ሃሳብን መግለፅ ... በጥሩ ቃላት !
ሁሉም ሰዎች ከእኔ / እኛ ጋር አንድአይነት ወጥ የሆነ አመለካከት፣ አስተሳሰብ ይኖራቸዋል ብሎ መጠበቅ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው።
ነገር ግን ከእኛ ጋር የሚቃረን ሃሳብ በተመለከትን ወቅት ለዛ ግብረመልስ የምንሰጥበት መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
ይህን ለማለት መነሻ የሆነን የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፍፁም ከመስመር የለቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ነው።
እኛ ያልደገፍነው ወይም ከእኛ ጋር የማይስማማ / ያላሳመነን ሀሳብ ስንመለከተ ከሰዎች ጋር እልህ እና ንትርክ፣ ጥላቻ ውስጥ በማያስገባ ቃላት በመጠቀም ሀሳባችንን ብንገልፅ የተሻለ ነው።
ለምሳሌ ፦
አንድ የግለሠብ ሃሳብ / ማንኛውም አይነት ዜና / መረጃ / ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ብንመለከት እና ያን ነገር ፍፁም በእኛ ዘንድ ተቀባይነት ባይኖረው እንዲህ በሚል ሃሳባችንን ብንገልፅስ ...
• ንግግሩ / መረጃው ሀሰት ከሆነ ፤ " ይህ ፍፁም ሀሰት ነው ፤ እኔ ይህ ሀሰት ስለመሆኑ በቂ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ " በሚል የኛን ማስረጃና ሃሳብ ማቅረብ።
• ሃሳቡን ካልደገፍነው / ካልወደድነው ፤ " እኔ ይህንን ሀሳብ በፍፁም አልደግፈውም / አልወደድኩትም ምክንያቱም ... ይህ ይህ ስለሆነ " ብንል።
• ጥላቻን የሚሰብክ መልዕክት ከሆነ ፤ " ይህ በእኔ አመለካከት ጥላቻን የሚሰብክ ስለሆነ አመለካከትህን ብታርም እና ቀና አመለካከት ብትይዝ " በሚል ወንድማዊ ምክር ብንለግስ።
በእርግጥ ያለንበት ሁኔታ በብዙ የሚያበሳጭ ፣ የሚያቆስል ፣ የሚያናድድ ጉዳዮች የተሞላ ቢሆንም በሌሎችም ጉዳዮች ሃሳብ ስንገልፅ እርስ በእርስ ለመግባባት ፣ ለመተራረም እና አብሮነትን ለማጠናከር በሚያግዙ ቃላት ብንመላለስ በትንሹም ቢሆን ሰላማዊ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መፍጠር ይቻላል።
ማንም ሰው እራሱንም ሆነ ሰውን እንዲሁም የገዛ ሀገሩን እስካልጎዳ፣ ሌላውን እስካልበደለ ድረስ የፈለገውን ሀሳብ የማራመድ መብት ቢኖረውም ያንን የሚገልፅበት መንገድ ነገ የተሻለ ለውጥን ሊያመጣ በሚችል መልኩ መሆን አለበት።
ተቃራኒ ሃሳብ ስንመለከተ ዘለን የገለሰቡን ብሄርን ፣ ማንነትን በመተንኮስ፣ በጥላቻ እንዲሁም በእልህ በፍረጃ የምንሰጠው ሃሳብ ችግር ከመፍጠር እና ከማባባስ ውጭ የሚፈይደው ነገር አይኖርም።
ሃሳብ እና አስተያየት የምንሰጥባቸው ቦታዎችን መምረጥ ተገቢ ነው ፤ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ፣ በፖለቲካውም ላይ ፣በትምህርቱም ላይ ... እየገቡ ከሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ ጋር መጋጨት እና መነታረክ ከምንም በላይ ለራስ ጤና ጎጂ ነው።
በጅምላ / ሌሎች ሰዎች ስለፃፉ ብቻ ሳይሆን ስለምናውቀው ጉዳይ በተሻለ ቃላት ሃሳባችንን የሚገባው ቦታ ላይ ብናስቀምጥ በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ያሉ በርካቶችን መለወጥ ይቻላል።
እዚህ ጋር ልብ ማለት የሚገባው ፦ በማህበራዊ ሚዲያው ሆን ተብለው ለጥላቻ ፣ ለግጭት ፣ ሰዎችን ለማበሳጨት እና ስሜታዊ ለማደርግ የሚከፈቱና ሁሉም ገፆች ላይ እየገቡ የሚፅፉ በርካታ ሀሰተኛ አካውንቶች መኖራቸውን ነው።
#tikvahfamily
@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT

TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ ስደተኞች ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14…
#ኢትዮጵያ #ሱዳን #መተማ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ፤ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በመሸሽ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ድንበር አቋርጠው ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሆነ አሳውቋል።
ይህ ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው ብሏል።
እስካሁን በሱዳን ጦርነት ምክንያት #በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥርም በአጠቃላይ ከ12 ሺ በላይ መድረሱ ተመላክቷል።
ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ በኩል ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ካሉት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎች እንደሚገኙበት የመንግሥታቱ ድርጅት መሥሪያ ቤት መረጃን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቢግ5_ኮንስትራክት_ኢትዮጵያ
በፈጣን ዕድገት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ጉዞ ለመቃኘት ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት ትክክለኛው መድረክ ነው፡፡
የተቋራጭ ባለቤት፣መሃንዲስ ፣ አርክቴክት አልያም በግንባታ ኢንደስትሪ ዙሪያ የተሰማሩ ከሆነ ይህን አጓጊ አለም አቀፍ እድል ለመቀላቀል አሁኑኑ በነፃ ይመዝገቡ : https://bit.ly/3oI8P6L
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/

#GreatBokojiRun
ለ2015ቱ ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ ዛሬውኑ ይመዝገቡ!
ግንቦት 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚካሄደውን ውድድር በመቀላቀል ይጓዙ፣ ይጎብኙ፣ ሀገርዎን ይወቁ!
የሩጫ መመዝገቢያ ዋጋ: 350ብር 🗣 ሙሉ መረጃ ልማግኘት 👉https://drive.google.com/file/d/1O_Y33f6mugB7zl_IDcK9mVsOna9co4Vm/view?usp=sharing
☎️ +251116635757/+251116185841
#2023GreatBokojiRun #EthioTelecom #LandofOrigins

#ኦፌኮ " ብልፅግና ፓርቲ ለፈፀመውና እየፈፀመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ፓርቲው እራሱ ነው፤ በዚህ ምክንያት የኦሮሞን ህዝብ ስም ማጥፋት ትክክል አይደለም " - የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በ2014 ዓ/ም 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ካካሄደ በኃላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፤ ገዢውን ብልፅግና ፓርቲ እንደ ኦሮሞ መንግሥት በመቁጠር ፓርቲው የተሳሳተውን ስህተት እና ህገወጥ ተግባር…
" በካድሬዎች አስተዳደር የኢትዮጵያ መሰረታዊ ችግር አይፈታም " - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
የኦሮሞ ፋደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ትላንት ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ነበር።
አንዱ ጉዳይ የነበረው ስለ " ሽግግር መንግሥት " ነው።
የኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላምና መረጋጋት ይፈልጋሉ ፤ ደሞክራሲያዊ አስተዳደር ይፈልጋሉ ፤ ትርጉም ያለው ልማትና ብልጽግና ይፈልጋሉ ያሉት ሊቀመንበሩ ሆኖም ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ቁጭ ብለው ተስማምተው እንዴት እንለውጥ ፤ ምን እናድርግ የሚለው ላይ አይስማሙም ሲሉ ገልጸዋል።
" በተለይ፥ የአሁኑ መንግስት ሽግግር መንግስት የሚለውን ለምን እንደሚፈራ እንደሚሸሽ አላቅም።" ያሉት ፕ/ር መረራ፤ " ሽግግሩን ከጠሉ በፈለጉት ስም ይጥሩት ግን ሁላችንንም የሚያቅፍ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያምንበት የኔ ነው የሚለው መንግስት በጣም ወሳኝ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፥ "ላለፉት 50 ዓመታት የኢትዮጵያ የሽግግር ምንድን ነው? ከአንድ ቀውስ ወዴሌላ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ ሲሸጋገር ነው የኖረው ስለዚህ አንድ ቦታ ላይ አቆቁመን ሁላችንንም በእኩልነት የምታስተናግድ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመፍጠር ነው ሌላ የተደበቀ አጀንዳ የለንም።" ብለዋል።
" በዚህ ሀገር ዘላቂ የሆነ ሰላምና መረጋጋት ከምን ይመጣል፣ ሀቀኛ የሆነ የፌደራል ስርዓት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዴት ይመጣል፣ ትርጉም ያለው ልማትና ብልጽግና መምጣት በሚችልበት መንገድ የሀገሪቱ ፖለቲካ ካልተዋቀረ በስተቀር በግልጽ ቋንቋ የካድሬዎች አስተዳደር የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግር አይፈታም " ነው ያሉት።
በሌላ በኩል ፤ አቶ ሀምዛ አዳነ (የኦፌኮ ምክትል ዋና ፀሀፊ) የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) በታንዛኒያው የመጀመሪያ ምዕራፍ የሰላም ድርድር ወቅት " የሽግግር መንግስት " ን በተመለከተ ጥያቄ አቅርቧል የሚል ጉዳይ ተነስቶላቸው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
አቶ ሀምዛ ፤ " የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽግግር መንግሥት ጥያቄን አቅርቧል የሚል ግልጽ የሆነ ያየነው ነገር የለም " ያሉ ሲሆን " ቢጠየቅም በድርድር ሂደት ውስጥ ብዙ ፌዞች ሊኖር ይችላል፤ በአጭሩ በታንዛኒያ የተደረገው ድርድር በጥሩ መልኩ መከናወኑን ነው መረዳት የቻልነው በቀጣይም ይቀጥላል " ብለዋል።
በመሀከላቸው ሰፊ ልዩነት እያለ ይህ ድርድሩ ይሳካል ወይ ? ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄም አቶ ሀምዛ " ድርድር ሲደረግ ከመጀመሪያው በመሀከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እና ወደ ሰላሙ ጉዞ ለመምጣት ነው ትልቁና ከባዱ ነገር ወደዚህ የሰላም ጉዞ መምጣት ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ቪድዮ ፦ በአሜሪካ ሀገር ቴክሳስ በምትሰኝ ግዛት በምትገኘው " አለን " ከተማ አንድ ታጣቂ በገበያ አዳራሽ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት ስምንት (8) ሰዎችን በጥይት ገድሏል።
በታጣቂው ከተገደሉት ውስጥ #ሕጻናት ይገኙበታል።
ከተገደሉት በተጨማሪ ሰባት (7) ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ህክምና እየደረገላቸው ሲሆን፣ ከመካከላቸው 3ቱ በጽኑ የተጎዱ ናቸው።
ታጣቂው በጅምላ ባገኘው ሰው ላይ በከፈተው ተኩስ ግድያውን የፈጸመ ሲሆን፣ በገበያ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ እንዲወጡ ተደርገዋል።
ታጣቂው እዚያው ጥቃቱን በፈጸመበት ስፍራ በፖሊሶች ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን፣ ጥቃቱን የፈጸመው ብቻውን እንደሆነ እንደሚታመን ቢቢሲ ዘግቧል።
እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።
ቪድዮ ፦ Fox News

#NBE
በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ አስቀማጮች ዋስትና ለመስጠት የተቋቋመው የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ እስከ 200 ሺሕ ብር ተቀማጭ ገንዘብ ላላቸው ዋስትና እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡
ባንኮች እና የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በየዓመቱ ከተቀማጭ ገንዘባቸው 0.2 በመቶ ለፈንዱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተከታዩን ብለዋል ፦
" በየባንኩ ለእያንዳንዱ አስቀማጭ እስከ 200 ሺሕ ብር ለሚሆን ተቀማጭ ገንዘብ የዋስትና ሽፋን ይሰጣል፡፡
የመድን ሽፋኑ መጠን እስከ 200 ሺሕ ብር ለሚሆነው ተቀማጭ ገንዘብ የዋስትና ሽፋኑ እንዲሰጥ የተወሰነው፣ 96 በመቶ ያህል አስቀማጮች የተቀማጭ ገንዘባቸው መጠን የተጠቀሰውን ያህል ስለሆነ ነው።
በዚህ መሠረት የመድን ሽፋኑ ይሰጣል። ይህ ውሳኔ አብዛኞቹን አስቀማጮች የሚሸፍን ነው።
ባንኮች ለዚህ ዋስትና ሽፋን ተቀማጭ የሚያደርጉት በየዓመቱ ከጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘባቸው 0.2 በመቶ የሚሆነውን በማስላት ለፈንዱ ገቢ በማድረግ ተፈጻሚ ይሆናል።
የተቀማጭ ገንዘብ ዋስትና ፈንድ አገልግሎት ሲጀመር ባንኮቹ የሚከፍሉት ክፍያ ይኖራል። የገንዘቡ መጠን ግን ገና አልተወሰነም ። "
More : https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-05-07
#ሪፖርተር

የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር ተገደሉ።
ከትላንት በስቲያ ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አሳውቋል።
ጥቃቱን " አሸባሪዎች " ናቸው የፈፀሙት ያለው የአፋር ብልፅግና " በፈፀሙት ድንገተኛ ጥቃት የአቶ ኡመር ለማን ህይወት ቀጥፈዋል ብሏል።
ፅ/ቤቱ ባሰራጨው መረጃ ጥቃት አድራሾቹ ላይ የተወሰደ እርምጃ ይኖር እንደሆነ እና ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በሌሎች ላይ ጉዳት ደርሶ እንደሆነ በዝርዝር ያሳወቀው ነገር የለም።
ከዚህ ቀደም በዚሁ ቀጠና እጅግ የለየለት የወንጀል ተግባር በታጠቁ አካላት እንደሚፈፀም ሲገለፅ እንደነበር ይታወሳል።
በዚሁ መስመር ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱና እንደ ከተማዎች ውስጥ በመግባት ጭምር ሰላማዊ ሰዎችን መግደል፣ በየመንገዱ ሰላማዊ ሰዎችን እያገቱ ከፍተኛ ገንዘብ የመጠየቅ ፤ በአጠቃላይ በቀጠናው ወጥቶ ለመግባት ከፍተኛ ስጋት የመፍጠር እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።
መንግሥት ይህንን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነና ዜጎች ቀንም ማታም ያለስጋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ቀጠና ይህን ያህል ጊዜ #ሙሉ_በሙሉ ከታጣቂዎች እንቅስቃሴና የወንጀል ተግባር ነፃ ማድረግ ለምን እንዳልቻለ የብዙሀኑ ጥያቄ ነው።
እስከ ዛሬ ድረስ በንፁሃን ላይ ሲፈፀሙት ለነበሩት ጥቃቶች ፣ ዝርፊያዎች ወንጀለኞቹ መቼ ነው ወደ ፍርድ አደባባይ የሚቀርቡት ? መቼስ ነው ፍትህ የሚሰጠው ? የሚለውም ጉዳይ መልስ ይፈልጋል።

#EHRC
" ... ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን ሪፖርት ለህ/ተ/ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።
በዚህም ወቅት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ በአማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አሳሳቢ እንደሆኑ ቀጥለዋል ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ አንስቶ መንግሥት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ በአሁን ወቅት በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ #በሲቪል ሰዎች ላይ ፦
- የሞት፣
- የንብረት መውደም፣
- የመፈናቀል ጉዳት መድረሱን በዚህም የሰብዓዊ መብት ስጋቱም መቀጠሉን አንስተዋል።
" መንግሥት የፀጥታ እርምጃ በአማራ ክልል በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል ፤ " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል " ነገር ግን ይህ ወታደራዊ እርምጃ የሰብዓዊ መብት እንድምታ ስላለው ፣ የሰብዐዊ መብት ተፅእኖ ስለሚፈጥር ይሄን በቅርበት እየተከታተልን ነው " ብለዋል።
" እስካሁን ባለው መረጃ በመነሳት ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋ ስለሆነ ኢሰመኮ #ውይይት እና #ሰላማዊ መፍትሄ አስፈላጊነትን አበክሮ በማሳሰብ ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል። " ሲሉ አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ዳንኤል ባቀረቡት ሪፖርት የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ሲታሰሩ የሚያዙበት መንገድ፣ ለሰብዓዊ ጉዳዮች አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
ዶ/ር ዳንኤል ፤ " በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀመው የዘፈቀደ እስር እና በእስር ወቅት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች / አንዳንድ ቦታዎች ድብደባን ጨምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እስራት እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመከበርም ቀጥሏል " ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚፈፀሙት የዘፈቀደ እስሮች #የቤተሰብ አባላትን ጭምር ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው ሲሉ ለፓርላማው በሪፖርታቸው አሳውቀዋል።

#ትፈለጋለች
በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ አንዲት እንጀራ እናት ሁለት ልጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደሏ እየተፈለገች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ስለጉዳዩ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ምን አሉ ?
ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ፦
" ወንጀሉ የተፈፀመው ቅዳሜ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም. በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሦስተኛ ቡራዩ በሚባል ስፍራ ነው።
ወንጀሉ የተፈፀመው ሌሊት ነው። ሁለት ሕጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ በእንጀራ እናታቸው ተገድለዋል ተገኝተዋል።
ተጠርጣሪዋ ነጋሴ ከበደ ብሩ የምትባል ስትሆን፣ የባለቤቷን ሁለት ልጆች አንገታቸውን ቀልታ፣ በተኙበት ብርድ ልብስ አልብሳ እሳት ለኩሳባቸው አምልጣለች። "
የልጆቹ አባት የሆኑት አቶ ጌታሁን ባልቻ ምን አሉ ?
በአካባቢው የሚገኝ ቄራ የሚሰሩ ሲሆን ግድያው በተፈፀመበት ዕለት ማምሻውን ከባለቤታቸው ጋር በልጆቻቸው ጉዳይ ተነጋግረው እንደነበር ገልጸዋል።
አቶ ጌታሁን ባልቻ ፦
" በልጆቼ ጉዳይ ተነጋግረን ነበር። በዚህም ምክንያት እንለያይ ተባብለን፤ እርሷም ‘እኔ እሄዳለሁ፣ አንተ እዚህ ትኖራለህ’ አለችኝ።
ምሽት ላይ ስንነጋገር ዛቻም ሆነ ለእንደዚህ አይነት አሰቃቂ ድርጊት ያበቃል ብዬ የምጠረጥረው ጠቋሚ ነገር አላየሁም።
ሌሊት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ወደ ቤት ስመለስ የቤቱ በር ክፍት ነበር። ወደ ውስጥ ስገባ እሳት ይነዳል። ልጆቼን አልጋ ላይ ሳያቸው ጭሱ አፈነብኝ ብዬ ሮጬ ወደ ውጪ አወጣኋቸው። በወቅቱ ትልቁ ልጄ ተቃጥሏል። ትናሿ ልጄንም አወጣኋት። ወደ ውጪ ካወጣኋቸው በኋላ እነርሱ ላይ ወድቄ ራሴን ሳትኩኝ።
ልጆቼን መጀመሪያ ሳያቸው በሕይወት ያሉ መስሎኝ ነበር ፤ ያሟሟታቸውን ሁኔታ ራሴን ከሳትኩበት አንድ ቀን በኋላ ነው ከአካባቢ ነዋሪዎች እና ከፖሊስ የሰማሁት።
ልጆቼን ማሳደግ እፈልጋለሁ እንለያይ አልኳት. . . እኔ እሄዳለሁ አንተ እዚህ ትኖራለህ አለችኝ። ይህንን ብቻ ነው የተናገረችኝ። እንደዚህ ዓይነት ድርጊት በልጆቼ ላይ፣ ቤተሰቤ ላይ፣ እንስሳትም ላይ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም። "
በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት የአቶ ጌታሁን ልጆች አንደኛው የ13 ዓመት ወንድ ሲሆን፣ ሌላኛዋ ደግሞ የ4 ዓመት ተኩል ሴት ናቸው።
ሁለቱም አንገታቸው ተቀልቶ ነው የተገደሉት።
አቶ ጌታሁን በ2013 ዓ.ም የልጆቻቸውን እናት በሞት ካጡ በኋላ ባለፈው ታኅሣሥ ነበር ከተጠርጣሪዋ ጋር የተጋቡት።
ሲጋቡም የልጆቻቸውን ሁኔታ ገልፀው፣ ተማምነው ነበር የተጋቡት።
ከዚያ በኋላ እዚያው ቡራዩ አካባቢ " ሽሮ ቤት " ከፍታ ስትሰራ ቆይታለች።
ነዋሪነቷም እዚያው ቡራዩ አካባቢ ኤጀርሳ ጎሮ የሚባል አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዋ እየተፈለገች ነው ...
ፖሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ የሁለት ህፃናትን ነፍስ ያጠፋችውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እያፈላለጋት ይገኛል።
በቁጥጥር ስር የዋሉ የቤተሰቦቿ አባላትም አሉ።
ከሰበታ እስከ አንቦ ድረስ ከተጠርጣሪዋ ጋር የሚመሳሰሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችም አሉ።
መረጃው #የቢቢሲ_አማርኛ እና የቡራዩ ፖሊስ ነው።

#big5construct
በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ላይ በመሳተፍ ታላላቅ የግንባታው ዘርፍ ተቋማትንና ባለሙያዎችን ያግኙ።
ልዩ ልዩ የግንባታው ዘርፍ አዳዲስ ፈጠራዎችን እና ዘላቂነት ያላቸው መፍትሔዎችን እንዲሁም የወደፊቱን የኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ አቅጣጫ አብረውን ያቅዱ!
የንግድ እና የግንባታ ፍላጎቶችዎን የሚያሟሉ ከ100 በላይ የሀገር ውስጥ እና ዓለምአቀፍ ተቋማት እና ባለሙያዎችን ለማግኘት ዕድሉን ይጠቀሙበት!
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/big5ethiopia

#አቢሲንያ_ባንክ
አፖሎን ተጠቅመው ቪዛ ካርድ ሲያዙ በ72 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በተመችዎት ቦታ ካርድዎን እናደርስሎታለን።
መተግበሪያውን ኣውርደው ካርድዎን ይዘዙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all