TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቅናሽ የኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ⬇️

▪️የስልክ #ኢንተርኔት ላይ 43%
▪️የብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ 54%
▪️የስልክ ድምፅ ላይ 40%
▪️የሞባይል ፅሁፍ (SMS) ላይ 43%

📌ቅናሹ #ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል መንግስት ለ4 ሺህ 280 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል። እነዚህ የህግ ታራሚዎች #ከነገ ጀምሮ በይቅርታ እደሚለቀቁ የተገለፀ ሲሆን ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥ 67 ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነገ ጀምሮ በግንባታ ምክንያት ለ1 ወር የሚዘጉ መንገዶች ፦

አንድነት ፓርክን መጎብኘት በሚያስችለው የውስጥ ለውስጥ ዋሻ ግንባታ ምክንያት ፦

• ከሂልተን ሆቴል ተነስቶ ወደ ቀኝ ለሚታጠፉ ተሽከርካሪዎች እና

• ከካዛንችስ ወደ አራት ኪሎ የሚያስወጣው መንገድ #ከነገ ጀምሮ እንደሚዘጋ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በዚህም አሽከርካሪዎች ከኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በንግድ ሚኒስቴር፣ በሂልተን ሆቴል ወደ 4 ኪሎ እንዲሁም ከካዛንቺስ መለስ አካዳሚ በሴቶች አደባባይ አቧሬ አድርገው ወደ 4 ኪሎ በመውጣት አማራጭ እንዲጠቀሙ መጠየቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

የ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ዛሬ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦተሪ የተሰጠው መግለጫ በአጭሩ ሲጠቃለል ፦

- ከተፈተኑት ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ አምጥተዋል።

- ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55.7 ፐርሰንቱ ከ350 በላይ አምጥተዋል።

- ከ600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 ናቸው።

- የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 669 ሆኖ ተመዝግቧል።

- #ከነገ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እና በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።

- ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DebreBirhan

በደብረ ብርሃን ከተማ #ከነገ ጀምሮ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች እና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ካላቸው ግለሰቦች ውጪ በከተማው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ፥ " በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች ገብተው አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ስራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ሰርጎ ገቦችን መለየትና አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነጻ ለማድረግ ነው " ብሏል።

በዚህም ለከተማውና ለነዋሪዎች ደህንነት ሲባል በከተማው በየትኛውም አካባቢ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና መታወቂያ ካላቸው ሰዎች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ ወገኖችም በተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍ ማሻሻያ ጥናት መደረጉ ታውቋል። በጥር ወር የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ይታወቃል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ፤ በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ መነሻ በማድረግ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ…
#Update

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ።

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ #ከነገ_ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ፦ ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች ፦

- የጉዞ ርቀት በኪሎ ሜትር እስከ 2 ነጥብ 5 ርቀት በነባር የክፍያ ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣

- ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ፤

- ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ከነገ ጀምሮ ከ60 ሺህ የማይበልጡ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና ይወስዳሉ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ #ከነገ_ጀምሮ በትግራይ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በ2012 ዓ/ም መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ ሲሆን በወቅቱ 120,000 ገደማ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ነበር።

አሁን ከነገ ጀምሮ በሚጀምረው የ8ኛ ፈተና ከ60 ሺህ የማይበልጡ ተማሪዎች ብቻ ለፈተናው ይቀመጣሉ።

ተፈታኝ ተማሪዎች የተሰጣቸው የትምህርት ጊዜ አጭር ቢሆንም በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቀ ትምህርት የተማሩ በመሆናቸውና በወላጅ መምህራን የተቀናጀ ጥረት ፈተናውን ለመውሰድ እንደማይቸገሩም አመልክተዋል ተብሏል።

ነገ የሚጀምረው ፈተና ለሶስት ለተከታተይ ቀናት ይቆያል።

@tikvahethiopia