TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" በወንጀል ድርጊት እየተሳተፈ ነው የሚል ጥቆማ ደርሶናል " በሚል እጅ ወደላይ ያነሳን ግለሰብ ከኋላ ተኩሶ የገደለው  ፖሊስ በእስራት ተቀጣ።

" የኬብል ስርቆት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚል ጥቆማ ደርሶናል " በሚል ቦታው ላይ ተገኝቶ ሟችን ወንጀል ከፈጸሙት ሰዎች መካከል ነው በሚል በያዘው ታጣፊ ክላሽ ተኩሶ የገደለውና ሟችን በስቶ የወጣው የጥይት እርሳስ አካባቢው ላይ ቆሞ በነበረው ተበዳይ ላይ ጉዳት አድርሶበታል በተባለው ግለሰብ ላይ በፍትህ ሚኒስቴር ክስ መስርቶበት በ9 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ1ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተደርጓል

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ከሆነ ኮ/ል ወንድወሰን ተስፋዬ የተባለው ተከሳሽ በዐቃቤ ሕግ ሁለት ክሶች ቀርቦበታል።

ጥር 16/2014 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሶፍያ ሞል እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ኬብል ስርቆት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚል ጥቆማ ደርሶናል በሚል ቦታው ላይ ተገኝተው ሟች ሱራፌል መስፍን ወንጀል ከፈጸሙት ሰዎች መካከል ነው በሚል ካሯሯጠው በኋላ ደርሶበት በእጁ ትክሻውን እና በእግሩ ታፋውን ከመታው በኋላ ሟች ሁለቱንም እጁን ወደ ላይ ሲያደርግ ይዞት በነበረው ታጣፊ ክላሽ ተኩሶ ከኋላው በኩል ጎኑን፣ ደረቱ እና ሆዱ ላይ በመምታቱ ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።

ከዚህም ባለፈ ፤ ሟችን በስቶት የወጣው የጥይት እርሳስ አካባቢው ላይ ቆሞ የነበረውን ተበዳይ ማቴዎስ ወጋየሁ በግራ ጀርባው አካባቢ በስቶ በመግባት በግራ በኩል ሆዱ በመውጣት ጉዳት የደረሰበት አንጀቱ ክፍል ተቆርጦ እንዲወጣ ሆኗል።

በዚህም የኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር እና 559/2/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈጸመው የግድያ እና በቸልተኝነት ከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሁለት (2) ክሶች ተመስርተውበት በክርክር ሂደት ቆይቷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት የቀረበው ተከሳሽ የተከሰሰበት ክስ በችሎት ተነቦለት " ድርጊቱ ተፈፅሟል ጥፋተኛ ግን አይደለሁም ስርቆት ሲፈፅሙ ነበር እኔንም ሊመቱኝ ነበር " በማለት ቃሉን አስመዝግሿል።

ተከሳሽ ጥፋተኛነቱን ባለማመኑ እንደክህደት ቃል ተቆጥሮ ዐቃቤ ህግ ስለ ጥፋተኛነቱ ማስረጃዎችን በማቅረብ በበቂ ሁኔታ ያረጋገጠ ሲሆን እንዲከላከል በተሰጠው ብይን መሰረት 3 የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ቢያሰማም የዐቃቤ ህግን ምስክሮችንና ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻ ተከሳሹ ይከላከል በተባለበት ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ተብሏል፡፡

ችሎቱም 6 የቅጣት ማቅለያዎችን በመያዝ በሁለቱም ክሶቹ በእርከን 28 ስር በማሳረፍ ተከሳሽን ያርማል በሚል  በ9 ዓመት ጽኑ እስራትና በ1ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
ማዳበሪያ . . .

" ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው

(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው)

" ሰላም ለእናንተ ይሁን !!

አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጥበት ይህን ጥሪ አቀርባለው።

ይህ ጉዳይ በገበሬዎች ላይ የሚያተኩር ነው። ገበሬወች ለማምረት ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ያስፈልጋቸዋል።

በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ለማግኘት በህገወጥ ነጋዴወች በኩል በስንት መከራ በጣም በውድ እንዲገዙ እየተገደዱ ነው።

ይህ ችግር የተፈጠረው #አምና ሲሆን ዘንድሮ ይበልጥ ማዳበሪያ ሚባል ለገበሬወች አልደረሰም።

ገበሬወች እንደሚሉት ከሆነ አሁን ላይ የዘር ወቅት ስለሆነ ከአንዳንድ ነጋዴወች ላይ ኩንታል እስከ አስር ሺህ ብር እየገዛን ነው ብለዋል ፤ ይህ ማለት አንድ ገበሬ አስር ኩንታል ዳፕ ቢፈልግ መቶ ሺህ ብር ሊያወጣ ነው ማለት ነው። ካሁን በፊት የአንድ ኩንታል ዋጋ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር በላይ ሁኖ አያውቅም።

ስለዚህ በኃላ የእህል ምርት አቅርቦት እንዳይቀንስ ከሆዲሁ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማዳበሪያ ቢያቀርብ መልካም ነው።

ይህ ካልሆነ ግን እመኑኝ ቀጣይ አመት የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ከዘንድሮው እጥፍ ይጨምራል።

ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬውች መዳበሪያ ሲጨምርም መንግስትን ልትጠይቁ ይገባል።

በዋነኝነት መንግሥት ልዩ የሆነ ትኩረት ሰጥቶ እንዲቆጣጠሯቸው ምፈልገው የወረዳ አመራሮችን እና የቀበሌ አስተዳዳሪወችን ነው ምክንያቱም እኒህ አመራሮች ከነጋዴወች ጋር በመስማማት ሚገባውን ማዳበሪያ ቀጥታ ነጋዴወች በውድ እንዲሸጡት ይሰጥቸዋል ፤ ለገበሬው ደግሞ #ማዳበሪያ_አልገባም እያሉ የዘር ወቅት ሳያልፍ ከነጋዴ ገዝተው እንዲዘሩ ይነገሯቸዋል።

ስለዚህ ይህን ችግር ለመፍታት ትኩረት መሰጠት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሰወች ጥናት ቢያደርጉበት መልካም ነው።

ትኩረት ለገበሬወች !! "

Via @tikvah_eth_BOT

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
ሶስት ዓመት ያለ መብራት . . .

• " የመብራት መቋረጥ የከፋ የኢኮኖሚ ችግር እየፈጠረብን ነው ፤  ስራ የነበራቸው ሁሉ ስራ ፈላጊ ሆነዋል " - ነዋሪዎች

• " ችግሩ ከወረዳው መንግስት አቅም በላይ ነው። የዞንና የክልል አመራሮች በአስቸኳይ መልስ ይስጡን " - የከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ታደሰ

ለሶስት ዓመታት መብራት የተቋረጠባት የከለላ ወረዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የመፍትሄ ያለ እያሉ ይገኛሉ።

በከለላ ወረዳ የ01 ደገር ከተማ ነዋሪዎች ባለፉት ሶስት ዓመታት የመብራት አገልግልት በመቋረጡ የከፋ ኢኮኖሚያዊ ችግር እየፈጠረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

የከተማ ነዋሪዎቹ አገልግሎት እየሰጠ የነበረው መብራት ከሶስት ዓመት በፊት መቋረጡን ገልጸው በዚህ ምክንያት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማለትም ፦
- በብረታ ብረትና ጣውላ ስራ፣
- በምግብና ሻይ ቤቶች
- በጸጉር ቤቶች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች #ስራቸውን_አቋርጠው ስራ ፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉት የመብራት አለመኖር በሚያከናውኑት የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንደፈጠረባቸውና #የኑሮ_ውድነት እንዲባባስ በማድረግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡

የወረዳው መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን እንዲፈታላቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ይህንን በተመለከተ የከለላ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሴን ታደሰ ፤ በከተማዋ የመብራት አገልግሎቱ መቋረጥ ለተከታታይ ሶስት ዓመታት በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ የፈጠረና በተደጋጋሚ የሚነሳ ጥያቄ ሲሆን የወረዳው መንግስትም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከዞን እስከ ክልል ድረስ በማነጋገር መፍትሄ እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡

" የመብራት መቆራረጡ በከተማው ነዋሪዎች እና በከተማዋ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ " ነው ያሉት ኃላፊው ችግሩ ከወረዳው መንግስት አቅም በላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው የዞን እና የክልል አመራሮች በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጡ አቶ ሁሴን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መረጃው ከከለላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia @tikvah_Eth_BOT
#ethio_telecom

ኪስዎ ሳይጎዳ ወሩን ሙሉ የሚወዷቸው ጋር ደውለው ይጨዋወቱ!

ለዘመድ ለጓደኛዎ እንዲሁም ለስራ አጋርዎ ያለገደብ እንደሻዎ ወሩን ሙሉ የሚጠቀሙበት የድምፅ ጥቅል በ999 ብር ብቻ ከተጨማሪ የፅሁፍ መልዕክት ጋር በቴሌብር እና ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያዎች አንዲሁም *999# ገዝተው ይጠቀሙ።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . .

ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ?

ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ተገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ሁለት / 2 ዓመታት አከራካሪ በሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች በተለይም ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የማሻሻያ ጥናት ማድረጉን አሳውዋል።

በጥናቱም ፦

በ2000 ዓ.ም ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተዘረዘሩት 83 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል 41 የሚሆኑት በስልታዊ የዘፈቀደ ዘዴ (systematic random sampling) ተመርጠዋል ሲል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት የሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ማለትም ፦

👉 የብሔር ብሔረሰቦች ሉዓላዊነት አንቀፅ 8፣

👉 የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣

👉 ብሔራዊ አርማ፣

👉 #ብሔርን መሠረት ያደረገው አስተዳደራዊ ወሰን፣

👉 #መገንጠልን የሚደነግገው አንቀፅ 39፣

👉 የፖለቲካ ፓርቲን #በብሔር_ማደራጀት

👉 #የአዲስ_አበባ_አስተዳደርን በተመለከተ መሻሻል እንዳለባቸው #ሕዝቡ_ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል ብሏል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . . ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ? ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት…
ስለ ሕገ መንግሥት ማሻሻል . . .

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?

" ሕገ መንግሥቱ #ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ክርክር እየተነሳ ይገኛል።

በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ  መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡

በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡  በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል።

ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል። "

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን ምን አሉ ?

" ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበት ሁኔታ አለ።

በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ ይሻሻላል።

391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል። በመሆኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊሆን አይችልም።

ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ  በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል።

የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመሆኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል።

ለምሳሌ ፤ የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች ተሻሽለዋል

ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ።

አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል ይገኝበታል።

ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው ነው።

ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው። ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ ይችላሉ።

በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም ነው። "

#አሚኮ

@tikvahethiopia
ወለንጪቲ . . .

ከአዳማ ከተማ #በ33_ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ወለንጪቲ ከተማ ዛሬ በተኩስ ስትናጥ ነበር።

በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ዛሬ ማክሰኞ ዘለግ ላለ ደቂቃ ከበድ ያለ ተኩስ ሲሰማ እንደነበር አመልክተዋል።

አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ፤ " ከ11:30 አካባቢ አንስቶ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ሲሰማ ነበር " ያለ ሲሆን መልዕክቱን እስከላከበት ሰዓት (ምሽት) ድረስ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ገልጿል።

ባለው ሁኔታ " ለአዳራችን ፈርተናል " ሲል ስጋቱን ገልጿል።

አቢ የተባለ የቤተሰባችን አባል በበኩሉ ከምሽት 12:00 ጀምሮ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲሰማ እንደነበር ጠቁሟል።

የተኩስ ልውውጡ በመንግሥት ፀጥታ አካላት እና መንግሥት " ሸኔ " እያለ በሚጠራቸው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መካከል እንደነበር አመልክቷል።

ይኸው የቤተሰባችን አባል፥ " ከ12 ሰዓት ጀምሮ በቃ በጣም ከባድ ተኩስ ነበር፤ አሁን ላይ ተኩሱ ጋብ ብሏል። ነገር ግን አሁን ላይ አልፎ አልፎ ራቅ ብሎ ወደ ጋራ የከባድ መሳሪያ ድምፀ ይሰማል። " ሲል ሁኔታውን ገልጿል።

" አሁን ላይ ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የለም " ያለው የቤተሰባችን አባል ማምሻውን የነበረውን ሁኔታ ለማስረዳት አጭር የድምፅ ፋይል አያይዞ ልኳል።

" በጣም ከባድ ሁኔታ ላይ ነን " ሲልም ሁኔታውን ገልጿል።

ሌላ የወልጪቲ ቤተሰባችን አባል ደግሞ ፥ " ሁኔታውን በቃላት ከምገልፀው በላይ ነው ፤ የሰዎች ህይወት አልፏል ፤ የተጎዱ ሰዎችም አሉ " ሲል አመልክቷል።

ይህ የወለንጪቲ መስመር እጅግ በጣም ወሳኝ ከሚባሉ የሀገራችን ቁልፍ የንግድ መስመሮች አንዱ ሲሆን በዚሁ መስመር በተደጋጋሚ ጊዜ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩ ፣ #ግድያን ጨምሮ ዘረፋ ፣ እገታ እጅግ የለየለት ወንጀል እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ መጠቆሙ የሚታወቅ ነው።

ከጥቂት ቀናት በፊት በዚሁ ቀጠና ላይ ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ " ወለንጪቲ " አካባቢ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማን እና ወንድማቸውን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች መገደላቸው መነገሩ አይዘነጋም።

Via @tikvah_eth_BOT

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ አደጋ ውስጥ የሚከት ነው " - ህወሓት

ህወሓት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አልቀበልም አለ።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከቀናት በፊት ምርጫ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

የምርጫ ቦርድን ውሳኔ " አልቀበለውም " ያለው ህወሓት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እወያይበታለሁ ብሏል።

የምርጫ ቦርድም ውሳኔውን እንደገና በማጤን የፕሪቶርያ ስምምነትና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ያስተላለፉትን ውሳኔዎች መነሻ በማድረግ እንዲያስተካክል ጠይቋል።

ህወሓት የሰላም ስምምነቱ ባለቤት ናቸው ያላቸው የድርጅቱ አባላት፣ የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የቦርዱ ውሳኔ የሰላም ሂደቱ ኣደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑ በመገንዘብ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የፌደራል መንግስትም " ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ በተጀመሩት አወንታዊ የሰላም እና የመደጋገፍ ጥረቶች ላይ ሊያሳድረው የሚችል አላስፈላጊ ጫና እንዲሁም የፌደራል መንግስቱ ህጋዊ ውሳኔዎችን እና ስምምነቶችን #በሁሉም የመንግስት ተቋማት እና አካላት እንዲከበሩ የማድረግ ኃላፊቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የቦርዱን ውሳኔ እንደገና ታይቶ ከህወሓት ህጋዊ ሰውነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ያሉትን ህጋዊና ፖለቲካዊ አማራጮች ተጠቅሞ ነገሮች ቅድመ-ጦርነት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ በሚያደርግ ቀና አካሄድ እንዲፈቱ እንዲያድረግና የፕሪቶርያ ስምምነት በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተጀመረውን የሰላም ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲያደርግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

(የህወሓት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#big5construct

Tomorrow it is!  Ethiopia’s largest construction event - Big 5 Construct Ethiopia kicks off tomorrow. Join us tomorrow at
11:00 AM to explore the future of construction.

Be a part of our Telegram group for regular updates: https://t.iss.one/big5ethiopia 
Register for your free pass using the link: https://bit.ly/3oI8P6L  📍 Millennium Hall, Addis Ababa 📅 18 – 20 May
#ብርሃን_ባንክ

የብርሃን ባንክ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ አርኪቴክቸራል ዲዛይን ውድድር የቀረቡ ዲዛይኖች ለህዝብ ዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ኤግዚቢሽኑ የባንኩ የስራ አመራሮች በተገኙበት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከግንቦት 5 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ልደታ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ኮሌጅ ጊቢ ውስጥ ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን ለሚቀጥሉት 15 ቀናት የሚቆየውን ኤግዚቢሽን እንድትመለከቱ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

https://t.iss.one/berhanbanksc