TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የIMF ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ናቸው።

ብሉምበርግ የዜና ወኪል ፤ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ የድርጅቱ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ይገኛሉ ብሏል።

በእርስ በርስ ጦርነቱ ሳቢያ ኢትዮጵያ ከIMF ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የነበራት ግንኙነት ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወሳል።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ የተቋሙ የባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ ከIMF ሊደረግላት ስለሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን “ቴክኒካዊ ሥራ ለማከናወን” ነው አዲስ አበባ የሚገኘው።

ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በተመለከተ ውይይት እና አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻቹ የተላኩት የIMF ባለሥልጣናት ለ10 ቀናት ያህል ይቆያሉ።

ቃላቸውን ለሮይተር የዜና ወኪል የሰጡ የIMF ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላት ተቋሙን እንደጠየቀች ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ " ሊሰጥ የሚችለው ድጋፍ አገሪቱ ለምታካሂደው አገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እና ምጣኔ ሀብቷን በማረጋጋት ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለድህነት ቅነሳ የሚውል ይሆናል " ብለዋል።

የIMF ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ውይይት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና በተቋሙ መካከል ሰብአዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮችን ለማሻሻል የተደረገ ንግግር ተከታይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መካከል ሲካሄድ የነበረው የድጋፍ፣ የብድር ስረዛ እና ሽግሽግ ንግግር በከፊል በትግራይ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ ነበር።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ጦርነቱ ያስከተለውን ውድመት መልሶ ለመገንባትና የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን አስፈላጊ ለሆኑ የገቢ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም ድጋፍ ያስፈልጋታል።

ጦርነቱ ካስከተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር በአፍሪካ ካሉ የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች መዳረሻ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን እና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተነሳ ከዓለም ባንክ (World Bank) አንዲሁም ከIMF የምታገኘውን ድጋፍ ገትቶት መቆየቱን አስታውሷል።

በጦርነቱ እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር የገጠማት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከመመዝገቡ በላይ እጥረትም ተከስቷል።

#ቢቢሲ #ብሉምበርግ #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
" ከአፍጥርና ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንታደግ " - ደም ባንክ

በተያዘው የጾም ወቅት በቂ ደም ከማግኘት አንፃር ውስነነት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ባንኩ በዚህ ወቅት በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋብኮ ተናግረዋል።

#ሕይወትን_ማትረፍ ከፆሙ ዓላማ አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ ከአፍጥር እንዲሁም ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ለመታደግ ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ደም የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ በተንቀሳቃሽ እና በቋሚ ቦታዎች እንዲሁም በሥራ ቀናት በትምህርት ቤቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በመዘዋወር የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ ቅዳሜ አደባባይ ላይ ድንኳን በመትከል የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በመቀስቀስ እና እሁድ በቤተ እምነቶች የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

#ኤፍቢሲ

More : @tikvahethmagazine
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
#AddisAbaba

ዛሬ ከሠዓት ላይ በአዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 መርካቶ በተለምዶ " ማር ተራ " ተብሎ በሚጠራው ቦታ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር።

የእሳት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር የተቻለው በእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፖሊስ አባላት እና በአካባቢው #ወጣቶች ከፍተኛ ርብርብ መሆኑ ተመላክቷል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እንዲሁም ያስከተለው የጉዳት መጠን በቀጣይ ተጣርቶ ይገለፃል ተብሏል

መረጃው የክ/ከተማው ኮምንኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

“ በጀት ተፈቅዷል። ትክክለኛ ቁጥሩን በሚመለከት ግን ገና እንነጋገራለን ” - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የፌደራል መንግስት፤ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ ለመልቀቅ መስማማቱ ገለፁ።

አቶ ጌታቸው ፤ የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል በጀት ለማስተላለፍ ከስምምነት ላይ መድረሱን የገለፁት ለ “ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ” ድረገፅ በሰጡት ቃል ነው።

ምንም እንኳን በጀት ለማስተላለፍ ስምምነት ላይ ቢደረስም የሚለቀቀውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ግን ገና ውይይት እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

“ በጀት ተፈቅዷል። [ትክክለኛ] ቁጥሩን በሚመለከት ግን ገና እንነጋገራለን ”

NB. ከተሾሙ በነገው ዕለት አንድ ሳምንት የሚሞላቸው አቶ ጌታቸው ረዳ 11 የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ይዘው ከፌደራል መንግስት ጋር ለመነጋገር በአዲስ አበባ ከተማ ይገኛሉ።

የትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መቼ እና ለምን ነበር የተቋረጠው ?

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመስከረም 2013 ባስተላለፈው ውሳኔ ነው የትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ የተቋረጠው።

የበጀት ድጋፍ እንዲቋረጥ የተደረገው፤ ክልሉ ከፌደራል መንግስት እውቅና ውጭ “ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ አካሄዷል” በሚል ነው።

Credit - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
#BrightRealEstateMarketing #OsloLuxuryApartment

ቦሌ ኦሎምፒያ ግሪክ ት/ቤት አካባቢ 80% የተጠናቀቀ በአዉሮፖ እስታንዳርድ እየተሰራ ያለ የራሱ የተናጠል ካርታ ያለዉ፣ ሲፈልጉ ከባንክ ጋር የሚያገናኙት ዘመናዊ ባለ 1, 2 እና 3 መኝታ 95, 148 እና 207 ካሬ አፖርትመንት ይዘንልዎት ቀርበናል፡፡
+251911041236    +251988969696
አድራሻ ፦ ቦሌ መድሀኒአለም አለምነሽ ፕላዛ 5ኛ ፎቅ 509
መቶ ሺህ ብር መደለያ ተቀብለዋል የተባሉት ዳኛ ከስራ ተሰናበቱ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩትን አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን ከስራ አሰናብቷል።

የስራ ስንብት ውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ፤ አቶ ፋንታሁን የዳኞች የስነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ክስ ስነ-ስርዓት ደንብ በመተላለፍና የሐቀኝነት ተነጻጻሪ ግዴታ በመተላለፍ ከአመልካች ብር 100 ሺህ (አንድ መቶ ሺህ ብር) መደለያ መቀበላቸው በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ የአቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን የስራ ስንብት የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 13/2015 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

@tikvahethiopia
#ፀድቋል

የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።

የውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ፦ " የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ሁሉን አቀፍ፣ ወጥና አስተማማኝ የሀገሪቷ ነዋሪዎች የሚመዘገቡበት ሥርዓት በመዘርጋት እና የተመዝጋቢዎችን መረጃ በመያዝ የዲጂታል መታወቂያ አጠቃቀም ስርዓትን ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው " ብለዋል።

መታወቂያውን በመጠቀም በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የግልፅነትና ተጠያቂነት አሰራር ስርዓት እንዲዘረጋና የተሳለጠ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር አመቺ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር አክለዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ የም/ ቤቱ አባላት ፥ የዲጂታል መታወቂያውን በተጭበረበረ መንገድ በሚሰጡ ግለ-ሰቦች እና ተቋማት ላይ #የሀገር_ክሕደት ወንጀል እንደፈፀሙ ታስቦ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በዝርዝር መቀመጥ አለበት ብለዋል።

ወ/ሮ እፀገነት አዋጁ ረዘም ላለ ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀው ፤ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት የተጭበረበረ መታወቂያ ሰጥተው ከተገኙ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እና አስተማማኝነቱም በመርህ ላይ መመስረቱን አስረድተዋል።

ምክር ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1284/2015 አድርጎ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል።

ምንጭ፦ የህ/ተ/ም/ቤት

@tikvahethiopia
የነጻ ትምህርት ዕድል !

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመጋቢተ 18 - 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም. ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ ወይንም በአገር አቀፍ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፡፡ 

የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት፤ ሐረር  በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፤ የድርጅቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው በተጨማሪም በድረ-ገጻችን https://www.mfmattc.edu.et ላይም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0256663738/1139 ወይም 0114714579 ደውሎ ማንጋገር ይቻላል፡፡ 

(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation)