ሰሞነኛው ዝናብ ...
በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ፥ ጎፋ ዞን ዑባ-ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ቀበሌ በጣለው ከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 21 ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
በህይወት የተረፉ ዜጎ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲጠለሉ የተደረገ ሲሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱ ተሰምቷል።
ተጎጂ ወገኖችን ለመደገፍም በዞኑ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።
#Amhara
በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ 02 አዋተል ቀበሌ ሚያዚያ 27/2015 ዓ.ም ምሽት ለተከታታይ 30 ደቂቃ የጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በእንስሳት፣ በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከ37 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።
#Gambella
በጋምቤላ ክልል ፤ በዲማ ወረዳና አጎራባች ወረዳዎች ከሚያዝያ 25 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እየጣለ ባለው ሃይለኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ በሚሊየን የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
የጎርፍ አደጋው እስካሁን ባለው መረጃ በወረዳው ከ70 በላይ መኖሪያ ቤቶች በውሃ ያጥለቀለቀ ሲሆን በሰብል ላይም ጉዳት አድርሷል።
ጎርፉ በዲማ ከተማ ወንዝ ዳር የነበረውን የከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ መሳቢያ ጀነሬተርና ፖምፕ ግንብ ቤቱን ጨምሮ በሚሊዮን በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ታውቋል።
በዚህም ችግር ሳቢያ የከተማው ንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መቆሙ ተነግሯል።
በተመሳሳይ በዲፕ (መርከስ) ቀበሌ የሚገኘው የእኩጉ ስደተኞች መጠለያ ጣብያና የአካባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት መሳቢያ ጀነሬተሮች በጎርፍ መወሰዱ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም የአኮቦ ወንዝ እስከጫፉ ድረስ በመሙላቱ ዲማ ወረዳን ጨምሮ ሁለት አጎራባች ወረዳዎች የሚያገናኝ የአኮቦ ብረት ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።
በደረሰው አደጋ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማገዝ የክልሉ መንግሥትን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
መረጃ ምንጮች ፦ የጎፋ ዞን ፣ የለገሂዳ እና የዲማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ናቸው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም አለን " - አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) መንግስት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ለመጠየቅ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅዶ የነበር ቢሆንም መንግሥት ሰልፉን እንዳይደረግ መከልከሉን አሳውቋል። የኮንፌደሬሽኑን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ እንዳሳወቁት ፤ ዛሬ የሚከበረውን የሰራተኞች…
መንግሥት የከለከለው ሰልፍ ...
በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ በአደባባይ ሊከበር የነበረው የሰራተኞች በዓል (ሜይዴይ) በመንግስት መከልከሉ ይታወሳል።
በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ምን አሉ ?
አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦
" የእኛ አላማ የነበረው የሰራተኛውን ጥያቄ ይዘን በመላው ከተማ ሳይሆን በመስቀል አደባባይ ብቻ ማክበር እና ጥያቄዎቻችንን በሰላም ማቅረብ ነበር።
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊዋ ግን ከበአሉ አንድ ቀን በፊት እሁድ ምሽት ይህን ማድረግ እንደማንችል ነገሩን፣ የሰራተኞች ቀንን ልታከብሩ ሳይሆን መንግስትን ልትጠይቁ አስባችኋል፣ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም ተብለናል። እንዲህ ብለው ተቆጡ፣ መጥቼ በአካል ላስረዳ ብልም አልቻልኩም፣ ደንብ እናስከብራለን ከፈለጋችሁ ሚሊኒየም አዳራሽ ሂዱ አሉኝ።
ልናቀርባቸው የነበሩት ሶስት ጥያቄዎች ፦
1. በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው እየተቸገረ ነው፣ በተለይ ደግሞ ደሞዝ ተከፋዩ። መንግስት መፍትሄ ይስጠን። አብዛኛው ሰራተኛ በቀን አንዴም ለመብላት እየተቸገረ ነዉ።
2. የስራ ግብር ይቀነስልን።
3. የዛሬ አራት አመት ወጥቶ የነበረው የዝቅተኛ ደሞዝ ማስተካከያ አዋጅ እስካሁን ደንብ ሳይወጣለት ቆይቷል። ይህም ትኩረት ይሰጠው፣ በ600 ብር እየኖረ ያለ ሰው አለ፣ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ደሞዝ በአማካኝ ከ800 - 1,200 ብር ነው።
4. የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ከደምበኛቸው ከሚቀበሉት ክፍያ ለሰራተኛው 80 ፐርሰንት ከፍለዉ ቀሪውን 20 ፐርሰንት እንዲወስዱ በሚል የወጣዉ መመሪያ አለመከበር በኤጀንሲ በተቀጠሩ ሰራተኞች ላይ ተመልካች ያጣ የጉልበት ብዝበዛ እየተካሄደ ነው፣ መንግስት ትኩረት ያርግበት የሚል ነው።
እነዚህን ህገ-መንግስታዊ እና የመብት ጥያቄዎች ለማቅረብ ብንፈልግም ተከልክለናል። "
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
ምስል /ተ.ቁ. 2 - አዲስ ማለዳ ጋዜጣ/

#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ሞባይል ባንኪንግን (*881#) ተጠቅመው :-
- የአየር ትኬትዎን ይቁረጡ!
- ያለ ኢንተርኔት በቀላሉ ገንዘብ ያስተላልፉ!
- የት/ቤት ክፍያዎን በቀላሉ ይክፈሉ!
- ከራስዎ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ገንዘብ ያስተላልፉ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

#MyWishEnterprise
DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።
• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT
0913356384 / 0912710661 0910626917 / 0928414395
0911606068 / 0922475851 0935409319 /0911602664

" እየተከናወነ የሚገኘው የአማራን ሕዝብ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት
የአማራ ክልላዊ መንግሥት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።
የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፥ በክልሉ የተወሰኑ አካባቢዎች በተመረጠ ሁኔታ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።
" ይህ የህግ ማስከበር ስራ እየተሰራ ያለውም የሰላም አማራጭ ገፍተው መንግሥትን ደካማ ለማድረግ እና ለመገዳደር የሞከሩ ቡድኖች ላይ ነው " ብሏል።
የክልሉ መንግሥት ፤ የሕግ ማስከበር እርምጃው በጣም ውስን በሆነ የክልሉ አካባቢዎች የሚደረግ እንጂ ሁሉንም የክልሉ አካባቢዎች የሚመለከት አይደለም ሲል አስገንዝቧል።
የአማራ ክልል መንግሥት ፤ ጽንፈኛ ናቸው ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እንደሚሉት የክልሉ ሕዝብ " በሕዝባዊ እምቢተኝነት ውስጥ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት " ብሏል።
" እንደውም ሕዝባችን በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ፤ ሠርቶ እንዳይበላ ለማድረግ የሚሞክሩትንና ከሰላማዊ አማራጮች ጋር የተፋቱትን ቡድኖች እንድናስታግስለት አበክሮ ሲጠይቅ የቆየ መሆኑን ራሱ ሕዝባችን የሚመሰክረው ሐቅ ነው " ሲል ክልሉ በመግለጫው ገልጿል።
የአማራ ክልላዊ መንግሥት በዚህ መግለጫው ፤ እየተከናወነ የሚገኘው የሕግ ማስከበር ሥራ የአማራን ሕዝብ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም ያለ ሲሆን ይህንንም ደጋግመን ለሕዝባችን አሳውቀናል ብሏል።
የሕግ ማስከበር ስራው የክልሉ፥ ሕዝብ ወደ ዘላቂ ሰላም በማስገባት የሕዝቡን የትግል ዓላማ ፣ ሰላም፣ ፍትሐዊ ልማት እና ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ ነው ሲል ገልጿል።
በዚህ ሥራ የትኛውም በክልሉ የሚኖር ሰላማዊ ዜጋ ሠርቶ የሚለወጥበት፤ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት አውድ የሚፈጠርበት ነው ብሏል።
የክልሉ መንግሥት ዛሬም ሰላም የሁልጊዜም ብቸኛው አማራጩ እደሆነ አመልክቷል።
በሌላ በኩል ክልላዊ መንግሥቱ አንዳንድ " ጽንፈኛ " ሲል የጠራቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አስጠንቅቋል።
ከሕግ ማስከበር ዓላማ ውጭ የሆነ፤ የሕዝብን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ጥቅሞች የሚያሳጣ እና የሕዝቡን መሠረታዊ ችግሮች የሚፈቱበትን ስልቶች የማይደግፍ እንዲሁም ሀገርን ወደ ትርምስ የሚመራ የሁከት እና የብጥብጥ ቅስቀሳ ሁሉ ፈጽሞ ስህተት እና ክልሉን እና ሕዝቡን ዋጋ የሚያስከፍል በተጨማሪ ለተራዘመ ጊዜ የሚያጎሳቁል መሆኑን መረዳት ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

" በአስቸኳይ መስጂዶችን ማፍረስ አቁሙ ፤ የፈረሱትንም በፍጥነት መልሳችሁ አሰሩ ፤ ህዝበ ሙስሊሙንም በይፋ ይቅርታ ጠይቁ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲሱ "በሸገር ከተማ " መስጂዶች እየፈረሱ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ።
ምክር ቤቱ ለኦሮምያው ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፃፈው ደብዳቤ ነው ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፈው።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እየፈረሱ ያሉ መስጂዶች በአስቸኳይ እንዲያስቆም ብሏል።
ከዚህ ባለፈም ፤ የፈረሱ መስጂዶች በሸገር ከተማ አስተዳደር በፍጥነት እንዲሰሩና ሕዝበ ሙስሊሙን አስተዳደሩ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል።
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ፥ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በተፃፈው ደብዳቤ :-
1. በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዉንዴሳ ወረዳ ልዩ ስፍራ ቀርሳ በቀን 14/07/15
2. በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ መጉላ ቶውፊቅ መስጂድ 19/08/15
3. በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አን ኢ ሳይት ሰላም መስጂድ በቀን 24/08/25
4. በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ በቀን 25/08/15 መፍረሳቸውና ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ መሆኑን አሳውቋል።

" የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቀጣዩን ድርድር በማፋጠን ህዝቡ ለተጠማው #ሰላም ቅድሚ ሊሰጡ ይገባል " - ኦፌኮ
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በ2014 ዓ.ም 2ተኛ ጠቅላላ ጉባኤን አካሂዷል፤ በመደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ ነጥቦችን የያዘ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ፦
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያን ጨምሮ በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ እየሞከረ ያለውን እርቅና ድርድር በመርህ ይደግፋል ብሏል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) መካከል የተፈጠረው ጦርነት መነሻው ፖለቲካዊ አለመግባባት በመሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ እንደተደረገው ጦርነት ሁሉ በሰላም እና በእርቅ እንዲቆም ደጋግሞ ጥሪ ማቅረቡን ኦፌኮ አስታውሷል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሰላማዊ መንገድ ድርድር መጀመራቸውን በደስታ እንደሚቀበል የገለፀው ፓርቲው የሁለቱ ወገኖች የመጀመሪያው ዙር ድርድር መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣዩ ድርድር በማፋጠን ህዝቡ ለተጠማው ሰላም ቅድሚ እንዲሰጡ አሳስቧል።
የሰላም ድርድሩ ከተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈ የኦሮሞን ህዝብ በሚመለከቱ ውስብስብ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ቀሪ የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎችን ማሳተፍ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋልም ሲል አስገንዝቧል።
ከዚህ ባለፈ ኦፌኮ ፤ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ እያደረሱ ያለው ህገወጥ ግድያ እስራትና ንብረት ማውደም፤ እንዲሁም በፓርቲው ደጋፊዎች፣ አባላት እና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለው እስራት ፣ ግድያ፣ ደብዛማጥፋት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠይቋል።
በተለያዩ ስም የመንግስት ካድሬዎች ያለ ደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲቆም፤ ከመንግስት እና ከገዢ ፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ህገ ወጥ ንግድን ቁጥጥር እንዲደረግበትም ኦፌኮ ጠይቋል።
ሌላው ኦፌኮ በመግለጫው የዋጋ ንረትን በተመለከተ ያነሳ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት በህዝብና በኢኮኖሚ ላይ ላደረሰው ጉዳት ገዢው ፓርቲ ሙሉ ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል ብሏል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት በገዢው ብልፅግና ፓርቲ የተሳሳተ ውሳኔ ምክንያት መሆኑን ፓርቲው (ኦፌኮ) ገልጿል።

Photo
#ኦፌኮ
" ብልፅግና ፓርቲ ለፈፀመውና እየፈፀመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ፓርቲው እራሱ ነው፤ በዚህ ምክንያት የኦሮሞን ህዝብ ስም ማጥፋት ትክክል አይደለም " - የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በ2014 ዓ/ም 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ካካሄደ በኃላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፤ ገዢውን ብልፅግና ፓርቲ እንደ ኦሮሞ መንግሥት በመቁጠር ፓርቲው የተሳሳተውን ስህተት እና ህገወጥ ተግባር የኦሮሞ ህዝብ ስህተት በማስመሰል የሚቀርቡ አቀራረቦች በህዝብ መካከል ቅራኔ የሚፈጥሩና እጅግ አደገኛ መዘዝ የሚያመጡ ናቸው አለ።
ኦፌኮ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገዥውን ፓርቲ እንደ ኦሮሞ መንግሥት በመቁጠርና የ ' ኦሮሙማ አገዛዝ ' የሚል የተሳሳተ ብያኔ በመስጠት አንዳንድ የአማራን ህዝብ እንወክላለን የሚሉ ኃይሎችና ምሁራን ይህ አካል የፈፀመውን ስህተት እና ህገ ወጥ ተግባራት የኦሮሞ ህዝብ ስህተት አስመስለው እያቀረቡ ነው " ሲል ገልጿል።
" ይህ በህዝቦች መካከል ቅራኔ የሚፈጥርና ከባድ መዝዝ ሊያስከትል የሚችል ስህተት የሆነ አስተሳሰብ ነው " ያለው ኦፌኮ ፤ " ብልፅግና ፓርቲ ለፈጸመውና እየፈጸመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ፓርቲው ራሱ ሲሆን በዚህ ምክንያት የኦሮሞ ህዝብ ስም ማጥፋት ትክክል ስላልሆነ እንደዚህ አይነት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን " ብሏል።

#Update
የዲቪ (DV) 2024 አሸናፊዎች ይፋ ተደረጉ።
ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ዲቪ (DV) ሎተሪ ይፋ ተደርጓል።
ለዲቪ /DV/ 2024 ማመልከቻ የሞሉ በ https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx ብቻ ውጤቱን / ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።
በአ/አ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ "የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው" በሚል #የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አደራ ብሏል።
አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

#CBE
በሲቢኢ ብር ነዳጅ ሲቀዱ ሁለት አማራጮች አሉ !
የመጀመሪያው ፦
ራስዎ ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያዎ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ክፍያ ፈጽመው ነዳጅ የሚቀዱበት ነው፡፡
ሁለተኛው ፦
ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ߹ የሰሌዳ ቁጥርዎን እና የሚቀዱትን ነዳጅ የገንዘብ መጠን አሳውቀው በሚደርስዎት አጭር መልእክት መሠረት የገንዘብ መጠኑን ትክክለኛነት አረጋግጠው ክፍያውን በመፈፀም ነዳጅ የሚቀዱበት አማራጭ ነው።
****************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787