TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በቦልቪያናዊዉ ናማኒ ቺንቼ ኢቬሊን የፓስፖርት ቁጥር AE57255 ከብራዚል ሳዖ ፖሎ አዲስ አበባ የገባዉ 8 ኪሎ ግራም የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

ዕፁን ይዞት ይጓዝ በነበረዉ ግለሰብ ላይ ከብራዚል ሳኦ ፖሎ ጀምሮ በጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንስ ቡድን ባደረገዉ የተቀናጀና ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊዉል መቻሉ ተገልጿል፡፡

ይህንን አድካሚና የተቀናጀ ስራ በመስራት እፁን መያዝ ለቻሉ የቦሌ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራር አካላትና ሰራተኞች የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡ ባለፈዉ ሳምንትም 20 ሚሊየን ብር የሚገመት 10.8 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡፡

Via #ethiofm
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ - ቴሌኮም [ethiotelecom] የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አሳውቋል። ማሻሻያውም ለመኖርያ ቤት 69 በመቶ ቅናሽ ፣ ለድርጅቶች 65 በመቶ፣ VPN ደግሞ 72 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።

ማሻሻያው በዋጋ ብቻ ሳይሆን በፍጥነትም ጭምር መሆኑ ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለመኖርያ ቤት የ 3 በመቶ ፍጥነት ፣ ለድርጅቶች 4 በመቶ ፍጥነት ይጨምራል።

PHOTO : #TikvahFamily [Andinet]

#ETHIOFM #ሔኖክአስራት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ…
#TPLF #ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቢሮ እንደሚከፍት ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ግን የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

ብልጽግና ፓርቲ ለትግራይ ክልል የተሾሙ ግለሰቦች እንዳሉ ሰምቻለሁ እነማን እንደተሾሙ ግን ወደ ፊት የሚሆነዉን የምናይ ይሆናል፡

ብልጽግና በትግራይ ክልል ብዙ ደጋፊ አለው ብዬ አላምንም፤ ማንኛዉም ፓርቲ ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ግን በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብት አለዉ።

#EthioFM #አባቱመረቀ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ከኢትዮጵያ ወደሀገሩ አሜሪካ እንደተመለሰ የተነገረለት አንድ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መያዙን Talk Media News ዘግቧል። ለጊዜው ወታደሩ ከኢትዮጵያ መቼ እንደተመለሰ የሰጠው ፍንጭ የለም።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጡት መረጃ የለም። በጉዳዩ ላይ የሚሰጡ መረጃዎች ሲኖሩ እንድታነቡት የምናደርግ ይሆናል።

https://www.talkmedianews.com/featured/2020/03/09/marine-back-from-ethiopia-tests-positive-from-covid-19-at-ft-belvoir-virginia/

#TalkMediaNews #EthioFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው!

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2,000,000 በላይ ሆኗል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 485,304 ሺህ ደሷል። የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 126 ሺህ 811 ደርሷል፡፡

- ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ባለው መረጃ ከ614 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ በዚሁ በሽታ ሲያዙ ከ26 ሺህ በላይ ያህሉ ህይወታቸውን አጥተዋል። በትላንትናው እለት ብቻ በአሜሪካ 2 ሺህ 385 ሰዎች በበሽው ሂወታቸው አልፏል፡፡

- በካናዳ የሟቾች ቁጥር ከ900 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 123 ሰዎች ሞተዋል። በሀገሪቱ በቫይረሳ የተያዙ ሰዎች ደግሞ ከ27 ሺህ በላይ ሆኖ ተመዝግባል፤ ከዚህ መካከል 1,383 የሚደርሰው ኬዝ በአንድ ቀን የተመዘገበ ነው።

- በቱርክ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ነው። ባልፉት 24 ሰዓት 4,062 አዲስ ኬዝ ሲመዘገብ፤ 107 ሰዎች ሞተዋል።

- በተመሳሳይ በሩሲያም ቫይረሱ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት 2,774 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአፍሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ በአፍሪካ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 790 ደርሷል።

#ETHIOFM #BBC #AFP #SKYNEWS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ventilators

ደቡብ ሱዳን 5 ምክትል ፕሬዘዳንቶች ያላት ቢሆንም ለ11 ሚሊዮን ህዝብ የሚሆን 4 የኦክስጅን መስጫ ማሽኖች አላት ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን ለኮሮና ቫይረስ ህመምተኞች ለመተንፈስ የሚያግዛቸው ቬንትሌተር ማሽን በደቡብ ሱዳን ካሉ ምክትል ፕሬዘዳንቶች እኩል ባይሆንም አንድም እንኳን ከሌላት ሱማሊያ በቁጥር ልቆ ታይቷል፡፡ በሱማሊያ ምንም አይነት የመተንፈሻ መሳሪያ እንደሌለ ዘገባው ያስረዳል፡፡

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን 3 ቬንትሌተር ብቻ ነው ያላት ፤ ላይቤሪያም በተመሳሳይ ከ6ቱ 3ቱ ብቻ ናቸው የሚሰሩት።

ቡርኪና ፋሶ ለ20 ሚሊየን ህዝብ 11 ነው ያላት ፤ በኬኒያ 257 ፤ በጋና 200 ፤ ሱዳን 80 አላቸው፡፡ በሀገራችንም 575 ቬንትለተሮች እንዳሉ ዘገባው ጠቁሟል፡፡

በአፍሪካ በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ 2,000 ቬንትለተሮች ያሉ ሲሆን ከ46 ሺህ በላይ ሰዎች በሞቱባት በአሜሪካ ብቻ 17 ሺህ ቬንትሌተሮች እንዳሉ ነው ዘ ኒዉ ዮርክ ታይምስ በዘገባው ያስረዳው፡፡

#ETHIOFM #DERESEAMARE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ የሚያበቃው መቼ ነው?

(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 - በሙሉቀን አሰፋ)

የኮሮና ቫይረስ የሰዉ ልጅ በቀላሉ የማይገላገለዉ ትልቅ ስጋት ሆኖ እንደሚቀጥል የቻይና ተመራማሪዎች ተናገሩ፡፡

ተመራማሪዎቹ እንዳሉት በመጀመሪያ ቫይረሱ ሲከሰት ምልክቶችን ስለሚያሳይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን በቀላሉ መለየት ይቻል ነበር፡፡

ይህም በቫይረሱ ለተጠቁ ሰዎች ክትትል ለማድረግም ሆነ ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ለማድረግ እድል ይፈጥር ነበር፡፡

አሁን ላይ ግን ሰዎች ቫይረሱን ተሸክመዉ ቶሎ ምልክቶቹን እያሳዩ አይደለም፤ይህ ደግሞ ቫይረሱን ተቆጣጥረነዋል ብሎ የመናገር እርግጠኛነትን መና ያስቀረዋል ነዉ ያሉት፡፡

የኮሮና ቫይረስ ሰዎች በየአመቱ በተጠንቀቅ የሚከላከሉት ወረርሽኝ እንጂ በአንዴ ተከስቶ የሚጠፋ ክስተት እንደማይሆንም ነዉ ተመራማሪዎቹ ስጋታቸዉን የገለጹት፡፡

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የተላላፊ በሽታዎች ብሄራዊ ተቋም ዋና ዳይሬክተር አንቶኒ ፋቺ ከብሉምበርግ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፣ ዓለም መቼም የኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ወደ ነበረችበት ቁመና መመለስ አትችልም ብለዉ ነበር፡፡

ዓለም ወደ ቀድሞ ቁመናዋ የምትመለሰዉ የኮሮና ቫይረስ በምንም መልኩ ዳግም የመከሰት እድል ከሌለዉ ብቻ መሆኑን ገልጸዉ፣ በእርሳቸዉ እሳቤ ግን ቫይረሱ በየወቅቱ ሊያገረሽ የሚችል የሰዉ ልጅ ክፋ ባላንጣ መሆኑን አስምረዉበታል፡፡

ተመራማሪዎቹ በቤተ ሙከራዎች የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ አሳማኝና ተጨባጭ መፍትሄን ይዘዉ ለመምጣት መቸገራቸዉን ገልጸዉ፣ ከቫይረሱ ተለዋዋጭ ባህሪይ ጋር ተዳምሮ የሰዉ ልጅና የኮሮና ቫይረስ ግብግብ በየአመቱ ሊቀጥል እንደሚችል መናገራቸውን ፎክስ ኒዉስ ዘግቧል።

#ETHIOFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ክትባት!

የቤጂንግ ባዮሎጂካል ምርምር ኢንስቲትዩት እና የቻይና ብሔራዊ ባዮቲክ ቡድን በጋራ እያዘጋጁት የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት 2 የምርመራ ፈተናዎችን አጠናቋል።

ይህ ክትባት በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ወይም በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ 'ለገበያ ዝግጁ' ሊሆን እንደሚችል ብሉምበርግ ዘግቧል።

ቻይና የኮሮና ቫይረስ ክትባት በዚህ አመት በስፋት ለማምረት ዝግጅት እያከናወነች ሲሆን በየአመቱ ከ100 ሚሊዮን እስከ 120 ሚሊዮን ክትባቶችን የማምረት አቅም ይኖራታል ተብሏል።

መድሀኒት ቀማሚዎች እስካሁን ቢያንስ 367 ሺህ ሰዎችን ለገደለው ተላላፊ በሽታ መድኃኒት ለማግኘት እየጣሩ ነው።

#EthioFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጦር ማንኛውም አይነት ጥቃት ለመመከት 24 ሰዓት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ETHIO FM 107.8 ጣቢያ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ ምዕራብ ጎንደር አካባቢ እያደረሰች ስላለው ጥፋት ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነው።

አምባሳደር ዲና ፥ የሱዳን ኃይል የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በርካታ ህገወጥ ድርጊቶችን መፈፀሙን ተናግረዋል።

ይህም "የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለዉን የህግ ማስከበር ተልዕኮ እንደ ክፍተት ተጠቅመዉ ኢትዮጵያን እና ሱዳንን ወደ ግጭት እንዲያመሩ ከከሚፈልጉ ሃይሎች የመነጨ ነዉ" ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሉኣላዊነቷን ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደር ዲና ፥ "ችግሩን በሰላማዊ መንገድ እንፈታለን ስንል ፍርሃት ከመሰላቸዉ ተሳስተዋል ፤ ማንኛዉንም ጥቃት ለመመከት የፀጥታ ሃይሉ 24 ሰዓት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል” ብለዋል፡፡

አምባሳደሩ ፥ "የኢትዮጵያን ዉድቀት፣ የኢትዮጵያን ችግር፣ የኢትዮጵያን ውጥንቅጥነት የሚመኙ ወገኖች ካሉ ተስፋ ቢቆርጡ ነው የሚሻላቸው ፥ ይህ የሚሳካ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

የኢትዮጵያን ውድቀት የሚመኙ ሀገራት መኖራቸዉን የሚገልፁት አምባሳደር ዲና ፥ ኢትዮጵያ በነጻነቷ ከመጡባት ማንንም እንደማትምር ከታሪካችን መረዳት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የሱዳን ህዝብ እና የሱዳን መንግስት ከሚጎትታቸዉ ሃይል እራሳቸውን እንዲቆጥቡም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አሳስበዋል፡፡ #EthioFM

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ቱርክ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች" - አምባሳደር ያፕራክ አልፕ

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የህዳሴዉ ግድብ ሶስትዮሽ ድርድር እና የኢትዮ ሱዳን የድንበር ዉዝግብ በሠላማዊ መንገድ ሊፈታ ይገባል አሉ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጡት ቃለምልልስ ነው።

ቱርክ ከሱዳን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት ያላት አገር መሆኗን የገለፁት አምባሳደሩ ፥ ጦርነት ለሁለቱም አገራት ስለማይበጅ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ያፕራክ አልፕ አገራቸዉ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆምም አስታዉቀዋል፡፡

አገራቸዉ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልዉዉጥ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደምትሰራም ገልፀዋል።

ቱርክ እና ኢትዮጵያ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸዉ የገለፁት አምባሳደር ያፕረክ አልፕ፤ አሁን ላይ የአገራቱ አመታዊ የንግድ ልዉዉጥ 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

በሌላ መረጃ : ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከቱርኩ የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር አዲል ካራይስማይሎግሉ ጋር ስምምነቱን መፈራረማቸውን በትዊተር ገጻቸው አሳውቀዋል።

#EthioFM #WeyzeroDagmawitMoges

@tikvahethiopia
#አህያ🫏

በአዲስ አበባ ከተማ ከተለመደው " የከብት ስጋ ውጪ ህገወጥ እርድ እየተፈፀመ ነው " የሚል ጥርጣሬን ተከትሎ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማሳወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

ህገወጥ እርድ የሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚጣለው ቅጣት መሻሻሉንም ባለስልጣኑ የገለፀ ሲሆን ህገወጥ እርድ የሚፈፀም ወይም የሚያቀርብ ማንኛውም አካል እስከ 15ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት አመልክቷል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚደረግን ህገወጥ እርድ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በመሆን ህገወጥ እርድን የመቆጣጠርና የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ፤ ከእንስሳት ዝውውር፣ ግብይትና ዕርድ ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦች ተሻሽለዋል ፤ ደንቦቹን ተላልፈው የተገኙ አካላትም እስከ 15 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲል ገልጿል።

ከህገወጥ ዕርድ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ በከተማዋ ከተለመደው የከብት ስጋ ውጪ እየተሸጠ ተድርጎ ቢወራም  ከዚሁ ጋር  ተያይዞ ባለስልጣኑ ምንም ጥቆማ እንዳልደረሰው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።

ነገር ግን ባለስልጣኑ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በ119 ወረዳዎች እንዲሁም በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለባለስልጣኑ የደረሰው  ጥቆማ አለመኖሩን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የስጋ ነጋዴዎች " የአህያ ስጋ በአዲስ አበባ እየተሸጠ ነዉ " በሚል ምክንያት የቀድሞ ገበያችን በከፍተኛ ደረጃ ተቀዛቅዟል ሲሉ ለ ' ካፒታል ጋዜጣ ' ተናግረዋል።

" በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ለምግብነት እየቀረበ ነዉ " በሚል ተሰራጭቷል በተባለው መረጃ ሳቢያ የዕለት ገበያቸዉ ከቀድሞ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ " ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ ከገበያዉ እንድንወጣ ሊያደርገን ይችላል " ብለዋል።

" አሁን እስከ 80 ሺህ ብር የተገዛው ሰንጋ በሬ ወደ ተጠቃሚዎች በሚቀርብ ጊዜ የአህያ ነዉ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እናስተናግዳለን " በዚህ ምክንያት ሳይሸጥ የሚያድርበት ቀናቶች በርካታ ናቸዉ " በማለት ተናግረዋል።

ከገቢ አንፃር ምን ያህል አጣችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸዉ ሁለት የስጋ ሽያጭ ሉካንዳ ቤቶች "ከገቢ አንፃር ብቻ ሳይሆን በፊት ለገበያ የምናቀርበው ሁለት ሰንጋ ከብቶች በህጋዊ መንገድ በቄራ እርድ ተፈፅሞ ቢሆንም አሁን ግን አንዱን በትግል ነዉ የምንጨርሰዉ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሁኔታዉ አሳስቦናል ያሉት የስጋ ነጋዴዎቹ  ከገቢ አንፃር ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነዉን ማጣታቸዉን ለ 'ካፒታል ጋዜጣ' ገልጸዋል።

ከሰሞኑን፤ 'ብሩክ ኢትዮጵያ' የተሰኘ የአህያ መብት ተሟጋች ተቋም በኢትዮጵያ በመንግስት ዕውቅና ተሰጥቶት ስራ የጀመረው የአሰላ የአህያ ቄራ ምንም እንኳን ለውጭ ገበያ ታስቦ ቢከፈትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሰላ አካባቢ ያሉ ስጋ ቤቶችም ስጋውን ለሽያጭ ሲያቀርቡ እንደተገኙ ተናግሯል።

በአህያ ቆዳ ንግድ ሳቢያ አህዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ መመናመን እየታየ ነው ብሏል።

በመንግስት እውቅና የተሰጠው የአሰላ የአህያ ቄራ በቀን ከ100 - 300 አህዮች ለእርድ ያቀርባል፤ በዚህ የተነሳ ከዚህ ቀደም ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው አህያ አሁን ከ9,000 እስከ 11,000 ብር እየተሸጠ ነው ተብላል።

ለቻይና ባሕላዊ ሕክምና እና ለኮስሞቲክስ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ጄልቲን ‘ኢጂአኦ’ ለማምረት የአህያ ቆዳ ተፈላጊ እንደሆነ ይነገራል።

Credit - #Capital #EthioFM

@tikvahethiopia