TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቐለ⬆️የትግራይ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን #በመቐለ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤው በክልሉ ስራ አስፈፃሚ የበጀት ዓመት አቅድ ላይ ይወያያል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ‼️

ታዋቂ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድምፃውያን የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት #በመቐለ ከተማ ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

ኮንስርቱ በመቐለ ከተማ ህዳር 8፣ 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፥ ድምፃዊ ሄለን መለስ፣ ካሕሳይ በርሀ፣ ሰለሞን ሀይለ እና አሊ ቢራ ይሳተፋሉ ተብሏል።

ኮንሰርቱ ዓላማም አሁን ላይ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተጀመረውን ሰላም የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ ዩኒቨርሲቲ🔝

የኢትዮጵያ የሰላም አምባሳደር እናቶች #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ ተገናኝተው ነበር።

"በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሰላም #እናቶች ልብ በሚነካ መልኩ በተማሪዎች መማሪያ ክፍል እየገቡ ተንበርክከው ስለ ሰላም አልቅሰዋል፤ ተማሪዎችንም ቃል አስገብተዋል።"

©ቀኔ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ አራተኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን “የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ #በመቐለ ከተማ ከታህሳስ 7 እስከ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊ትግራይ አማራ የሰላም መድረክ🕊

የትግራይና አማራ ክልሎች የሰላም መድረክ #በመቐለ_ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ትላንት ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የሁለቱን ህዝቦች ዘመናት የተሻገረ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክሩ፣ ስጋት ለፈጠሩ ክስተቶች መፍትሔ የተባሉ ሃሳቦች ቀርበውበታል፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጨምሮ የተሻለ ምክረ ሀሳብ ለፖለቲካ መሪዎች ለማቅረብ በቀጣይነት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

የመድረኩ አስተባባሪና ጥናት አቅራቢ ዶክተር ገብረየሱስ ተክሉ የግጭት ስጋቶች ለማምከን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ገንቢ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚስተዋሉ #ግጭቶችና የግጭት ስጋቶች ለመከላከል ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tukvahethiopia
መቀለ‼️

በፖለቲካዊ ምክንያት ለዓመታት ተለያይተው የቆዩት የህወሓት ነባር አመራሮች ትላንት #በመቐለ ተገናኝተው 44ኛውን የካቲት 11 በዓል በጋራ አክብረዋል፡፡ 

በመድረኩ ለሁሉም የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1993 ዓ.ም ህወሓት ካጋጠመው ክፍፍል በኋላ ነባር የሚባሉት የድርጅቱ አመራሮች ፖርቲው ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በአንድ መድረክ ተገናኝተው ትግል የጀመሩበት 44ኛውን ዓመት የካቲት 11 አክብረዋል፡፡ 

አስተያየታቸውን የሰጡት የቀድሞ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ዓረና ትግራይ የተባለ ፖርቲ መስርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ #ገብሩ_አስራት "የካቲት 11 የአንድ ድርጅት በዓል ተደርጎ እየተከበረ መቆየቱ ተገቢ አልነበረም" ብለዋል፡፡ የቀድሞ ታጋይ፣ ከትግል በኋላ የመከላከያ ሚኒስተር የነበሩት እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ለዓመታት ታስረው የተፈቱት አቶ ስየ አብረሃ በበኩላቸው "ብዙ መቆሳሰል ቢያልፍም የጋራ ታሪክ አለን" በማለት በአሉ ከቀድሞ ጓዶቻቸው ጋር ማክበራቸው ጥሩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡ 

በስነ ስርዓቱ የወቅቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የመድረኩ አዘጋጅ የትግራይ ክልል ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክርቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአክሱም...

"ኣገር ኣቀፍ የተማሪዎች ህብረት #በመቐለ የነበረው ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ ኣሁን ደግሞ ከ14 ዩንቨርስቲዎች የተውጣጣ ቡድን ትናንት ነጃሺ ታሪካዊ መስጊድ ዛሬ ደግሞ በኣክሱም ጉብኝት እያደረግን እንገኛለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዛሬ ምሽት አሳውቋል። ባንኩ በቀጣይ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ አገልግሎቱን በማስፋትና በየደረጃው በሁሉም ቅርንጫፎች ላይ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሰራ ገልጿል። በሰሜን…
#Lion #Wegagen

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሽረ እንደስላሴና አካባቢው የሚገኙት ቅርንጫፎቹ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በአላማጣና በራያ ጥሙጋ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

ባንኩ ሰቲት ሁመራ፣ አዲ ረመፅ ፣ ዳንሻ  እና ተከዜ ቅርንጫፎች ቀደም ብለው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውሷል።

በቅርቡም ፤ #በመቐለ እና #በሽረ ዲስትሪክቶች በሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

የኢፌዴሪ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የባለድርሻ እና አጋር አካላት የውይይት መድረክ #በመቐለ ለመጀመርያ ጊዜ ይካሄዳል።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የባለድርሻ እና አጋር አካላት መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በመቐለ እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት ከሰላም ስምምነቱ ብኋላ ክልሉ ላይ አንፃራዊ  መረጋጋት መፈጠሩ እና በሁለቱም ተስማሚ ወገኖች የመተማመን ጉዳዩ መጎልበቱን ማሰያ ነው ብሏል።

በመድረኩ ለመሳተፍ የተለያዮ ባለድርሻ እና አጋር  አካላት ከፌዴራል መንግስት የተላከ የልኡኳን ቡድን  በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ መሪነት ዛሬ መቐለ ገብቷል።

የፌደራል መንግስቱ ልኡኳን ብድኑ ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የሰቪክ ማህበራት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  እንዲሁም ከንግድ ሚኒስቴር እና የተለያዮ ክልሎች ተወካዮች ያካተተ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

#ድምፂወያነ

@tikvahethiopia
#Axum

" የሃውልቱ ዲዛይንና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው ፤ አይገናኝም ! "
 
ዛሬ በአክሱም ከተማ የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃውልት ተመርቋል።

ነገር ግን ከሃውልቱ ግንባታ ጋር በተያያዘ በርካቶች " አይመጥንም " በሚል ተቃውመዋል።

በአክሱም በይፋ የተመረቀው የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃወልት ለግንባታው አራት (4) አመት መፍጀቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።

በምረቃ ስነ-ሰርዓቱ የተገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሃውልቱ ግንባታ ዙሪያ የተነሳው ተቃውሞ ተከታትሏል።

በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ምእመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የኢትዮጵያና የዓለም የዜማ አባት የሆነው ማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ የሚያስታውስ ሃወልት መቆሙ ቢያስደስታቸውም " ሃውልቱ የዜማ አባቱን ክብርና ዝና የሚመጥን አይደለም " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በስነ-ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳዳሪ ንቡረ እድ ጎደፋ መርሃ ምእመናኑና እና ታዳምያን " ሃወልቱ አይመጥንም " ሲሉ ያነሱትን ቅሬታ ተጋርተውታል።

የምረቃ ስነ-ሰርዓቱ በሚድያ ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኃላ ' ሃወልቱ ቅዱስ ያሬድን አይወክልም ፤ አይመጥም ' የሚል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያለው ወገን ተቃውሞውን በማህበራዊ ሚድያ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እያጋራ ነው።

ከዚህ አለፍ ሲል ፈርሶ ድጋሜ እንዲገነባና ሃወልቱ ማህሌታይ ያሬድን በሚመጥን መልኩ በሀገር ያሉና በውጭ ያሉ ባለሞያዎችን አሳትፎ እንዲገነባ " ገንዘብ እናዋጣለን " እንዲሁም እውቀታችንን እናካፍላለን ያሉ አሉ።

" የሃውልቱ ዲዛይን እና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው አይገናኝም " ያሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ባለመከታተሉ ወቅሰዋል።

ሃወልቱ #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ እና በአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳደር ትብብር የተገነባ ሲሆን ለግንባታው ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle                                               
@tikvahethiopia