TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Lebanon

እንደ ሌባኖስ ጤና ሚኒስቴር መረጃ #በሌባኖስ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች መካከል ስምንት (8) ኢትዮጵያዊያን ይገኙበታል።

በቤይሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ግን ስለተጠቀሰው አሃዝ ከአገሪቱ መንግሥት የተሰጠው መረጃ #እንደሌለ ለቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ተናግሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ https://telegra.ph/BBC-05-16-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ለ1 አመት ያህል ትምህርት በርቀት እንዲሆን ወሰነ!

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

በዓለም ላይ ካሉት እውቅ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ለአንድ (1) አመት ያህል በክፍል ውስጥ የሚኖር ትምህርት #እንደሌለ አስታውቋል።

ሆኖም ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉም ትምህርቶች በ 'ኦንላይን' የሚሰጡ ሲሆን " ከተቻለም የተወሰኑ ተማሪዎችን በቡድን አንድ ቦታ ላይ በማድረግ መማር የሚችሉበትን መንገድ ልናመቻች እንችላለን ብሏል።

ዩኒቨርስቲው 'ይህ መሆን የሚችለው ግን ጥቂት ተማሪዎች ቢሆኑም አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ ሲችሉ ነው' በማለት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
" የምግብ ችግሩ የከፋ ነው "

ከትግራይ አዋሳኝ በሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች " አበርገሌ " እና " ፃግብጅ " ተፈናቅለው በዋግኽምራ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች በምግብ እጦት ምክንያት በተለያዩ በሽታዎች እየተጠቁ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይ ነፍሰጡር እናቶች እንዲሁም እናቶች በምግብ እጦት ለበሽታ እየተጋለጡ ሲሆን ለሁለት ዓመታት በዋግኽምራ ዞን ሲቆዩ ከተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እርዳታ እያገኙ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች እርዳታ እየመጣ አይደለም ተብሏል።

ነፍሠጡር እናቶች ፣ የሚያጠቡ እናቶች እና ህፃናት በሳምባ ምች እና በተቅማጥ በሽታ እየተያዙ መሆኑ ተመላክቷል።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ለተፈናቃዮች የሚቀርብ የምግብ ድጋፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ የውሃ አቅርቦት፣ መድሃኒት በመቋረጡ / እንደ በፊት ባለመሆኑ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው ብሏል።

" ዜጎች በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ " ያለው መምሪያው በተለይም የምግብ ችግሩ የከፋ ነው " ሲል አሳውቋል። በምግብ እጥረቱ ሳቢያ እንዲሁም በውሃ አቅርቦት አለመኖር ዜጎች ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆናቸውን ገልጿል።

ጤና መምሪያው መሰረታዊ የህክምና አገልግሎቶች እየሰጠ የተፈናቃዮችን ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ጠቁሞ በህፃናት ላይ የሚታየው የሳንባ ምች እና የተቅማጥ በሽታ ለመከላከል የሚያስፈልጉ መድሃኒቶች ከፍተኛ እጥረት መኖሩን ጠቁሟል።

ከምንም በላይ ግን የምግብ አቅርቦቱን ማስተካከል ካልተቻለ ያለውም ችግር መቅረፍ እንደሚያጋግት ጠቁሟል።

#ምግብ_እጦት ጋር በተያያዘ ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ የተጠየቀው የጤና መምሪያው ፤ #በቀጥታ በረሃብ የሞተ ሰው #እንደሌለ ነገር ግን #ረሃብ ለሌሎች በሽታዎች ስለሚያጋልጥ በሌሎች ህመሞች የመሞት እንድል እንዳላቸው አመልክቷል።

የጤና መምሪያው መንግስት በዋግኽምራ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች ትኩረት እንዲሰጥ ፣ አጋር ድርጅቶችም ከዚህ በፊት ሲያደርጉ የነበረውን የመድሃኒት ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና ሌሎች ድጋፎች እንዲቀጥሉና ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቋል።

በተጨማሪ የሰላም ስምምነት ከተፈጠረ አካባቢው ነፃ መሆን አለበት ነዋሪዎችም ወደ ቀደመው ቄያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ እና እንዲደገፉ የማድረግ ስራ መንግስት ሊሰራ ይገባ ተብሏል።

መረጃ ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ።

@tikvahethiopia
" ለ ' ህወሓት' የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ለ "ህወሓት" እውቅና ስለ መሰጠቱ የሚሰያጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይም በፌስቡክ ለ " ህወሓት " እውቅና ስለመሰጠቱ #ሀሰተኛ_መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን በተደረገ ቅኝት ማየት መቻሉን የገለፀ ሲሆን ለ " ህወሓት " የተሰጠ እውቅና #እንደሌለ ቢሮው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው እለት ፦
- ለወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ለኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ
- ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ለተባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አሳውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለ "ህወሓት" እውቅና ተሰጠ ተብሎ የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ ፥ መረጃውን የእውነት ለማስመሰል እየተደረገ ያለ ሙከራ መሆኑን የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያስረዳ ሲሆን " ለህወሓት የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " ብሏል። 

ማንኛውም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን የተመለከተ መረጃ በቦርዱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እስካልወጣ ድረስ መረጃዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውንና ቦርዱን የማይወክሉ መሆኑን እንዲታወቅልኝ ሲል ቦርዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia