TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቀለ‼️

በፖለቲካዊ ምክንያት ለዓመታት ተለያይተው የቆዩት የህወሓት ነባር አመራሮች ትላንት #በመቐለ ተገናኝተው 44ኛውን የካቲት 11 በዓል በጋራ አክብረዋል፡፡ 

በመድረኩ ለሁሉም የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1993 ዓ.ም ህወሓት ካጋጠመው ክፍፍል በኋላ ነባር የሚባሉት የድርጅቱ አመራሮች ፖርቲው ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በአንድ መድረክ ተገናኝተው ትግል የጀመሩበት 44ኛውን ዓመት የካቲት 11 አክብረዋል፡፡ 

አስተያየታቸውን የሰጡት የቀድሞ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ዓረና ትግራይ የተባለ ፖርቲ መስርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ #ገብሩ_አስራት "የካቲት 11 የአንድ ድርጅት በዓል ተደርጎ እየተከበረ መቆየቱ ተገቢ አልነበረም" ብለዋል፡፡ የቀድሞ ታጋይ፣ ከትግል በኋላ የመከላከያ ሚኒስተር የነበሩት እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ለዓመታት ታስረው የተፈቱት አቶ ስየ አብረሃ በበኩላቸው "ብዙ መቆሳሰል ቢያልፍም የጋራ ታሪክ አለን" በማለት በአሉ ከቀድሞ ጓዶቻቸው ጋር ማክበራቸው ጥሩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡ 

በስነ ስርዓቱ የወቅቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የመድረኩ አዘጋጅ የትግራይ ክልል ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክርቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia