቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አቅም መገንባት እና ተዓማኒነትን ማሳደግ ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው የትምህርት ተቋማትን ተዓማኒነት ለመሸርሸር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተገቢ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ አባላት የፈተና አሰጣጥ እና እርማት ሂደት እንዲሁም በፈተናዎች ደህንነት ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበዋል።

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እርማትና ውጤት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ያለበት ማንኛውም አካል ሂደቱን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ ከፈለገ ማስተናገድና ግልጽነት መፍጠር እንደሚቻል የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በመጀመሪያው ዙር ከተሰጡት የትምህርት አይነቶች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና እንደተሰረቀ የሚያሳዩ አሳማኝ መረጃዎች መቅረባቸውን ተከትሎ የሲቪክስ ውጤት ከዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ እንዲሰረዝ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙዔል ክፍሌ (ዶ/ር) አስታውሰዋል።

ከክልሎች የተውጣጡ የፖለቲካ አመራሮች እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ትንተና እና የአስተራረም ሂደት ታይቶ የተፈጠረ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበር የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈሪ ፈይሳ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ የህ/ተ/ም/ቤት

More @tikvahuniversity
#HoPR

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ም/ቤቱ እያካሄደ ባለው ሰብሰባ የም/ቤቱን 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ አፅድቋል።

በተጨማሪ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት ፦

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሰብሳቢ
2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፤ ም/ሰብሳቢ
3. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል፤ አባል
4. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
5. ዶ/ር በድሉ ዋቅጀራ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
6. ዶ/ር መሣይ ገ/ማሪያም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
7. ዶ/ር ወዳጀነህ ማዕረነ አማካሪ፤ አባል
8. ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል
9. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል ሆነው ሹመተቸው በተቃውሞ በ11 እና በ17 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በአሁን ሰዓት ም/ቤቱ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማድመጥ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#HoPR

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቃል የሚሰጡትን ምላሽ ያዳምጣል።

ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ መደበኛ ጉባዔ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተያዘው አጀንዳ መሠረትም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ጥያቄዎችን ያቀርባሉ። እንደዚሁም አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ።

ስብሰባው በቀጥታ ለህዝብ ይሰራጫል ተብሏል።

Via HoPR

@tikvahethiopia
#HoPR

ነገ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ህ/ተ/ምክር ቤት ይቀርባሉ።

በዚህም በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

በተጨማሪ ፓርላማው በተለያዩ ጉድዮች ላይ ውይይት ያደርጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ! ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በህ/ተ/ም/ቤት ቀርበው ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል። የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንፁሃን ዜጎች ግድያን ፣ የህግ ማስከበርን፣ ሰላማዊ ሰልፍ፣ የሰላም ጉዳይን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። ያንብቡ 👉https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-07-07 (የጠ/ሚ…
#HoPR

የ2015 ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ/በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ አውቶሜት ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል።

ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በርካታ ታብሌት ኮምፒዩተሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት አምራች ድርጅቱ ኮምፒዩተሮቹን በተያዘለት ጊዜ ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኮምፒዩተሮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከደረሱ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የቀጣይ ዓመት ፈተና ኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ታብሌቶቹ በሚጠበቀው ጊዜ ካልደረሱ፥ መንግስት የፈተና ስርቆት የሚቀነስበት የተሻለ አሰራር በመከተል ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#HoPR

ዛሬ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ይካሄዳል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ቀርበው ከም/ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ፤ የመንግስትንም አቋም ያሳውቃሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል። ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር። ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ…
#ኦዲት

" በ86 የመንግስት መስሪያ ቤቶች 6 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ነው ተመላሽ የሆነው " - የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት

የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ፤ የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ ስለመጣ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰቡ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ይህ ያሳሰቡት ከቀናት በፊት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለፓርላማው የ2014 ዓ/ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ክንዋኔ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለት ዓለማ በትክክል እንዲውል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚበረታታ ነው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " የክዋኔ ኦዲት ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ የሪፖርቱን ተአማኒነት እና ተቀባይነትን ማረጋገጥ ይገባል " ብለዋል።

ዋና ኦዲተር የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ እና ሪፖርት በወቅቱ በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በይበልጥ ጥረቱን አጠናክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " አስፈጻሚው አካል ለኦዲት ግኝቶች ትኩረት ባለመስጠት የገንዝብ የመመለስ ምጣኔው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተቋማትን በመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ የመጣ በመሆኑ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።

የፌደራል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው ፤  " በ86 የመንግስት መ/ ቤቶች 6 ቢለዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ተመላሽ በመደረጉ የሚፈለገውን ለውጥ እያመጣ አይደለም።  " ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ኦዲተሯ ፤ በተወሰኑ የመንግስት እና የህዝብ ሃብት ባባከኑ የስራ ኃላፊዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰዱን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

#HoPR

@tikvahethiopia
በዲጂታል እና ፋይናንሻል አካታችነት ሴቶችን ማብቃት!

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል ተካታችነት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት “Connected Women” ኢኒሼቲቭ- ከ GSMA ጋር በባርሴሎና ስፔን ተፈራርሟል::

ስምምነቱ በሀገራችን የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት /ቴሌብር/ ተጠቃሚ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ኩባንያው ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አካታች የሞባይል ኢንተርኔት እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ሴቶች በሀገራችን ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ኩባንያችን አሁን የሚታየውን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማጥበብ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚው ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
#HoPR

በእስር ላይ የሚገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት ተነሳ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው ስብሳባ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

ዛሬ ያለ መከሰስ መብታቸው የተነሳው የተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከወራት በፊት ከቤታቸው ተወስደው መታሰራቸው የሚዘነጋ አይደለም።

እስሩ በአማራ ክልል በመንግሥት የፀጥታ ኃይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የትጥቅ ግጭት ከተጀመረ በኃላና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ የተፈፀመ እንደነበር ይታወሳል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው በማሸነፍ ነበር።

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT
#PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF

(ኢትዮ ቴሌኮም)
TIKVAH-ETHIOPIA
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የኢዴፌሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሠረት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲተገበር የሚያደርግ አዋጅ አፅድቋል።

አዋጁ የቤት አከራይ ከ2 ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ እንደማይችልም ያስገድዳል።

አዋጁ ምን ይላል ?

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን የተመለከተው የአዋጁ አንቀጽ የመኖሪያ ቤት አከራዮች በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ እንዳይጨምሩ ይከለክላል።

አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።

በአዋጁ መሠረት የሚደረገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።

የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።

አከራዮች ከሁለት ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም

የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው የመያዝ ግዴታ አለባቸው።

ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ሁለቱም ወገኖች የቤት ኪራይ ውሉ በተፈረመ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ውሉን አቅርበው እንዲረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። አዋጁን ተከትሎ የሚደረግ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም።

NB. በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ አካል ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡ #HoPR #ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ #አጽድቋል። ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል። አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው። የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት…
#Ethiopia

የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በዛሬው እለት ጸድቋል።

ስለ አዋጁ ...

➡️ በልማድ ሲከበር የቆየውን " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ #አስቀርቷል፡፡ 

➡️ የሰማዕታትን ቀን ( #የካቲት_12 ) እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ( #ህዳር_29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ #ታስበው ይውላሉ።

➡️ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ፣ የሰንደቀ አላማ ቀን ፣ የሴቶች ቀን ፣ የአፍሪካ ቀን ሌሎችም ታስበው ይውላሉ።

➡️ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይከበራል።

➡️ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ ያለባቸው ተቋማት ዝርዝር ተቀምጧል።

በዚህም  ፦
° የውሃ
° የመብራት
° የስልክ
° ሚዲያዎች (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ)
° የጤና ተቋማት እና መድሃኒት ቤቶች
° መከላከያ
° ፖሊስ
° ደህንነት
° የእሳት አደጋ መከላከል
° የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች
° ነዳጅ ማደያዎች
° ሙዝየሞች ፣
° ፓርኮች ክፍት ሆነው ከሚውሉት ውስጥ ናቸው።

ስለ አዋጁ ምን ጥያቄ ተነሳ ?

አንድ የምክር ቤት አባል ፦

" የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ተከብረው ከሚውሉት በዓላት ለምን አልተካተተም ? ለምን ታስቦ ከሚውል ውስጥ ተካተተ ? ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ነች !! ታስቦ ይውላል እና ተከብሮ ይውላል የሚለው የተለያየ አጀንዳ አለው " የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር።

የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ከኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ አንድ በዓል እንዲከበር እና ታስቦ እንዲውል የሚያደርገው የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ተጠንቶ ነው ብለዋል፡፡

" ኢኮኖሚያችንስ ? " ሲሉ የጠየቁት ወ/ሮ ወርቀሰሙ " ሁል ጊዜ ስራ እየዘጋን ፤ በዓል እያከበርን መዋል በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ ጫና አለ። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች በዓል ታስቦ የሚውል በተለያዩ ነገሮች ደምቆ የሚውል ሊሆን ይችላል በሚል ነው በታሳቢነት እንዲቀጥል የተደረገው " ሲሉ አስረድተዋል።

#ShegerFM #TikvahEthiopia #HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበው 236.7 ቢሊዮን  ብር ነው። አጠቃላይ የ2017 በጀት (971.2 ቢሊዮን) በ2016 በጀት ዓመት ከጸደቀው የወጪ በጀት አንጻር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው  ተገልጿል። ዛሬ ከሰዓት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ምክር…
#ብር #ዶላር

የፌዴራል መንግሥት #የ2017_በጀት ሲዘጋጅ ብርን ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሬ ተመን #የሚያዳክም ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል በሚል ታሳቢነት እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለተወካዮች ም/ ቤት ተናግረዋል።

በኢ-መደበኛው እና በባንኮች በሚደረግ ይፋዊ ምንዛሬ (official exchange) መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ እርምጃን አስመልክቶ  " ምንም የቀረበ ነገር የለም "  ብለዋል።

አቶ አህመድ ፥ የፌዴራል መንግሥት በጀት የተዘጋጀው " የነበረው አካሄድ #እንደሚቀጥል ታሳቢ ተደርጎ " ሲሉ ገልጸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ " ዘንድሮ የነበረውን ይፋዊ የውጭ ምንዛሬ መጠን (official exchnage rate) ታሳቢ አድርጎ ነው በጀቱ የቀረበው " ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህን ማብራሪያ የሰጡት በም/ቤቱ የኢዜማ ተወካይ ዶ/ር አብርሃም በርታ ፥  " ህጋዊውን እና ኢ-መደበኛውን የውጭ ምንዛሬ ገበያ እኩል ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች እንዳሉ ከአንዳንድ ወገኖች እየሰማን ነው ፤ ... የውጭ መንግስታት #በብድር_ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር ይህንኑ ለማስፈጸም እንደሚንቀሳቀሱ የሚገልጹ መረጃዎችም አሉ ፤ እንዲህ አይነቱ እርምጃ የማንወጣው ችግር ውስጥ ይከተናል የሚል የባለሙያዎች ትንታኔ አለ " በማለት ላነሱት ሀሳብ ነው።

#EthiopianInsider #HoPR #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት አዋጅ በ4 ተቃውሞ በ6 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

አዋጁ ፤ ከዚህ በፊት በልማት ተነስተው የካሳ ክፍያ ያላገኙትን እና አሁንም ድረስ እየጠበቁ ያሉ የልማት ተነሺ ሰዎችን እንደማያካትት ተሰምቷል።
 
ከምክር ቤት አባላት ምን ተጠየቀ ? ምን ምላሽ ተሰጠ ?

Q. ከዚህ በፊት በርካታ የካሳ ክፍያዎች አዲሱ የካሳ ክፍያ እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበት አዋጅ እስከ ሚፀድቅ ድረስ እንዲቆዩ ተደርገዋል ይህ አዋጅ እንዴት ሊያስተናግዳቸው አስቧል ?
 
Q. ካሳ የመክፈሉ ኃላፊነት ለክልሎች በአዲሱ አዋጅ መስጠቱ ለሰራተኞቻቸው እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልቻሉ ክልሎች ባሉበት ሰዓት እንዴት እንዲህ አይነት ክፍያ ሊከፍሉ ይችላል ?

Q. አንዳንድ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በተመለከተ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት መስጠቱ አግባብነት የለውም። ይህ እንዴት ሊታይ ታስቦ ነው ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ችግሮችን ለማየት ስልጣን የተሰጠው ?


ሌላው ፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ ይፈፀም የነበረው በክልሎችና በወረዳዎች በሚጣሉ የካሳ ተመኖች ነበር አዋጁ ይህ እንዲባባስ ሊያደር ይችላል የሚል ስጋት ተነስቷል።
 
በተ/ም/ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፥ ከዚህ በፊት ከልማት ጋር በተያያዘ ያልተከፈሉ ክፍያዎች የሚዳኙት በቀድሞ አዋጅ መሰረት ነው ብለዋል።

አዲሱ አዋጅ የሚመለከተው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ያሉ የካሳ ክፍያዎች ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
 
በክልሎች ያለው በጀት ጉድለት እንዳለ ሆኖ ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው የፌደራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው የበጀት ድጎማ እንደሆነ ተመላክቷል።

በክልሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ለክልሎች የሚመደበው በጀት ላይ የካሳ ክፍያ ታሳቢ ይሆናል።
 
ከዳኙነቱ ጋር በተያያዘም ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሌላኛው የቋሚ ኮሚቴ አባል ፤ " ውሳኔውን ለመስጠት የተፈለገው ልማቶች ሲካሄዱ ፈጣን ፍርድ ለማሰጠትና ሀብትን ከምዝበራ ለመታደግ በማሰብ ነው " ብለዋል።

#ShegerFM
#HoPR
 
@tikvahethiopia
#HoPR

ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል።

በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ  ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#HoPR

" ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦

" ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ።

ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና ለመዋጋት ብሔራዊ የጸረሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ብንሰማም አርቂ ስራ ሲሰራም ሆነ በሙስና ምክንያት ያንዣበበውን ሀገራዊ አደጋ ለመቀልበስ እርባና ያለው ስራ ሲሰራ አልታየም።

በአጠቃላይ መንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ይሄ ነው የሚባል መፍትሄ እየሰጠ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም ላይ ጥያቄ ይነሳል።

ምክንያቱም የህዝብ እና የመንግስት ሀብት በዘረፉ ሙሰኛ ባለስልጣናት ላይ መቀጣጫ የሚሆን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ተጨማሪ ሹመት እና የቦታ ዝውውር በመስጠት መንግስት ሙሰኞችን አብሮ አቅፎ ይኖራል ማለት ይቻላል።

ከዚህ የተነሳ ፦

የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል።

ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል።

ዜጎች የዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በአደባባይ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው።

ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከሀገር ወጥቶ እየሸሸ ነው።

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት እያባከኑ ነው።

በኦዲት ሪፖርት መሰረት በየመ/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ይታያል።

መ/ቤቶች ገንዘብ ያለማስረጃ ወጪ በማድረግ ይጠቀማሉ ፣ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ በወጪ ይመዘግባሉ፣ ከፋይናንስ መመሪያና ደንብ ውጭ የገንዘብ ክፍያ ይፈጸማል።

እንደሚታወቀው ብዙ ሀገራት ለችግሩ በሰጡት ትኩረት የማያወላውል እርምጃ ስለወሰዱ ችግሩን ማቃለል ችለዋል።

ለምሳሌ በቅርቡ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ለልምድ ልውውጥ የጎበኟቸው የእስያ ሀገራት እነ ሲንጋፖር ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ስንመለከት ለእድገታቸው ዋናው መሰረት በሙስና ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ነው።

በሀገራችን የሌብነት ችግር ለመቅረፍ አፋጣኝ እና አስተማሪ የሚሆን እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር የጸረ ሙስና ህጋችንን አሻሽለን ቢሆን በሀገራችን አሁን የምናያቸው ፈተናዎች ተደምረው ሙስና የሀገራችንን ህልውና መፈተኑ አይቀርም።

ክቡር ጠ/ሚኒስትር በህዝቡ የሚቀርበው ተደጋጋሚ ቅሬታና የጄነራል ኦዲተር መ/ቤት በማስረጃ አስደግፎ ያቀረበልን ስር የሰደደ የሙስናን ችግር ለመቅረፍ መንግስትዎ ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ?

በተደጋጋሚ እንደታዘብነው ቃል ከመግባት ባለፈ ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቧል ?

ህዝቡስ ከመንግስትዎ ምን ይጠብቅ ? "

#Ethiopia

@tikvahethiopia