TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማዳበሪያ . . .

" ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው

(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው)

" ሰላም ለእናንተ ይሁን !!

አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጥበት ይህን ጥሪ አቀርባለው።

ይህ ጉዳይ በገበሬዎች ላይ የሚያተኩር ነው። ገበሬወች ለማምረት ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ ያስፈልጋቸዋል።

በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ለማግኘት በህገወጥ ነጋዴወች በኩል በስንት መከራ በጣም በውድ እንዲገዙ እየተገደዱ ነው።

ይህ ችግር የተፈጠረው #አምና ሲሆን ዘንድሮ ይበልጥ ማዳበሪያ ሚባል ለገበሬወች አልደረሰም።

ገበሬወች እንደሚሉት ከሆነ አሁን ላይ የዘር ወቅት ስለሆነ ከአንዳንድ ነጋዴወች ላይ ኩንታል እስከ አስር ሺህ ብር እየገዛን ነው ብለዋል ፤ ይህ ማለት አንድ ገበሬ አስር ኩንታል ዳፕ ቢፈልግ መቶ ሺህ ብር ሊያወጣ ነው ማለት ነው። ካሁን በፊት የአንድ ኩንታል ዋጋ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር በላይ ሁኖ አያውቅም።

ስለዚህ በኃላ የእህል ምርት አቅርቦት እንዳይቀንስ ከሆዲሁ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማዳበሪያ ቢያቀርብ መልካም ነው።

ይህ ካልሆነ ግን እመኑኝ ቀጣይ አመት የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ ከዘንድሮው እጥፍ ይጨምራል።

ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬውች መዳበሪያ ሲጨምርም መንግስትን ልትጠይቁ ይገባል።

በዋነኝነት መንግሥት ልዩ የሆነ ትኩረት ሰጥቶ እንዲቆጣጠሯቸው ምፈልገው የወረዳ አመራሮችን እና የቀበሌ አስተዳዳሪወችን ነው ምክንያቱም እኒህ አመራሮች ከነጋዴወች ጋር በመስማማት ሚገባውን ማዳበሪያ ቀጥታ ነጋዴወች በውድ እንዲሸጡት ይሰጥቸዋል ፤ ለገበሬው ደግሞ #ማዳበሪያ_አልገባም እያሉ የዘር ወቅት ሳያልፍ ከነጋዴ ገዝተው እንዲዘሩ ይነገሯቸዋል።

ስለዚህ ይህን ችግር ለመፍታት ትኩረት መሰጠት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ሰወች ጥናት ቢያደርጉበት መልካም ነው።

ትኩረት ለገበሬወች !! "

Via @tikvah_eth_BOT

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia