TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መተማ

የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ናቸው የተባሉና በመተማ ዮሐንስ በኩል ጭነት ይዘው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ ሲሉ እንዲቆሙ በተደረጉ አምስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ ገለጸ።

ትናንት ከሰዓት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ አምስት የመከላከያ ሠራዊት ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ መተማ ዮሐንስ ላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ ታግደው እንዳያልፉ መደረጋቸውን በስፋት እያነጋገረ ይገኛል።

ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎችና ፎቶግራፎች እንደሚጠቁሙት ጭነት የያዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቂት በማይባሉ ሰዎች ተከበው መንገድ ዳር እንደቆሙና የአካባቢው ባለስልጣናትም ስለጭነቱ ህጋዊነት ለማወቅ የማጣራት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ያመለክታሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Metema-08-19
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አማራ ክልል!

የሱዳን አዋሳኝ በሆነው የምዕራብ ጎንደር ዞን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የመከላከል ስራው 'ከክልሉ አቅም በላይ' መሆኑን የአማራ ክልል የኮሮና መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል አስታውቋል።

የአማራ ክልል ም/ርዕስ መስተዳደርና የኮሮና መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በተለይ የሱዳን አዋሳኝ በሆነው የምዕራብ ጎንደር ዞን #መተማ አካባቢ ችግሩ አሳሳቢ እንደሄነ ግብረ ኃይሉ በቦታው ተገኝቶ መመልከቱን ተናግረዋል።

ሁሉንም ወደክልሉ የሚገቡ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ለማስገባት እና ለጤና ባለሞያዎችም ሆነ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገቡት አስፈላጊ 'ግብአቶችን ማሟላት' ከክልሉ አቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ በአካባቢው የአደጋ ምላሽ ማዕከላት እንደሚያስፈልግ ግብር ኃይሉ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው 235 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው አስር (10) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

አስሩም (10) ወንድ ሲሆኑ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው። የእድሜ ክልላቸው ከ24 እስከ 50 ዓመት ውስጥ ይገኛል። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና #መተማ ለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 97 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 3 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 3 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል 2,792 የላንራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ አንድ መቶ አስራ ስምንት (118) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 23 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ምዕራብ_ጎንደር

በሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች ከግጭቱ በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን #መተማ_ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች ትገኛለች።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ የፍቅር ከተማ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህ የጦርነት ስጋት ሽሽት ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።

መረጃ / ፎቶ፦ የምዕራብ ጎንደር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ  ስደተኞች ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14…
#ኢትዮጵያ #ሱዳን #መተማ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ፤ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በመሸሽ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ድንበር አቋርጠው ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሆነ አሳውቋል።

ይህ ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው ብሏል።

እስካሁን በሱዳን ጦርነት ምክንያት #በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥርም በአጠቃላይ ከ12 ሺ በላይ መድረሱ ተመላክቷል።

ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ በኩል ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ካሉት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎች እንደሚገኙበት የመንግሥታቱ ድርጅት መሥሪያ ቤት መረጃን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia