TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ክሳቸው ተቋርጧል "

በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክስ መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በፌዴራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) መሃከል በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ ያለውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል። 

ስለሆነም በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክስ በማቋረጥ ጉዳያቸው በቀጣይ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ እንዲታይ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። 

ስለዚህ በተገለፀው አግባብ ከዚህ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ሂደት ላይ ይገኙ የነበሩ የወንጀል ክሶች በአዋጅ 943/2008 አንቀጽ 6 (3) (ሠ) መሰረት የተነሱ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Nekemte

" ግድያው የተፈፀመው የቤታቸው ደጃፍ ላይ ነው "

ዛሬ የነቀምቴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት የ33 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ በታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

ግድያውን በተመለከተ የከተማ አስተዳዳሩ ምን አለ ?

- ለሥራ ከቤታቸው ሲወጡ በቤታቸው ደጃፍ ነው ባልታወቁ ሰዎች ነው የተገደሉት ብሏል።

- አቶ ደሳለኝ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር በቁርጠኝነት እና በተቆርቋሪነት. . . ያለምንም ፍርሐት ሕዝቡን ሲያገለግሉ ነበሩ ሲልም ገልጿል።

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ምን አሉ ?

- ግድያው የተፈፀመው በታጠቀ አካል ነው ብለዋል።

- ምንም እንኳን ግድያውን የፈፀሙ አካላትን ማንነት በስም ባይገልፁም ግድያውን የተፈፀሙት ከአገሪቱ የለውጥ መንገድ በተጻራሪ የቆሙ አካላት ናቸው ብለዋል።

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በፖለቲካ ፓርቲዎች የመሰብሰብ መብት ላይ የሚደረጉ ገደቦችና በአባላቶቻቸው ላይ የሚደርሱ እንግልቶች በዘላቂነት ሊቆሙ ይገባል ብሏል።

ኮሚሽኑ በመሰብሰብ መብት ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ተግባሮችን የመመርመርና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥት መሆኑንም በላከልን መግለጫ አስገንዝቧል።

(ከኢሰመኮ የተላከ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 "የቀድሞ" አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አስገብተዋል ሲል የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል። ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ…
#ሰበር_ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል። በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን…
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?

ካሁን ቀደም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበትና በመቀጠል አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው 10ሩ የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመምጣት እስካሁን ድረስ በበዓታቸው ጸንተው የቆዩት 3ቱም የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ፦
👉 ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣
👉 ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
👉 ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ላይ አስቀድሞ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ #ተነስቷል፡፡

- ውግዘቱ የተነሣላቸው 3ቱም ሊቃነ ጳጳሳት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀነ 2015ዓ.ም. ጀምሮ በቀድሞ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረጋቸውና ስማቸው ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሊቀጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ሊቀጳጳስ ተብለው እንዲጠሩና አስቀድሞ ተመድበው ይሰሩበት በነበረው የሥራ ኃላፊነታቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ጥሪውን ተቀብለው ለስምምነቱ ተገዥ በመሆን በጽሑፍ ጥያቄያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያቀረቡት 20ዎቹ የቀድሞ መነኮሳት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ #ተነስቷል፡፡ ቀሪዎቹ 5ቱ ባለው ጊዜ ተጠቅመው ወደቤተ ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ ያሳሰበ ሲሆን ውግዘቱን በሚመለከት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ታይቶ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ውግዘቱ የተነሣላቸው 20ዎቹም የቀድሞ መነኮሳት አስቀድሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከዲቁና እስከ ቁምስና ባለው ማዕረገ ክህነታቸው እንዲያገለግሉ እና በምንኩስና ስማቸውም እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ሃያዎቹ (20ዎቹ) የቀድሞ መነኮሳት የሥራ ምደባን በተመለከተ በተደረሰው ስምምነት መሠረት በቀድሞው የሥራ መደብ ደረጃቸው እንዲመደቡ ቅዱስ ሲኖዶስ በመወሰን ዝርዝር ጉዳዩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አዟል።

- ምንም እንኳን አስቀድሞ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይትና ስምምነት መሠረት የታሰሩት ግለሰቦች በሙሉ እንደሚፈቱ ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በርካታ ሰዎች በእስር ላይ የሚገኙ ስለሆነ መንግስት አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ሁሉንም እስረኞች እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ አሳስቧል።

- በተከሰተው ችግር ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ላይ በኃላፊነት ተመድበው ሲሰሩ ቆይተው በችግሩ ምክንያት ተፈናቅለው የቆዩት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት በምድብ ሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

(#ሙሉ ውሳኔው እንዲሁም መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ከእስር ተፈተው ወደ ቤታቸው ገብተዋል " - ጠበቃ ሃፍቶም ከሰተ

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ከእስር ተፈቱ።

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21/2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት ጠበቃ ሃፍቶም ከሰተ ተናግረዋል።

ጠበቃው ይህን የተናገሩት ለ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ ነው።

በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ ፦ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አሳውቀዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
የመኪና ዘረፋ !

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኝ ድርጅት 2 እቃ ጫኝ መኪኖች መሰረቃቸው ተጠቆመ።

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ኢንድስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ንብረትነታቸው "ሶራና ኢንደስትሪ እና ኢንጂነሪንግ ድርጅት" የሆኑ ሁለት የእቃ ጫኝ መኪኖች ትላንት ምሽት ከነበሩበት ተሰርቀዋል።

ድርጅቱ ለቲክቫህ እንዳስታወቀው መኪኖቹ የጠፉት ከድርጅቱ ጊቢ ውስጥ ከሥራ መልስ በቆሙበት ነው ያለ ሲሆን ድርጊቱ ማታ 3:30 ላይ መፈጸሙን በግቢው በነበረ የደኅንነት ካሜራ መመልከት ተችሏል።

አንደኛው መኪና ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 34655 የሆነ 28 ኩንታል የመጫን አቅም ያለው ቫን መኪና ሲሆን ሁለተኛው መኪናም ተርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 04794 የሆነ 35 ኩንታል የመጫን አቅም ያለው አይሱዙ ነው። በመኪኖቹ ላይም "ሶሎ የመኪና አስመጪ እና የመኪና መስታዎት" የሚል ሎጎ እንዳለም ተገልጿል።

በዕለቱ በድርጅቱ 2 ጥበቃዎች እንደነበሩ የገለጹት የድርጅቱ ጥቆማ ሰጪ አንደኛው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት የሚገኝ ሲሆን አንደኛው ከዘራፊዎቹ ጋር አብሮ መጥፋቱን ጠቁመዋል።

" ዘረፋው መፈጸሙ የታወቀው ጠዋት ለስራ ሲገባ ነው፤ የጠፋው ጥበቃ ተያዥ ሆኖ ካስቀጠረው ሰው ጭምር ጋር አልተገኘም " ሲሉ አስረድተዋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው አንደኛውን ጥበቃ በማታለል ወይም እንቅልፍ ላይ ሳለ በሌላኛው ጥበቃ ረዳትነት እንደሆነ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ገልጸዋል።

ጉዳዩን ለላፍቶ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከታቸውን ጠቅሰው፤ መኪኖቹን የተመለከቱ ግለሰቦች ለሚመለከተው የጸጥታ አካል ወይም በስልክ ቁጥር ስልክ ቁጥር 0911487570 / 0911210220 ጥቆማ ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
" የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ወንድማማችነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንሰራለን " - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ የሚያጋጥሙንን የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ወንድማማችነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንሰራለን አሉ።

ይህን ያሉት ለክልሉ ሚዲያ አሚኮ በሠጡት ቃለ ምልልስ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ፥ የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ወደ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማሳደግ ተደጋግፈን ከችግራችን የምንወጣበትን መንገድ ማመቻቸት አለብን ብለዋል።

" የፖለቲካ ልዩነትን በውይይት ከመፍታት ይልቅ ጦርነትን አማራጭ ማድረግ መፍትሄ አልባ ኪሳራ እንደሚያደርስ አስተምሮናል " ያሉት ዶ/ር ይልቃል ቀድሞውኑ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ተፈተው ቢሆን ፣ በውይይት እና ድርድር ተፈተው ቢሆን ፣ በሽምግልናና በሰለጠነ አግባብ ተፈተው ቢሆን ይህ ሁሉ ችግር እና ምስቅልቅል በሀገሪቱ ላይደርስ ይችል ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ይልቃል ፤ ጦርነት ከሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ባለፈ ስነልቦናዊ ስብራትን እንደሚያስከትል የአማራ እና ትግራይ ህዝብ በተግባር አይተዋል ያሉ ሲሆን " የአማራ ክልል ህዝብ የትግራይ ህዝብ ወንድሙ እንደሆነ ድሮም አብሮ ይኖር ነበር ወደፊትም ቢሆን አብሮ ለመኖር የተዘጋጀ ህዝብ ነው ፤ ከወንድሙ ጋር የሚያጋጥመውን ችግር በሰላም እና በድርድር ለመፍታት ነው የሚዘጋጀው የሚያስበው። የትግራይ ክልል ከኛ የሚጠይቀው ጉዳይ ካለ በሰላም በውይይት ፣ ከዚያም ባለፈ በህግ መፍታት እንችላለን ይሄን የሰለጠነ መንገድ ሁላችንም ተቀብለን መፈፀም አለብን " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጦርነቱ የፈጠረውን ቁስል በሚያክም መንገድ መግባባት ፣ መገናኘት እንደ አንድ ሀገር ዜጋ እንደ ወንድም እና እህት ማህበረስብ መተሳሰብ ይገባናል ብለዋል።

" በዚህም ረገድ የአማራ መንግስትም ሆነ የአማራ ህዝብ የትግራይ ህዝብ የኔ ወንድም እና እህት ነው ብሎ የሚያስብ በችግሩ ጊዜ የሚደርስ በመሆኑ በዚያ መንፈስ ነው የምናየው ፤ ሰላም አብሮነትን የሚያፀና ፣ የሚያጠናክር ይሆናል ብለን እምነት እናደርጋለን " ሲሉ አክለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
36 የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ተፈተዋል።

በወንጀል ተጠርጥረው ክሥ ቀርቦባቸው የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክሥ ማቋረጡን የፍትሕ ሚኒስቴር ከአስታወቀ በኋላ እነ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ 36 ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ሃሙስ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከእስር ተለቀዋል።

ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ ሀፍቶም ከሠተ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ ከእስር ተፈቺዎቹ፣ በማረሚያ ቤት መኪኖች፥ ሳሪስ፣ ፒያሳ እንዲሁም ሲኤምሲ ወደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እንደተሸኙና ቤተሰቦቻቸውም አቀባበል እንዳደረጉላቸው ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት 16ቱ የህወሓት የሲቪል እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የክሥ መዝገብ ሥር እንደነበሩ ጠበቃው ገልጸዋል።

በሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የክሥ መዝገብ ሥር ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው 20 ተከሣሾች እንደሆኑም ጠበቃው ለሬድዮ ጣቢያው ጠቅሰዋል።

Photo : File

@tikvahethiopia