TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስት በጉባኤው አባላት በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል። ዛሬ ጠዋት በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ በጀመረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-መንግስት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባኤ የቀረበው ረቂቅ ህገ-መንግስት በ10 ተቃውሞ በ2 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  ረቂቅ ህገ-መንግስቱ 11 ምዕራፎች፣ 141 ዋና ዋና አንቀጾች…
#Update

የቀድሞው የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ከበደ " ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "ን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ ተሾሙ።

የ44 ዓመቱ ገልማሳ አቶ ጥላሁን ከዚህ ቀደም ፦
- በሃዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የጤና ጣቢያ ኃላፊ፣
- በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን የውባ ደብረፃይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣
- በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን ንግድ እና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ፣
- በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን የድርጅት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፣
- የቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፣
- በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የግብርና እና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እንዲሁም የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ
- የደቡብ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነው መስራታቸው ተገልጿል።

አመራሩ በትምህርት ደረጃቸው በከተማ ልማት አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም በተመደቡበት ቦታ ህዝባቸውን #በንፅህና በእኩልነት የመሩ ናቸው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ።

ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው።

በዚህም መሠረት :-

- የም ዞን

- ምስራቅ ጉራጌ ዞን

- ጠምባሮ ልዩ ወረዳ

- ቀቤና ልዩ ወረዳ

- ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል በሞሽኑ ቀርቦ ፀድቋል።

የምክር ቤቱ ጉባኤም ተጠናቋል፡፡

መረጃው የደ/ሬ/ቴ/ድ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ትላንት ለስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ / አዲስ አበባ የመጡት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ሄደዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ። ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው። በዚህም መሠረት :- - የም ዞን - ምስራቅ ጉራጌ ዞን - ጠምባሮ ልዩ ወረዳ - ቀቤና ልዩ ወረዳ - ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው…
#NewsAlert

የደቡብ ኢትያጵያ ክልላዊ መንግስት አዲስ ዞን እና የወረዳ አስተዳደር መዋቅርን ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- የአማሮ ፣ የደራሼ ፣ የባስኬቶ፣ የቡርጂ፣ የአሌ ልዩ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው እራሳቸውን ችለው #በዞን ይደራጃሉ።

- በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ እንዲደራጅ ተወስኗል።

- የደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ዞን እንዲደራጅ ተወስኗል።

• ከደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ፣ የሐመር፣ የበና ጸማይ ፣የሰላማጎ፣ የኛንጋቶም የዳሰነች ወረዳ እና የቱርሚ ከተማ አስተዳደር በጋራ #በዞን የሚደራጁ ይሆናል።

• ከደቡብ ኦሞ ዞን የደቡብ አሪ፣ የወባ አሪ የባካ ዳውላ ፣ የሰሜን አሪ ወረዳዎች እንዲሁም የጂንካ ከተማ አስተዳደር እና የገሊላ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በጋራ ሆነው #በዞን ይደራጃሉ ተብሏል።

መረጃ የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
ቴሌግራም ላይ በኮፕ ቻፓግራም https://t.iss.one/ChapagramBot የግብይት ክፍያ መፈፀም ተቻለ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በ " ደቡብ ኢትዮጵያ " እና በ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ " ክልሎች ምስረታ ጉባኤ ላይ የተደረጉ ሹመቶችን በተመለከተ ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
" ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት ተነጋግረን ወርቅ ፣ ብር እና ነሀስ እንዲመጣ እናደርጋለን " - አትሌት ለተሰንበት ግደይ

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራችን በሴቶች 5000 እና 10,000 ሜትር ረጅም ርቀት ውድድር ሁለቱም የወርቅ ሜዳሊያ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ (10,000 ሜትር) እና ጉዳፍ ፀጋይ (5000 ሜትር) መገኘት ችሎ ነበር።

ሁለቱም አትሌቶች አምና ሀገራችን በርቀቱ ላስመዘገበችው ደማቅ ውጤት አስቀድሞ በሜዳ ላይ የተሰራው የቡድን ስራ ትልቅ ሚናን እንደተጫወተ ገልጸዋል።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ፥ " በውድድሩ ማንም እንዲያሸንፈን አልፈቀድንም ፤ እኔም መርቼ ቢሆንም ለሀገራችን ወርቁ እንዲመጣ ነበር ፣ ከውድድሩ በፊት እኔ ፣ ጉዳፍ እና ዳዊት ተነጋግረን ገብተን ነበር " ብላለች።

ተነጋግረን የነበረው " ተጋግዘን ወርቁን ለሀገራችን እናምጣው " በሚል ነበር ያለችው ለተሰንበት ፤" በመነጋገራችን እና በቡድን በመስራታችን የፈልገነውን ነገር አሳክተን ወጥተናል " ስትል አስታውሳለች።

ዘንድሮስ ?

አትሌት ለተሰንበት በዛሬው ውድድር ላይም " ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት ተነጋግረን ወርቅ ፣ ብር እና ነሀስ እንዲመጣ እናደርጋለን " ብላለች።

በውድድሩ ላይ ሊገጥም ስለሚችለው ፉክክር ሀሳቧን ያካፈለችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በበኩሏ ፤ " የተፎካካሪዎቻችን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ማወቅ ያስፈልገናል " ብላለች።

አትሌት ሲፋን ሀሰን ጠንካራ ተፎካካሪ ልትሆን እንደምትችልም አልሸሸገችም።

" የተሻለ ውጤት ለማምጣት ስራ መስራት ያስፈልጋል ፣ ጠንክራ ስራ ይጠብቀናል ትልቁ ሚስጥር ይሄ ነው " ስትል ጉዳፍ ተናግሯለች።

ምሽት 3:55 ሲል በሚጀምረው የሴቶች 10,000ሜትር ውድድር ሀገራችን ፦
- በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ፣
- በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ፣
- በአትሌት እጅጋየሁ ታዬ
- በአትሌት ለምለም ሀይሉ የምትወከል ይሆናል።

ድል ለሀገራችን !

More 👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት ተነጋግረን ወርቅ ፣ ብር እና ነሀስ እንዲመጣ እናደርጋለን " - አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራችን በሴቶች 5000 እና 10,000 ሜትር ረጅም ርቀት ውድድር ሁለቱም የወርቅ ሜዳሊያ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ (10,000 ሜትር) እና ጉዳፍ ፀጋይ (5000 ሜትር) መገኘት ችሎ ነበር። ሁለቱም አትሌቶች አምና ሀገራችን በርቀቱ ላስመዘገበችው…
ተጀመረ !

በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ10,000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል።

ሀገራችን ፦

- በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ፣
- በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ፣
- በአትሌት እጅጋየሁ ታዬ
- በአትሌት ለምለም ሀይሉ ተወክላለች።

ውድድሩን በብሔራዊ ቴሌቪዥን መዝናኛ ቻናል እንዲሁም በDSTV 226 ላይ መመልከት ይቻላል።

ድል ለሀገራችን !
ድል ለአትሌቶቻችን !

@tikvahethiopia