TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስት በጉባኤው አባላት በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል።
ዛሬ ጠዋት በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ በጀመረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገ-መንግስት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባኤ የቀረበው ረቂቅ ህገ-መንግስት በ10 ተቃውሞ በ2 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁ ተነግሯል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረቂቅ ህገ-መንግስቱ 11 ምዕራፎች፣ 141 ዋና ዋና አንቀጾች እና በርካታ ንዑሳን አንቀፆች አሉት ተብሏል።
ከዚህ ባለፈ ፥ 32 ብሔሮችና ብሔረሰቦች ይኖሩበታል የተባለው ይኸው ክልል የመወከልበት ሰንደቅዓላማ ለጉባኤው አባላት ቀርቦ ተዋውቋል።
በሌላ በኩል ፤ የደቡብ ብሔር-ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ህገ-መንግስትን በማሻሻል በአዲስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለሚደራጀው ክልል የተዘጋጀው ረቂቅ የህገመንግስት ሰነድ በወልቂጤው ጉባዔ ላይ ፀድቋል።
የህገመንግስት ሰነዱ በ5 ተቃውሞ፣ በ3 ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁን ነው ለማወቅ የተቻለው።
@tikvahethiopia

" ሸኔ ነሽ " በሚል ሴት የደፈረው የፖሊስ አባል 7 ዓመት እስር ተፈረደበት።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን፤ ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ ውስጥ የፖሊስ አባል የሆነ ግለሰብ (ስሙ ፦ ኮንስታብል ገነሜ ኮንሶ) አንዲት ሴትን ‘ሸኔ’ ነሽ ብሎ በማስፈራራት በመድፈሩ የ7 ዓመት እስር ተፈረደበት።
ይህን በተመለከተ ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ በዳኔ ደንቦቢ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል።
ዳኛ በዳኔ ደንቦቢ ምን አሉ ?
" የግል ተበዳይ (ስሟን ለመጠበቅ አልተገለፀም) ፤ ወንጀሉ የተፈጸመባት ደምቢ ሶሮ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ሐምሌ 04/2015 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡30 ላይ ከሌላ ሴት ጋር ከቤቷ በወጣችበት ወቅት ነው።
የግል ተበዳይዋ ከሌላ ሴት ጋር ሆና ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው መጸዳጃ ቤት ጋር ሲደርሱ በስፍራው የነበረው ተከሳሽ የፖሊስ አባል ያስቆማቸዋል።
በዚህ ለሊት ወደየት ነው የምትሄዱት ? በምሽት መንቀሳቀስ ክልክል ስለሆነ የቅጣት 200 ብር አምጡ በማለት የመድፈር ወንጀሉን ከመፈጸሙ በፊት ገንዘብ ለመቀበል ሙከራ አድርጎ ነበር።
ሁለቱ ሴቶች ገንዘብ እንደሌላቸው ሲመልሱለት ‘ኦነግ ሸኔ’ ናችሁ የሚል ሌላ ክስ ማቅረብ ጀመረ።
ለቅጣት ያለውን ገንዘብ እንደማያገኝ ሲረዳ ‘እናንተ ኦነግ ሸኔ ናችሁ። ኦነግ ሸኔ ያለበትን ቦታ ስለምታውቁ ከዚያ ነው የምትመጡት’ በማለት ተቆጣ። ተበዳዮቹም ሸኔ ናችሁ በመባላቸው ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ገቡ።
የጦር መሳሪያ ደቅኖባቸው ‘እገድላችኋለሁ’ ብሎ አስፈራርቶ ወደ ጢሻ ይዟቸው ገባ። ወደ ሰዋራ ቦታ ከወሰዳቸው በኋላም አንደኛዋን ‘ቁጭ በይ ድምጽሽን እንዳታሰሚ’ በማለት ካስፈራራ በኋላ፣ ባለትዳር የሆነችውን ሌላኛዋን ሴት ደፈረ።
ሚስቱ ወደ ውጪ ወጥታ የቆየችበት የተበዳይ ባለቤትም ሚስቱን ፍለጋ ሲወጣ፣ ወንጀሉ ከተፈጸመበት ቦታ ደርሶ አግኝቷታል።
ተከሳሽ ኮንስታብል ገነሜ በሱሮ ባርጉዳ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ወንጀሉን አልፈጸምኩም ብሎ ቢከራከርም፣ ለቀረበበት ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም።
የግል ተበዳይን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ምስክርነት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል።
ተከሳሽ ኮንስታብል ገነሜ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 620/1 መሠረት ጥፋተኛ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ወስኗል።
አንድ ተከሳሽ በኃይል ወይም በመሳሪያ አስፈራርቶ የመድፈር ወንጀል ከፈጸመ ከ5 አስከ 15 ዓመት እስር ያስቀጣል። ወንጀሉ ሲፈጸም በተበዳይ ላይ የደረሰ ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንደሌለ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈጽሞ እንደማያውቅ እና ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የ7 ዓመት እስር ተፈርዶበታል። "
via ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ

#Hawassa
" ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል " - አቶ አብርሃም ማርሻሎ
የሲዳማ ክልል መንግሥት የግምገማ መድረክ እያደረገ ይገኛል ተብሏል።
ታዲያ በዚሁ እየተካሄደ ባለው የግምገማ መድረክ ላይ ከተገመገሙት አመራሮች አንዱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ናቸው ተብሏል።
ከንቲባው በ " ብልሹ አሰራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " በሚል ከስልጣን ተነስተው በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑ ተነግሯል።
ከንቲባው ከስልጣን መነሳታቸውንም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ብልፅግና ፓርቲ አረጋግጧል።
ፓርቲው የከንቲባውን ከሃላፊነት መነሳት ያረጋገጠው በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ አማካኝነት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።
አቶ አብርሃም ፤ በሀዋሳ ከተማ በርካታ መሰራት ያለባቸው የልማት ሥራዎች ሳይሰሩ መቅረታቸውን ጠቅሰዋል።
በመካሄድ ላይ በሚገኘው የግምገማ መድረክ ላይ ከንቲባ ፀጋዬ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ከንቲባው ባሳዩት የሥራ ድክመት ከኃላፊነታቸው እና ከፓርቲ አባልነት እንዲነሱና በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑን አመልክተዋል።
ከንቲባውን በሚመለከት በተካሄደ ግምገማ ወቅት ፤ " አመራራቸው ደካማ ነው ፤ የአቅም ውስንነት አለባቸው ፤ ከፍተኛ ሙስና ውስጥም ገብተዋል " የሚሉ ሀሳቦች ተነስተው ነበር።
በተለይም ከተማው አስገነባሁት ካለው የመግቢያ በር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በሚዲያ 90 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት ቢነገርም በመሃንዲስ ተጣርቶ ወጪው ከ30 ሚሊዮን እንደማይዘል በግምገማ መድረኩ ላይ መነሳቱ ተሰምቷል።
ከንቲባው ስብሰባ ረግጠው ወጥተዋል በሚለው ጉዳይ ላይ ፤ እንዲሁም በግምገማው ወቅት ስለተነሳባቸው ክስ ምን ይላሉ ? የሚለውን ለማወቅ እና ምላሻቸውን ለማግኘት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ሊሳከልን አልቻለም።
ከንቲባው ብዙ ጊዜ ወቅታዊ ጉዳዮችን በሚፅፉበት የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይም የሰጡት አስተያየት የለም።
ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ምላሽ የሚሰጡ ከሆነ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።
በሌላ በኩል ፤ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን በፌስቡክ ላይ " Hawassa City Press Secretary " እና " Mayor office of Hawassa ,Sidaama " የተሰኙ ገፆች የሚያሰራጩት መረጃ እና መልዕክት ሙሉ በሙሉ የከተማው አስተዳደርን የሚወክል እንዳልሆነ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም በክልሉ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያነጋገራቸው ሰራተኞች ፣ ወጣቶች ክልሉ በሙስራ እና በብልሹ አሰራር ተዘፈቀ በመሆኑ ከታች እስከ ላይ ያለው #እንያንዳንዱ አመራር በጥልቅ ሊገመገም ይገባል ብለዋል።
መረጃው ከዶቼ ቨለ ሬድዮ፣ ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር እንዲሁም ከሲዳማ ክልል የቲክቫህ አባላት የተሰባሰበ ነው።

#Hawassa " ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ሲገባቸው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል " - አቶ አብርሃም ማርሻሎ የሲዳማ ክልል መንግሥት የግምገማ መድረክ እያደረገ ይገኛል ተብሏል። ታዲያ በዚሁ እየተካሄደ ባለው የግምገማ መድረክ ላይ ከተገመገሙት አመራሮች አንዱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ናቸው ተብሏል። ከንቲባው በ " ብልሹ አሰራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " በሚል ከስልጣን…
" የት እንዳሉ አላውቅም "
በሀዋሳ ከተማው እየተካሄደ ባለው የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ግምገማ በርካታ አመራሮችን ለህግ ሊያቀርብ እንደሚችል ተነግሯል።
እየተካሄደ ባለዉ ግምገማ ፦
- በነበረ የፕሮጀክት አፈጻጸም ፣
- የፋይናንስ ህግ ጥሰት
- #ከገበሬ_ማዳበሪያ_ስርቆት ጋር ተያይዞ በርካታ አመራሮች በከፍተኛ ሁኔታ መገምገማቸዉ ተሰምቷል።
ይሁንና በግምገማ ሂደቱ ላይ እንደማንኛዉም ሰዉ የተገመገሙት ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ ግን ግምገማውን ሳይጨርሱ ከህግ ስርአት ዉጭ መዉጣታቸዉን የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ገልጿል።
በጉባኤዉ የተገመገሙ አመራሮች ላይ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የገለጹት የክልሉ ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈትቤት ሀላፊ አቶ አብርሀም ማርሻሎ በዚህ ሰአት ረ/ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ የት እንደሚገኙ እንደማያዉቁ ገልጸዋል።
አቶ አብርሀም ህግን በተከተለ መልኩ እርምጃዎች መወሰድ መጀመሩንና ከግምገማዉ በኋላም እንደሚቀጥል አመላክተዉ ሁሉም አመራር ከህግ በታች ነው ብለዋል።
ቅዳሜ ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀዉ በዚህ ግምገማ ማጠቃለያ የበርካታ አመራሮች ሹም ሽር እንደሚኖር ይጠበቃል።
መረጃውን የሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።

#Budapest 🇪🇹
ሀገራችን #ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ውድድር ደማቅ ታሪክ ከምትፅፍባቸው ውድድር አንዱ የሆነው የ " ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና " በቡዳፔስት፤ ሀንጋሪ ነገ ቅዳሜ ይጀምራል።
🥇በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን ከምሽቱ 3:55 ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተጠባቂው የ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ላይ ትሳተፋለች።
የ10,000 ሜትር #ሴቶች ሀገራችን በማን ትወከላለች ?
1. ለተሰንበት ግደይ
2. ጉዳፍ ፀጋይ
3. እጅጋየሁ ታዬ
4. ለምለም ሀይሉ
5. ሚዛን አለም (ተጠባባቂ )
የቲክቫህ ስፖርት ገፅ @tikvahethsport አባል ከቡድኑ ጋር ወደ ሀንጋሪ ያቀና ሲሆን ተከታታይ መረጃዎችን እና ፎቶዎችን ከስፍራው ለቲክቫህ ቤተሰብ የሚያደርስ ይሆናል።
(ዝርዝር ፕሮግራሙን ከላይ ይመልከቱ)
ድል ለኢትዮጵያ !
ድል ለሀገራችን ልጆች !
More : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

#Budapest 🇪🇹 ሀገራችን #ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ውድድር ደማቅ ታሪክ ከምትፅፍባቸው ውድድር አንዱ የሆነው የ " ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና " በቡዳፔስት፤ ሀንጋሪ ነገ ቅዳሜ ይጀምራል። 🥇በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን ከምሽቱ 3:55 ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተጠባቂው የ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ላይ ትሳተፋለች። የ10,000 ሜትር #ሴቶች ሀገራችን በማን ትወከላለች ? 1. ለተሰንበት…
" ለሀገሬ ክብር ስል ሪከርዱን አስመልሳለሁ " - አትሌት ለተሰንበት ግደይ
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ5,000 ሜትር ሪከርድ በኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ከሀገራችን ስለተወሰደበት መንገድ ስትናገር ቁጭት ውስጥ ሆና ነው።
የ1500 ሜትር የገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ ከዛም በቀናት ልዩነት የራሷ የ5000 ሜትር ሪከርድ በፌዝ ኪፕዬጎን ሲሰበር መመልከት " የሀገር ክብር " እንደመነካት ነው ብላለች።
" የሚፈለገው ብር አይደለም ሁለቱ ሪከርድ ከሀገራችን ሲወጣ በጣም ተበሳጭቻለሁ " የምትለው ለተሰንበት ግደይ ፤ " ይህን ሪከርድ እንደማስመልስ ቃል እገባለሁ ለራሴ ሳይሆን ለሀገሬ #ኢትዮጵያ ክብር ስል " ብላለች።
" ኢትዮጵያ ሀገራችን ሁሌም ቢሆን የወርቅ ሀገር እንድትሆንልኝ እመኛለሁ " ስትልም ተናግራለች።
የሀንጋሪ፣ ቡዳፔሽት የዓለም ሻምፒዮና ነገ ሲጀምር በ10,000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ የምትወዳደረው ለተሰንበት ግደይ እንደ ኦሪገን ውድድር ሁሉ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ ለማምጣት ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።
More : @tikvahethsport

ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ምላሽ ሰጡ።
ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ከሀዋሳ ከንቲባነታቸው እንደተነሱ መግለፁ ይታወቃል።
ከሰሞኑን በነበረ የክልሉ ግምገማ ወቅት በአመራራቸው ላይ ከፍተኛ ትችት ካስተናገዱት አንዱ የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ስለሰሞነኛው ጉዳይ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ለከተማው ነዋሪዎች እና ለሲዳማ ህዝብ ባሰራጩት መልዕክት ፤ "ከሰሞኑ ከሚድያ ሰለራኩኝ ለሶስት ቀናት የሚነዙ የሚድያ አሉባልታና ወሬዎችን የሰማሁ ቢሆንም በጤንነቴ ላይ መጠነኛ እክል ስለገጠመኝ በዉቅቱ ምላሽ ለመስጠት ባለመቻሌ ይቅርታ እጠይቃለሁ " ብለዋል።
" ከሰሞኑ በክልሉ በየነበረዉ የግምገማ ሒደት ለ4 ቀናት የፈጀ ዘመቻ በሐዋሳ ከተማ (ከንቲባ) ላይ ብቻ ባነጣጠረ መልኩ ሲካሔድ ቆይቷል " ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ " ዘመቻዉ እዉነትም የሲዳማን ህዝብ ለዉጥና ብልጽግና ለማሳካት ያለመ ነዉ ? ወይስ ግለሰቦች የራሳቸዉን ፍላጎት ለማርካት እንደ መሸጋገርያ ድልድይ ሊጠቀሙበት ያዘጋጁት ነዉ ? የሚለዉ ሁሉንም ነገር የሲዳማ ህዝብ ጠንቅቆ ስለሚያዉቅ ለእዉነትና ለግዜ ፍርዱን እታዋለሁ " ብለዋል።
የግምገማ ሒደቱ ከመነሻዉ የድርጅታዊ መርህን ያልተከተለ መሆኑን የገለፁት ረ/ፕሮፌሰሩ " ከስራ ይልቅ ግለሰብ ላይ ያነጣጠረና የግል ስብዕናዬን የጎዳ አልፎም በኔ ምክንያት መርጨና ፈቅጄ ያልተወድኩበት ጎሳዬም ጭምር የተሰደቡበት እና ከግምገማነቱ ይልቅ በብዙ ዛቻና ማስፈራርያ የታጀበ ነበር። " ሲሉ ገልጸዋል።
" እኔ መሰረቴ መምህርነት ነዉ። " ያሉ ሲሆን " ፈረሃ- እግዚያብሔር ካለዉ ቤተሰብም ጭምር ነዉ ተኮትኩቼ ያደኩት፣ የመረጠኝን እና ያከበረኝን ህዝብ የማዋርድ፣ ከደሃዉ ህዝቤ ሰርቄ የምበላም ግለሰብ አይደለሁም ለዘላለምም አላደርገዉም። " ብለዋል።
" ነገር ግን የሲዳማ ህዝብ የመዝረፍና የማቆርቆዝ ፍላጎት ባላቸዉ በተደራጁ ቡድኖች እየተፈጸመብኝ የነበረው ተደጋጋሚ የነብስ ግድያ ሙከራና የተደራጀ ውኪቢያ፣ ማስፈራርያና ዛቻ በግምገማ ሰበብ በውሸት አላማቸዉን ለማስፈጸም እየሔዱ የነበሩበት ርቀት ቀላል አይደለም። " ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት በከተማው በርካታ ስራዎች መሰራቱን ሕዝቡም ለከተማ አስተዳደሩ ባለው አጋርነት በርካታ ስከቶች መመዝገባቸውን ገልጸው " በስራዬ ላይ ጥፋት ፈጽመሀል ብሎ ለሚጠይቀኝ አካል መልስ ለመስጠትም ዝግጁ ነኝ ፤ ነገር ግን እዉነታዉን የሲዳማ ህዝብ ገለልተኛ ሆኖ የሚያጣራ አካል ባለበት በተፈለገዉ መንገድ ለማስረዳት ዝግጁ ነኝ። " ሲሉ አሳውቀዋል።
" በክልል መንግስት የሚፈጸመዉ ስረአት አልበኝነትና ዉክቢያ በገለልተኛ ወገን ይጣራ ያኔ ያሉ እዉነታዎች ገሀድ ይወጣሉ። " ሲሉም አክለዋል።
" ህዝብ ሲመርጠኝ የሲዳማን ህዝብ ለመለመወጥ እና ለማበልጸግ እንጂ ጥቂት ግለሰቦችን ለማበልጸግ አይደለም። " ያሉት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ " አሁን ህኪምናዬን እየተከታተልኩ በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ። በቅርቡም በመረጠኝና ባከበረኝ ህዝብ መሀል ተገኝቼ እዉነቱን ለህዝብ አጋራለሁ። " ብለዋል።
" ከዚህ ውጭ የሚነዛዉ ተራ አልሉባልታና የመሻት ወሬ እንደሆነ ማስገንዘብ እወዳለሁ። " ሲሉም ገልጸዋል።
ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የት ሆነው ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ በፅሁፋቸው ላይ ያሉት ነገር የለም።
የሲዳማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በሰጡት ቃል ፤ በግምገማ መድረክ የተገመገሙ አመራሮች ላይ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የገለፁ ሲሆን በዚህ ሰአት ረ/ፕሮፌሰር ጸጋዬ የት እንደሚገኙ እንደማያዉቁ ገልጸዋል።

#Mekelle
" በመቐለ ከተማ ከ184 ሄክታር በላይ የመንግስትና የህዝብ መሬት መጭበርበሩ በጥናት ተረጋግጧል " - የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ
በትግራይ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ከተሞች ህገ ወጥነት ተንሰራፍቶ በርካታ ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከንቲባ ይትባረክ ኣማሃ ገለፁ።
ከንቲባው ፤ የመንግስትና የህዝብ መሬት ዘረፋና የፀጥታ መደፍረስ ዋነኛ ተጠቃሽ ችግሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል።
የመሬት ወረራው የተካሄደው ለምቶ ወደ ተጠቃሚዎች ለመተላለፈ በተዘጋጀ ፤ በእርሻና በመንግስት ክፍት ቦታ ፤ ከገጠር ወደ ከተማ በተካለለና በተቀሙ የኢንቨስትመንት መሬቶች መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ ፤ " በህገወጥ ተግባሩ 3337 ሰዎች ተሳትፈዋል " ብለዋል።
" በመሬት ወረራው የተሳተፉ ህገወጦች በህግ እንዲጠየቁ የህዝቡ ጥያቄ ጭምር ነው " ያሉት ከንቲባ ይትባረክ " ከእርምጃው በፊት የተወረረው መሬት ማጥናት ፣ ቦታዎቹ የሰነዱ ፋይሎች ድህንነት ማረጋገጥ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር ተገብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።
አሳሳቢ የሆነውን የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ በተካሄደው ጥናትና ክትትል በቡድን የሚዘርፉ ፣ ህገ-ወጥ ሕትመት የሚያካሂዱ ፣ የመሬት ፕላን ሰርተው የሚሸጡ ፣ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ የፎርጅድ ገንዘብ ማተምያ ማሽንና የተለያዩ ህገ ወጥ ገንዘቦች እጅ በፈንጅ ተይዘዋል ብለዋል።
የመሬት ወረራ ሆነ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራት ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑ ያብራሩት ከንቲባው ህዝቡ መረጃና ሰነዶች ከመስጠት እስከ መመስከር ንቁና ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ አባል የተላከ ነው።

" ኢትዮጵያውያን በፀሎት እንዳይለዩን " - ጉዳፍ ፀጋይ
የዓለም የወርቅ እና ብር ሻምፒዮኗ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ዛሬ ምሽት በ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ለሀገራችን የመጀመሪያ ሜዳሊያን ለማስገኘት ከቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች።
ከውድድሩ አስቀድሞ ሀሳቧን ያካፈለችው ጉዳፍ ፤ " የራሳችን ጥረት እና ልፋት እንዳለ ሆኖ ሁሉም ነገር የሚያምረው ፈጣሪ ሲጨመርበት ነው ፣ ህዝባችን ሁሌም ከጎናችን ነው አሁንም እንዲሆን እንፈልጋለን ፤ በፀሎት አይለየን " ብላለች።
" የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ነው መግለፅ ያቅተኛል ፤ በየትኛውም ቦታ የተለየ ክብር ነው የሚሰጠኝ ፣ ከዚህ በላይ መስራት እንዳለብኝ የቤት ስራ ሰጥቶኛል። የህዝቡን ፍቅር ለመግለፅ እቸገራለሁ " ስትል ገልጻለች።
ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ ፣ ለምለም ሀይሉ ተካፋይ ይሆናሉ።
#TikvahSport
More 👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport

አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።
አቶ እንዳሻው ዛሬ በቀጠለው ጉባኤ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም በሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ሰርተዋል።