TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሀገር አፍራሾች‼️

በማህበራዊ ሚዲያ #ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ህዝብን #የምታሸብሩ አካላት ከዚህች ምስኪን እና ድሃ ሀገር ላይ እጃችሁን አንሱ። ከአስነዋሪ ድርጊታችሁ ተቆጠቡ። መንግስት በማህበራዊ ሚዲያ ህዝብን ለማቃቃር እና በሀሰተ ኛ እና ባልተረጋገጠ መረጃ ለመረበሽ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን እንዲሁም ቡድኖችን (ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ የሚያንቀሳቅሱ) አካላት ላይ #የማያዳግም እርምጃ ሊውስድ ይገባል።
.
.

እንያንዳዱ የፌስቡክ ተጠቃሚ የተደበቀ #ይመስለዋል እንጂ ከመንግስት እይታ ውጭ አለመሆኑ ግልፅ ነው። የሀገሪቱ መንግስት እያንዳንዱ የጥላቻ እና የሀሰት መረጃ የሚያሰራጩ እና ህዝብን ከህዝብ ለማቃቃር የሚጥሩ አካላት ላይ ለሌላው አስተማሪ የሆነ #ቅጥት ሊቀጣ ይገባል።

ሰላም፤ ፍቅር፤ አንድነት!
ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech🔝

TIKVAH-ETH ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር #በመተባበር እያደረገ የሚገኘው የStop Hate Speech እንቅስቃሴ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት #የሁለተኛው_ቀን መድረክ ተካሂዷል። በዛሬው እለት ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች መካለል አቶ #እሸቱ ተገኝተው መልዕክት አተላልፈዋል። አቶ እሸቱ እንደተናጋሩት ተማሪዎች ከየትኛውም አይነት #የጥላቻ_ንግግር እና አንደንዛዥ አስተሳሰቦች #ሊርቁ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን ላይክ እና ሼር ባለማድረግ ለሀገራቸው #ሰላም ዘብ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፤ ከዚህ ባለፈም ስለግቢያቸው #ሀሰተኛ መረጃ ሲሳራጭ #ሲመለከቱም እውነታውን መፃፍና እውነቱን ብቻ ማጋራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። አቶ እሸቱ ከወራት በፊት በግቢው በተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ የተፈጠረውን ክስተት አንስተው ተማሪው እውነቱን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

•በዛሬው ምሽት ቆይታ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በአካል ተገናኝተው አጭር ቆይታ አድርገዋል፤ በርካታ ስራዎችን በቀጣይ ለመስራትም አጭር ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም TIKVAH-ETH በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንደ ማህበር የሚቋቋምበት መንገዶች ላይ በቀጣይ ሰፊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

ምሽቱ ልክ እንደትላንቱ #በትሩ_ላይፍ የኪነ ጥበብ ቡድን ታጅቦ አልፏል። #TrueLife

በነገው ዕለት የ3ኛውና የመጨረሻው ቀን መድረክ የሚኖር ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፋሉ።

በቀጣይ፦

አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech
#TIKVAH_ETH

ፎቶ፦ @odansiif (ዱሬሳ-TIKVAH-ETH)

የሀሳቡ ደጋፊዎች፦ 0919 74 36 30

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_መረጃ፡ ድምፃዊ አበበ ተካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_መረጃ:ኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ራሱን #አገለለ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው። ክለቡ እስካሁን ራሴን ከሊጉ #አላገለልኩም ብሏል።

Via #ቴዎድሮስ_ታከለ/ሶከር ኢትዮጵያ/
@tikvahethsport
ሌላው ደግሞ ይህ ደብዳቤ ሀሰተኛ ነው!

/#Fake/

ንግድ ባንክ የሰጠው ማሳሰቢያ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቋቋም ላይ ከሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አክሲዮን ግዥ ፍላጎት ያለው መሆኑን የሚገልፅ #ሀሰተኛ_መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ይገኛል።

የባንኩ ዓላማ አገልግሎቶችን በማስፋፋይና በማሳለጥ ህዝቡን ማገልገል ብቻ እንጂ ከሌሎች የፋይናስ ተቋማት ጋር የአክሲዮን ትስስር መፍጠር አለመሆኑን ለመግለፅ ይወዳል። ስለዚህ በፕሬዘዳንቱ ተፃፈ የተባለው ደብዳቤ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን እየገለፅን ወደፊትም ባንኩን አስመልክቶ የሚወጡ ማናቸውም መረጃዎች በባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ብቻ የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_መረጃ

የመቐለ ጊዜያዊ ከንቲባ የነበሩት አቶ አታኽልቲ አዲስ ሹመት እንደተሰጣቸው ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰተኛ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።

አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ ፥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን አዲስ ሹመት ስለማግኘታቸው የተሰራጨው ዜና #ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል።

የቀድሞው ጊዜያዊ ከንቲባ ፥ "አሁን የመቐለ ነዋሪ ብቻ ነኝ ሲሉ" አስረድተዋል።

ምንጭ፦ www.addiszeyeb.com

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት "የምርጫ ወቅት እና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት" ላይ ትኩረቱት ያደረገ አጭር ገለፃ በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ይኖረናል። ገለፃው በዋነኝነት በዚህ ለሀገሪቱ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ሊፈጠር የሚችለውን ችግር በማስቀረቱ ረገድ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን። አቅራቢዎቹ : ከመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል…
Audio
AudioLab
#ሀሰተኛ_መረጃ_እና_ምርጫ2013

"የምርጫ ወቅት ላይ ስለሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና እንዴት እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንችላለን" በሚለው ጉዳይ ዛሬ በቀጥታ Voice Chat ለቲክቫህ ቤተሰቦች ገለፃ ተደርጓል/ለጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል።

ገለፃና ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ከCARD በፍቃዱ ኃይሉ ፤ ከኢትዮጵያ ቼክ ደግሞ ኤልያስ መሰረት ነበሩ።

ምናልባት በቀጥታ በVoice Chat ገለፃውን ማዳመጥ ሳትችሉ የቀራችሁ ቤተሰቦቻችን ከላይ የድምፅ ቅጂው ተያይዟል፤ አዳምጡት።

@tikvahethiopia
#Update

"በደሴ 10 በሚሆኑ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ተሞልተው ተገኙ" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

በ10ሩ የምርጫ ጣቢያዎች የተፈጠረውን ጉዳይም ዛሬ በነበራቸው መግለጫ አስረድተዋል።

በምርጫ ጣቢያ ደረጃ የውጤት አገላለፅ እንዲሁም የውጤት አመዘጋገብ በትክክለኛው መንገድ ስለመፈፁ የሚረጋገጥበት የራሱ ደረጃ አለው ይህም በስልጣና ላይ ተሰጥቷል ብለዋል።

ከእንዚህ ደረጃዎች/ሂደቶች መካከል ፦
- የመጀመሪያው በዚያ ጣቢያ ስንት ሰው ነው የሚመዘገበው ?
- በዕለቱ መጥቶ መዝገብ ላይ ፈርሞ ድምፅ የሰጡ ብዛት ስንት ናቸው ? ፊርማቸው ተቆጥሮ መመዝገብ አለበት።
- የመጡት ሰዎች ተመዝግበዋል ከተባሉት ሰዎች ቁጥራቸው መበላለጥ ስለሌለበት ይህም ይረጋገጣል።
- የደረሰው የድምፅ መስጫ ወረቀት ብዛት ስንት ነው ?
- ሳጥን ውስጥ የተገኘው ምን ያህል ነው ?
- የተበላሸ የድምፅ መስጫ ወረቀት ስንት ነው ? የሚሉት ይገኙበታል።

ደሴ የተገኙት 10 ምርጫ ጣቢያዎች ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጡ አካሄዶችን ሳይፈፅሙ ፣ ሂሳቡንም በትክክል ሳይሰሩ በመላካቸው በምርጫ ክልል ደረጃ እንደገና መታየት ስላለበት / ድምፅ ቆጠራው መደገም ስላለበት የምርጫ ክልሉ ለጊዜው ኳራንታይን አድርጎ አስቀምጦታል።

ይህ ሁኔታ ነው የማይሆን ትርጉም ተሰጥቶት #ሀሰተኛ_መረጃ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው ሲሉ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
" የትኛው ፖሊስ ጋር ነው ያመለከቱት ? ፌክ ኒውስ በጣም በብዛት እያሰራጩ ነው " - የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በታጣቂዎች እገታዎች ተፈፅመው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚጠየቅ በተደጋጋሚ መገለፁ ይታወቃል።

በቅርቡ አንድ ሰዓሊ ከጓደኛው ጋር ሶደሬ አካባቢ ከታገተ በኃላ ቤተሰቦቹ ጋር ተደውሎ ገንዘብ ከተጠየቁ በኃላ ለመነጋገር ድጋሚ ሲደውሉ " በእሱ ጉዳይ አትደውሉልን አፈር አልብሰነዋል " የሚል መርዶ ተነግሯቸው ሀዘን ላይ እንደነበሩ ፤ ጓደኛው ግን 500 ሺህ ብር ከፍሎ ከእገታ መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህ ክስተት በፊትም የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ከመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸውን መግለፃችን ይታወሳል።

እኚህን ባለስልጣን ያገቷቸው ታጣቂዎች 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸው መነገሩም አይዘነጋም።

ወደ ጎጃም መስመር " ዓሊዶሮ " ላይም 30 ሹፌሮች እና ረዳቶች በታጣቂዎች መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው መግለፃቸው ፤ ከታገቱት ውስጥም 500 ሺህ እና 1 ሚሊዮን ብር ቤተሰቦቻቸው ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው መግለፃችን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

እንደውም ከቀናት በፊት ልጃቸውን ከእገታ ለማስለቀቅ 1 ሚሊዮን ብር የከፈሉ አሳዛኝ መምህር ታሪክ መሰራጨቱ ይታወሳል።

ወራትን ወደኃላ ብንጓዝ በርካቶች እየታገቱ ገንዘብ ተጠይቆባቸው ለአጋቾች ተከፍሎ ተለቀዋል ፤ በርካታ ሚዲያ ላይ ያልቀረቡ መሰል ክስተቶች አሉ።

ከታጋች ቤተሰቦች እንደሚሰማው ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ቢወስዱት አጋቾች የያዙትን ሰው ህይወት ያጠፋሉ የሚል ስጋት አለ ፤ ከዛ ውጭ ግን ጉዳዩን ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ዛሬ በነበረው የፓርላማ ውሎም የምክር ቤት አባላት የእገታ ጉዳይን አንስተው አሳሳቢነቱን ገልጸዋል። ለጠ/ሚኒስትሩም ጥያቄ አቅርበዋል።

ይህንን የእገታ ጉዳይ በተመለከተ ዶቼ ቨለ ሬድዮ አንድ አጭር ዘገባ አሰራጭቶ የተመለከትን ሲሆን በዚሁ ዘገባ ላይ የነዋሪዎች / አሽከርካሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ ቃል ይገኝበታል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ አሽከርካሪ ፤ ጅቡቲ ኮሪደር ላይ እስካሁን ከነበረው አሁን ላይ መሻሻል እንዳለ፤ መንግሥት ከፍተኛ ሰራዊት መድቦ ከወለንጪቲ እስከ መተሃራ በፌዴራል እና መከላከያ የሚጠበቅ ቀጠና መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ትልቁ ችግር ያለው ከፍቼ - ጎሃ ፂዮን ያለው ቀጠና ነው ብለዋል።

አንድ የአ/አ ነዋሪ ደግሞ ከእገታ ጋር በተያያዘ 3 ዓይነት ሰዎች አሉ ፤ እራሳቸው ሳይታገቱ " ታግተናል " በሚል ለፖለቲካም ሆነ ለሌላ አላማ የሚጠቀሙ ፣ የገንዘብ ፍላጎት ኖሯቸው የሚንቀሳቀሱ አሉ እነዚህ ገንዘብ ያላቸውን ፣ ቢዝነስ ውስጥ ያሉ ሰዎችን አጥንተው የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፤ በረሃ ላይ አሸከርካሪዎችን የሚያግቱም አሉ እነዚህም ገንዘብ ይጠይቃሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ልጅም " ታገትኩ " ብሎ አባቱን ገንዘብ የሚያስጠይቅም አለ እውነቱን ለማወቅ አቸጋሪ ጊዜ ነው ነገሩ ሁሉ ውስብስብ ነው ሲሉ አክለዋል።

የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ግን የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ መሆኑን ገልጸው አሽከርካሪዎችም ሆኑ ሌሎች ከታገቱ የት ፖሊስ ጣቢያ ሄደው እንዳመለከቱ መረጃ ሊጣራ ይገባል ብለዋል።

አቶ ጄይላን ፤ " የትኛው ፖሊስ ጋር ነው ያመለከቱት ? ፌክ ኒውስ በጣም በብዛት እያሰራጩ ነው ፤ ፌዴራል ፖሊስ መንገድ ላይ እዛው አመልክተዋል ወይ ? ሆን ተብሎ ፌክኒውስ ሀገሪቱ ላይ ሰላም እንደሌለ ለማስመሰል ፤ፌክኒውስ እየተሰራጨ ነው ያለው ሰው ታግቷል ተብሎ " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተሽከርካሪዎች_ጨረታ_ጉምሩክ_ኮሚሽን_አዳማ_.pdf
ውዝግብ የፈጠረው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ !

" ' የጉምሩክ ኮሚሽን ' የገንዘብ ሚኒስቴርን ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን " - ከሰደት ተመላሾችና 10 የሚደርሱ የአገር ውስጥ አስመጪዎች

" በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ በተከተለ መልኩ ነው። ' ህጋዊ ስርዓቱን አልተከተለም ' በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ፤ #ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ እንጠይቃለን " - ጉምሩክ ኮሚሽን

ከሰሞኑን የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ያወጣው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ውዝግብ የፈጠረ ሆኗል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ከሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ፤ " ጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔን በመጣስ 237 ተሽከርካሪዎች ለሐራጅ አወጣብን " በሚል ከሰዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ፤ " ምንም አይነት የህግ ጥሰት አልፈተፈፀም ህጉን እና አሰራሩን በተከተለ መልኩ ነው ተሽከርካሪዎቹ ለጨረታ የቀረቡት " ሲል አሳውቋል።

ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-24

@tikvahethiopia
" ለ ' ህወሓት' የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ለ "ህወሓት" እውቅና ስለ መሰጠቱ የሚሰያጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይም በፌስቡክ ለ " ህወሓት " እውቅና ስለመሰጠቱ #ሀሰተኛ_መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን በተደረገ ቅኝት ማየት መቻሉን የገለፀ ሲሆን ለ " ህወሓት " የተሰጠ እውቅና #እንደሌለ ቢሮው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው እለት ፦
- ለወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ለኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ
- ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ለተባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አሳውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለ "ህወሓት" እውቅና ተሰጠ ተብሎ የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ ፥ መረጃውን የእውነት ለማስመሰል እየተደረገ ያለ ሙከራ መሆኑን የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያስረዳ ሲሆን " ለህወሓት የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " ብሏል። 

ማንኛውም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን የተመለከተ መረጃ በቦርዱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እስካልወጣ ድረስ መረጃዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውንና ቦርዱን የማይወክሉ መሆኑን እንዲታወቅልኝ ሲል ቦርዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia