TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቻይና የዱር እንስሳት ንግድን ልታግድ ነው!

የቻይና ከፍተኛው የህግ አውጪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የዱር እንስሳት መነገድም ሆነ መመገብ ለአዲሱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ መነሻ ናቸው በሚል ድርጊቱን ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ፡፡

ለብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ (NPC). የተመራው ረቂቅ ህግ የትኛውንም የዱር እንስሳት መመገብም ሆነ መነገድን የሚከለክል ሲሆን ይህም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ አልፎ ብዝሀ-ህይወትን ለመታደግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው 3ሺ የብሄራዊ የህዝብ ምክር ቤት አባላትን ሲወክል ኮሚቴው በመጪው ወር በሚያደርገው ስብሰባ አዋጁን እንደሚያጸድቀው ቢጠበቅም በሀገሪቱ የተከሰተው የጤና ቀውስ እንደሚያዘገየው ከወዲሁ ተገምቷል፡፡

የቻይና የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስ በውሀን ግዛት የመከሰቱ መነሻ የዱር እንስሳት ገበያ እንደሆነ ግምታቸውን አስቀመጠዋል፡፡

የቻይና ወግ አጥባቂዎች ጤንነታቸው ያልተረጋገጠ የዱር እንስሳት ሲሸጡ ቻይና ዝም በማለቷ ለተከሰተው የጤናና ኢኮኖሚዊ ቀውስ ሀላፊነቷን አልተወጣችም በማለትም ሲወቅሷት ሰንብተዋል፡፡

#AFP #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተመዘገበው ሞት!

በግብፅ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ህክምና ሲደረግለት የነበረው ጀርመናዊ ቱሪስት መሞቱና በአፍሪካ አህጉር የመጀመርያው ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡ የ60 አመቱ ጀርመናዊ ግብፅ በደረሰ ከሳምንት በኋላ ምልክቱ እንደታየበት ተጠቅሷል፡፡

ግለሰቡ በወቅቱ ሬድ ሲ ሪዞርት ሆስፒታል ገብቶ የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ እንደነበረ ዘገባው አመልክቷል፡፡ ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው የአተነፋፈስ ስርዓቱ በአጣዳፊ የሳንባ ምች መጎዳቱን ያሳያል ተብሏል፡፡ በሽተኛው ወደ ገለልተኛ ማቆያ ክፍል መዘዋወር ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከገለፀ በኋላ ሊሞት እንደቻለ ተነግሯል፡፡

#BBC #AFP
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy #Russia #COVID19

ሩስያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ በብርቱ እየተጠቃች ያለችውን ጣልያንን ለመደገፍ ሐኪሞችን እና የህክምና ቁሳቁስ እየላከች መሆኗን አስታውቃለች።

ሩስያ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችዉን ጣልያንን ለመደገፍ በዘጠኝ የጭነት አውሮፕላኖች የሕክምና ባለሞያዎች እና ቁሳቁስ ወደስፍራው ለማጓጓዝ በችካሎቭስኪ ወታደራዊ ሰፈር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጻለች።

በተልዕኮው ስምንት (8) ተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድኖችን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ እና የጸረ ቫይረስ [COVID-19] ርጭት ተሽከርካሪዎች ያካተተ መሆኑን ተገልጿል።

#AFP #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማጠቃለያ አጫጭር መረጃዎች፦

- አውሮፓ ውስጥ ብቻ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ15,000 በልጧል።

- ደቡብ አፍሪካ መንግሥት ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴን የማገድ አዋጅ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራል።

- በፈረንሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ 365 የኮቪድ-19 ሞት ተመዝጓል አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 1,696 ደርሷል።

- በዩናትድ ኪንግደም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 11,658 ደርሷል። የሟቾች ቁጥርም ወደ 578 ከፍ ብሏል።

- የG20 አገራት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተዳከመውን የዓለም ኢኮኖሚ ለመደገፍ 5 ትሪሊዮን ዶላር ወደ ዓለም ገበያ ፈሰስ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

- በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ80,000 ተሻግሯል። በአሜሪካ ያሉ ተጠቂዎችም ከጣልያን በልጠዋል። በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም 1,163 ደርሷል።

- ኡጋንዳ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን አግዳለች። የንግድ ተቋማት ድርጅቶቻቸውን እንዲዘጉ መንግሥት ውሳኔ አስተላልፏል።
 
- በአውሮፓ ከጣልያን ቀጥላ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ እየተጎዳች የምትገኘው ስፔን በ24 ሰዓት 498 ሰዎችን አጥታለች። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 4,145 ደርሰዋል።

- በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 524,007 ደርሷል፤ 23,670 ሰዎች ሞተዋል። 123,322 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

#CGTN #BBC #AFP
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው!

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2,000,000 በላይ ሆኗል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 485,304 ሺህ ደሷል። የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 126 ሺህ 811 ደርሷል፡፡

- ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ባለው መረጃ ከ614 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ በዚሁ በሽታ ሲያዙ ከ26 ሺህ በላይ ያህሉ ህይወታቸውን አጥተዋል። በትላንትናው እለት ብቻ በአሜሪካ 2 ሺህ 385 ሰዎች በበሽው ሂወታቸው አልፏል፡፡

- በካናዳ የሟቾች ቁጥር ከ900 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 123 ሰዎች ሞተዋል። በሀገሪቱ በቫይረሳ የተያዙ ሰዎች ደግሞ ከ27 ሺህ በላይ ሆኖ ተመዝግባል፤ ከዚህ መካከል 1,383 የሚደርሰው ኬዝ በአንድ ቀን የተመዘገበ ነው።

- በቱርክ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየጨመረ ነው። ባልፉት 24 ሰዓት 4,062 አዲስ ኬዝ ሲመዘገብ፤ 107 ሰዎች ሞተዋል።

- በተመሳሳይ በሩሲያም ቫይረሱ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት 2,774 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአፍሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ በአፍሪካ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 790 ደርሷል።

#ETHIOFM #BBC #AFP #SKYNEWS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#LatinAmerica

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ላቲን አሜሪካ አዲሷ የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ-19/ ወረርሽኝ #ማዕከል መሆኗን አሳውቋል - #AFP

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን ተወያየ ?

በትግራዩ ጦርነት ለተጎዳዉ የክልሉ ሕዝብ ተጨማሪ ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ የተባበሩት መንግስታት (UN) የፀጥታው ጥበቃ ም/ቤት አባል ሃገራት ጠይቀዋል።

አስራ-አምስቱ የምክር ቤቱ አባላት ትግራይ ዉስጥ ስላለዉ ስብአዊ ሁኔታ በዝግ ተነጋግረዋል።

የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ምክር ቤቱ በይፋ ያወጣዉ መግለጫ የለም።

ይሁንና ዜና አገልግሎቱ የጠቀሳቸዉ ዲፕሎማት እንዳሉት የርዳታ ድርጅቶች ለትግራይ ሕዝብ ተጨማሪ ሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ ይበልጥ ይፈቀድላቸዉ ዘንድ ሁሉም ተሰብሳቢዎች ጠይቀዋል።

የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤትን ስብሰባ የጠሩት አየርላንድ ፤ ኢስቶንያ ፈረንሳይ፣ ኖርዌ፣ ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ናቸዉ።

ከስብሰባው በኃላ ይፋዊ መግለጫ ባይወጣም ስብሰባውን አስመልክቶ ዲፕሎማቶች ባደረጉት ገለፀ ኬንያ ፣ ቱኒዝያ፣ ቻይናና ሩሲያ አሁን ባለው ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደር አይገባም ብለዋል/ፍቃደኛ አልሆኑም።

#DeutscheWelle #AFP #Bloomberg

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
* TPLF

የ " ህወሓት ኃይሎች " ባለፉት ቅርብ ሳምንታት የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (USAID) የሆኑ የእርዳታ መጋዘኖችን መዝረፋቸው ተገለጸ።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳሬክተር ሾን ጆንስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ፥ "የህወሓት አማጺያን በደረሱባቸው ስፍራዎች የሚገኙ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል" ብለዋል።

የUSAID የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ፥ "የታጠቁ ሰዎች ከዜጎች ምግብ ሰርቀዋል። ህወሓት በገባባቸውና ጦርነት በከፈተባቸው ሁሉም የአማራ አካባቢዎች መጋዘኖችን ዘርፏል፤ ተሽከርካሪዎች ዘርፏል። ውድመት ፈፅሟል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሾን ጆንስ አክለው ፤ "በተለይ የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካበቢዎች በርካታ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ስለመዝረፋቸው እና መጋዘኖቹ ባዶ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አለን" ብለዋል።

በተጨመሪ ፥ "ህወሓት ሁኔታዎችን ያለአግባብ እየተጠቀመ እንደሆነ አምናለሁ። ከተረጂዎች ላይ በኃይል እርዳታ እየነጠቀ አንደሆነ ይሰማናል፤ የምናውቀው ሃቅ ግን የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ዘርፈዋል" ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ የአሜሪካ ተወካይ በተመሳሳይ "በአማራ ክልል ውስጥ የእርዳታ መጋዘን በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን" ተናግረው እንደነበር ቢቢሲ አስነብቧል።

#EBC #BBC #AFP

@tikvahethiopia
#Afar

በበራህሌ ስደተኞች መገደላቸው ተገለፀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት " በራህሌ መጠለያ " ሰፈር ላይ በተፈፀመ ጥቃት ስደተኞች መገደላቸውን አስታወቀ።

ተመድ አፋር ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ውጊያ ከኤርትራ የገቡ ስደተኞች የተጠለሉበትን ሠፈር በብርቱ እንደጎዳ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

በአፋር እና ትግራይ ክልል አዋሣኝ በሚገኘው በራህሌ መጠለያ ሠፈር ላይ በተጣለ አደጋ 5 ሰዎች ሲገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መሸሻቸውን አመልክቷል።

ጥቃቱ ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ መፈፀሙን ተመድ ተናግራል።

የታጠቁ ሰዎች ጥር 26 ወደ መጠለያ ሠፈሩ ከገቡ በኋላ " ቢያንስ 5 ስደተኞችን መግደላቸውንና ብዙ ሴቶችን ጠልፈው መውሰዳቸውን " ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎችን ጠቅሷል።

ተመድ ባወጣው መግለጫ በመጠለያው ላይ ጥቃት ያደረሱትን ኃይሎች ማንነት አልገለፀም።

ነገር ግን በዚህ ሳምንት አፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ የደረሱ ሰዎች ጥቃቶቹን ያደረሰው ህወሓት መሆኑን ለAFP ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ከስደተኞቹ አንዱ የሆኑት መሃሙዳ አህመድ " አንድም የመንግሥት ደጋፊ ታጣቂ ሌለበት አካባቢ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው " ሲሉ ተናግረዋል። " ወታደሮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ ሲከፍቱ አይቼ አላውቅም። የሚዋጋቸው ወታደርም አልነበረም። የነበሩት ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ብቻ ነበሩ። እናም ከባድ መሣሪያዎችን ይተኩሱ ነበር " ብለዋል።

የአፋር ክልል መንግሥት ባለሥልጣናት እና የብሄራዊ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳዮች አስተዳደር ለጥቃቱ ተጠያቂው ህወሓት ነው ማለታቸውን AFP በዘገባው ላይ ጠቅሷል።

#AFP #VOA

@tikvahethiopia
#ሰበር

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ዛሬ አወጀ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅታቸው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ማወጁን አሳውቀዋል።

#AFP

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Kenya

ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው።

መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል።

ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡

ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል።

ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል።

ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ተነግሯል።

ይህ በኬንያ ወጣቶች መሪነት የተነሳው እና ባለፈው ማክሰኞ በናይሮቢ ከተማ ተጀምሮ በመላው አገሪቱ የተሰራጨው ተቃውሞ በመጭው ማክሰኞ ብሔራዊ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ተቃዋሚዎቹ ለምን አደባባይ ወጡ ?

ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደስተኛ አይደሉም።

አካሄዳቸውም ለብዙ ኬንያውያን ኑሯቸውን አስቸጋሪ ማድረጉን ይገልጻሉ።

በተለይም መንግሥት አሁን ያዘጋጀው የታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ የህዝቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል እንደሆነ በመግለጽ እየተቃወሙ ነው።

የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቶ ነው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ የተቀየረው።

የኬንያ መንግሥት ምን ይላል ?

መንግሥት የታክስ ጭማሪ ሊያደርግ ያቀደው ብድር ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ ገልጿል።

ተቃውሞውን ተከትሎ ከረቂቅ አዋጁ ላይ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን ዛሬም ቀጥሏል።

የታክስ ጭማሪው ምን ላይ ነው ?

መንግሥት በያዘው እቅድ የታክስ ጭማሪው በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የሚደረግ ነው።

በነዳጅ ላይ ሊጨመር የታሰበው 9 ሺልንግ ሲሆን ጭማሪው ለፈረሱ መንገዶች መጠገኛ እንደሚሆን የአዋጁ አርቃቂዎች አስታውቀዋል።

መንግስት በተጨማሪ አካባቢን ለመጠበቅ በሚል ታክስ ለመጣል ያቀደ ሲሆን ይህም ደግሞ የፕላስቲ ውጤቶች የሚያስከትሉትን ብከላ ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል።

ብሔራዊ ሸንጎው ረቂቅ አዋጁን ሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ለተቃውሞ የወጡት ኬንያውያን ግን በተቃውሟቸው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።

#AFP
#VOA
#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GRED🇪🇹 የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 3ኛው እና 4ኛውን ተርባይኖች ሥራ መጀመራቸውን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሳውቀዋል። " ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉም " ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ ተደምጧል " ብለው " የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA #GERD 🇪🇹

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መስሪያ ቤት ምን አለ ?

(ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት / አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የሰጠው ቃል)

- በቅርቡ 2 የግድቡ ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸው ከግድቡ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል።

- ከዚሕ ቀደም ብሎ ሥራ የጀመሩ ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ።

- ከሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫሉ።

- ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከ5 ሺሕ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

- የግድቡ ግንባታ አሁን ወደ መጠናቀቁ ነው።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት እና ብዙ ቢሊዮን ዶላር ያፈሰሰበት ግድብ ከአፍሪቃ ትልቁ የኃይል ማመነጫ ነው።

ቪድዮ ፦ PM OFFICE

#Ethiopia #AFP

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA

አሜሪካ በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን " የርስ በርስ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው " ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ይህንን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት እንደሆነ ተነግሯል።

ብሊንከን "በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ያሳስበኛል" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶችን ጨምሮ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት የፖለቲካ ውይይት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ " በፕሪቶሪያው ስምምነት እና አፈጻጸሙ ዙሪያ " መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት የሀገራቸው እገዛ እንደማይለያት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊነክን በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና እየተባባሰ ነው ያሉት ውጥረት እንዲረግብም በዚሁ ጊዜ መጠየቃቸውን ተዘግቧል።

#AFP #DW

@tikvahethiopia