TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በኢትዮጵያ አማካይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ #ስርጭት 0.9 መድረሱን #ጥናት አመለከተ። ጥናቱ የተካሄደው በዋናነት በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲሆን ጤና ሚኒስቴር፣ የአሜሪካ መንግስት የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል፣ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አይካፕ፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤትና ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ነው።

©ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሜቴክ ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (#ሜቴክ) የተሰየመው አዲሱ የሥራ አመራር ቦርድ፣ በኮርፖሬሽኑ ያለ ገበያ #ጥናት ተመርተው ገዥ ማግኘት ባለመቻላቸው በአዳማ የእርሻ መሣሪያዎች ኢንዱስትሪ ከስድስት ዓመታት በላይ ተከማችተው የሚገኙ ከአሥር ሺሕ በላይ የሚሆኑ ትራክተሮችና መለዋወጫዎች፤ከተቻለ በርካሽ ዋጋ እንዲሸጡ ካልሆነም ለክልሎች በስጦታ እንዲበረከቱ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥናት

በሶስት ክልሎች ሲዳማ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵካ በተደረገ የሰላም ልኬት የናሙና ጥናት የክልሎቹ ተወላጆች በሌላ ክልል ተወላጆች ላይ ያላቸው እምነት 14 በመቶ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል።

የክልሎቹ ጎሳዎች ወይም ተወላጆች እርስ በእርስ ያላቸው እምነት 48 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል።

በሶስቱም ክልሎች 801 ሰዎችን ፣ 101 የቀበሌ አስተዳደሮችን እና 101 የሀገር ሽማግሌዎችን በናሙናነት ተወስደዋል።

ጥናቱ እንዲካሄድ ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር ከኢንተርፒስ በጋራ ሆነው ነው።

በዚሁ ጥናት ፤ የኢትዮጵያ ሰላም ጥናት ልኬት (Peace Index) በሶስቱ ክልሎች ከአስር ፤ 6.7 እንደሆነ ተመላክቷል።

በግለሰብ በቤተሰብ፣ በህብረተሰብ እና በወሰን መካከል ያለው የሰላም ልኬት ውጤት ይለያያል ተብሏል።

ጥናቱን ያቀረቡት ተመራማሪ ፤ ሙሉ ተካ  ፤ " መለኪያው ከ0 - 10 ነው ፤ በግለሰቦች ውስጥ ያለው ሰላም 8.1 ነው። በቤተሰብ ጋር 7.1 ነው። ማህበረሰብ ጋር 6.3 ነው ፤ በአካባቢ ድንበሮች 5.4 ነው " ብለዋል።

እነዚህ ሶስቱ ክልሎች በአንፃራዊነት ሰላማዊ የነበሩ እና ሆነው የቆዩ ክልሎች ናቸው ነጥባቸው ግን ትልቅ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ አሁን የተመዘገበው ውጤት የአንድ ችግር አለመላካች ነው ያሉ ሲሆን " የጥናቱ አንድምታ አሁን መተንተን አይቻልም። መጠንቀቅ አለብን ከዚህ አንድምታውን እና ድምዳሜውን መስጠት አቸጋሪ ነው ፤ ይሄ ጥናት መነሻ ነው " ብለዋል።

በሶስቱ ክልሎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሌላው ጎሳ ላይ ያላቸው እምነት 14 በመቶ፣ በሌላ ሃይማኖት ላይ ያላቸው እምነት 14 በመቶ እና በሌሎች ክልሎች ላይ ያላቸው እምነት 13 በመቶ ብቻ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል።

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው ፤ እንዲህ አይነት ጥናት በሁሉም ክልሎች ተጠንቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ያሉ ሲሆን እንዲህ አይነት ጥናት መደረጉ ችግሮችን በግምት ከመለየት ይልቅ ሳይንሳዊ በመሆነ መንገድ በመለየት መፍትሄ ለመስጠት ይረዳል ሲሉ አሳውቀዋል።

ጥናቱን በተመለከተ ክልሎቹ ምን አሉ ?

ያንብቡ : https://telegra.ph/Sheger-FM-06-30

Credit : Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
#ጥናት #ሞዴስ

በኢትዮጵያ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት ከሚያገኙት ገቢ አንጻር ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ " ቢቢሲ አፍሪካ ቪዡዋል ጆርናሊዝም " ባካሄደው ጥናት አመልክቷል።

ጥናቱ ፦ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ዋጋ ምን ያህል ተመጣጣኝ እንደሆነ ለማየት የተደረገ ነው። 9 የአፍሪካ ሀገራትንም ዳሷል።

ጥናቱ ፤ ዝቅተኛ ወርሃዊ ገቢን ከርካሽ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ዋጋ ጋር ያነጻጸረ ሲሆን በዚህም የምርቶቹ ዋጋ የበርካታ ሴቶችን አቅም ያገናዘቡ እንዳልሆኑ ደምድሟል።

ጥናቱ የተደረገባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?
- ጋና፣
- ኢትዮጵያ፣
- ሶማሊያ፣
- ኡጋንዳ ፣
- ናይጄሪያ፣
- ሩዋንዳ፣
- ታንዛኒያ፣
- ደቡብ አፍሪካ
- ኬንያ ናቸው።

በጋና ዝቅተኛ ደመወዝ ያላቸው ሴቶች ከሚያገኙት ገቢ #ከፍተኛ የተባለውን ወጪ የሚያወጡባት ሲሆን ኢትዮጵያ ከጋና ቀጥላ ተቀምጣለች ፤ ኬንያ በአንጻሩ ምርቶቹ ርካሽ የሆነባት አገር ናት።

ከ9ኙ አገራት መካከል በ6ቱ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች በየወሩ እያንዳንዳቸው 8 ነጠላ ሞዴሶችን የያዙ 2 እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለመግዛት ከደመወዛቸው ከ3 እስከ 13 በመቶ የሚሆነውን ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

በጋና አንዲት ሴት ከምታገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ተብሎ ከተቀመጠው 26 ዶላር ውስጥ ሦስቱን ዶላር ወይም ከሚያገኙት 7 ዶላር ውስጥ አንዱን፣ ሁለት እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት ታወጣለች።

ይህም አሜሪካ እና በዩኬ ካሉ ሴቶች ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ ነው። በአሜሪካ ሴቶች ከሚያገኙት 1 ሺህ 200 ዶላር ዝቅተኛ ገቢ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት የሚያወጡት 3 ዶላር ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ አንዲት ሴት ከምታገኘው ገንዘብ በአማካይ ስድስት በመቶውን ለሞዴስ ታወጣለች ብሏል ጥናቱ።

በኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በፊት በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ ማድረጓን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።

በዚህ ውሳኔ መሠረት እነዚህ የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም።

ጎረቤት አገር ኬንያ በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ በማድረግ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር የሆነችው እንደ አውሮፓውያኑ 2004 ነበር።

ከ2 ዓመት በኋላ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ አድርጋለች።

በዚህ ምክንያት በኬንያ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ዋጋ ቀንሷል። አሁን ላይ ርካሹ የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በ35 የአሜሪካ ሳንቲም ይሸጣል።

ሆኖም ሴት ፖለቲከኞች እና ተሟጋቾች ምርቶቹ ከዚህ ያነሰ ዋጋ ለተገልጋዮች እንዲቀርቡ አሁንም እየጠየቁ ነው።

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 53 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ በአብላጫነት ይደግፋሉ " - የአፍሮባሮሜትር ጥናት (በኢዮብ ትኩዬ) 66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንደሚሹ መመላከቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ #አፍሮባሮሜትር ይፋ ካደረገው ጥናት ተረድቷል። የዳሰሳ ጥናቱ ከላይ ከተጠቀሰው የገደብ ፍላጎት በተጨማሪ 67 በመቶ ኢትዮጵያውያን የሕገ…
#ኢትዮጵያ #ጥናት

54 በመቶ ኢትዮጵውያን የኢትዮጵያን የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት ለማስተናገድ ከአሃዳዊ ይልቅ ፌደራላዊ የመንግሥት ሥርዓትን እደሚመርጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አፍሮባሮሜትር ከግንቦት 17 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም አጠናሁት ካለው የጥናት ግኝቶች ተገዝቧል።

42 በመቶ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ፌደራሊዝምን ወደ ግጭት የሚመራ ሥርዓት አድርገው ይመለከታሉ።

በጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች መሠረት፦

- ከአሥሩ ውስጥ አራቱ (42 በመቶ) ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝምን ወደ ግጭት የሚመራ ሥርዓት አድርገው ይመለከታሉ፣ ስለዚህ ወደ አሃዳዊ የመንግሥት ሥርዓት መሸጋገሩን የሚደግፉ ናቸው።

ጥናቱ 54 በመቶ በገጠር፣ 56 በመቶ በከተማ እንዲሁም 54 በመቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝም ኢትዮጵያ ካላት የባህል እና የቋንቋ ብዝሃነት የተነሳ፣ ነጻ የሆኑ የክልል መንግሥታት ያለው ፌደራሊስም ሥርዓት የተሻለነው ማለታቸውን ያስረዳል።

ነገር ግን 43 በመቶ በገጠሩ፣ 40 በመቶ በከተማ እንዲሁም 42 በአገራዊ ያሉ ኢትዮጵያውያን " በባህልና በቋንቋ ማንነት ላይ የተመሰረተው የፌደራሊዝም ሥርዓት አንዳንዴ ወደ ግጭት ስለሚመራ ኢትዮጵያ ወደ አሃዳዊ መንግሥት መቀየር አለባት፣ ማእከላዊ መንግሥት በሥልጣን አሰጣጥ የበለጠ ሥልጣን ይኖረዋል " ብለው እንደሚስማሙ የጥናት ውጤቱ ይገልጻል።

3 በመቶ በገጠር፣ 4 በመቶ በከተማ፣ 3 በመቶ በአገራዊ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሁሉም አልስማማም፣ አላውቅም፣ ፈቃደኛ አይደለሁም ማለታቸውን ጥናቱ ያስገነዝባል።

- በ2012 ከተደረገው የተቋሙ የዳሰሳ ጥናት ጋር ሲነጻጸር፣ የፌደራል ሥርዓት መንግሥትን የሚደፉ ሰዎች በሰባት በመቶ (ከ61 በመቶ ወደ 54 በመቶ ወርዷል)። አሃዳዊ የመንግሥት ሥርዓትን በመደገፍ ረገድ ደግሞ የአምስት በመቶ ብልጫ አለው።

በ2020 61 በመቶ ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝም የተሻለ ሥርዓት ነው ብለው ይስማሙ እንደነበር፣ በ2023ቱ ጥናት ደግሞ ፌደራሊዝም የተሻለ ሥርዓት ነው የሚሉት ወደ 54 በመቶ  ዝቅ እንዳለ እንዲሁም በ2020 ጥናት 37 በመቶ የሚሆኑት ሥርዓቱ ወደ አሃዳዊ የመንግሥት መዋቅር መቀየር አለበት ብለው እንደነበር፣ በ2023 ደግሞ አሃዳዊ ይሁን ያሉት ወደ 42 በመቶ ከፍ እንዳለ ግራፉ ያመለክታል። 

- ግማሽ ያህሉ (49 በመቶ) ኢትዮጵያውያን ፌደራሊዝም በብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነት መሠረት የተቀመጡ ክልሎችን መሠረት አድርጎ ፌደራላዊ የመንግሥት ሥርዓት መቀጠል እንዳለበት፣ ግማሾቹ (48 በመቶ) ክልሎቹ ደግሞ በመልካዓ ምድራዊ ገፅታዎች እንጅ የተለያዩ ብሄር፣ ብሄረሰቦች በሚኖሩበት መልኩ መሆን እንደሌለበት መናገራቸው በጥናቱ ተቀምጧል። 

በዚህም 54 በመቶ የሚሆኑት የከተማ ነዋሪዎች መልካዓ ምድራዊ ገፅታዎች መሠረት ያደረገ የፌደራል ሥርዓትን የመምረጥ ዝንባሌ እንዳሳዩ፣ በገጠር ያሉ 51 በመቶ የሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ በማንነት ላይ መሠረት ያደረገውን የፌዴራል ሥርዓት የመምረጥ ዝንባሌ እንዳሳዩ፣ ይህም በአገር ደረጃ ከ2012 ዓ.ም ጥናት ጋር ሲነጻጸር እነዚህ አስተሳሰቦች እምብዛም እንዳልተለወጡ ጥናቱ አክሏል። ይህኑም በግራፍ መግለጫው በዝርዝር አብራርቷል።

ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ለዘጠነኛ ጊዜ የተጠና ሲሆን፣ 53 በመቶ ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ፣ 66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንደሚሹ ከዚሁ ጥናት የተመለከትነውን ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ጥናት

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው፣ በዕጣ የቤት ባለቤት የሆኑ ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት (ACRC) እና ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) በጋራ ባደረጉት ጥናት ማረጋገጥ መቻላቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ተቋማት ጥናቱን ለአንድ ዓመት ያህል ነው ያደረጉት።

በጥናቱ ከ6 በላይ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊ ሽግግርና በወጣቶች አቅም ግንባታና በመኖሪያ ቤቶች ላይ የተደረገ ነው።

ጥናቱ ምን ይላል ?

- በአዲስ አበባ ከተማ ከመነሻውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም፡፡

- መንግሥት 40/60 ወይም የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ለደረሳቸው ሲያቀርብ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ስለማይገነቡ፣ ዕድለኞች መልሰው አፍርሶ ለመሥራት ይገደዳሉ ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ፦
* ለኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ፣
* የሲራሚክ ንጣፍ፣
* ለመፀዳጃ ቤት መስመር፣
* ግድግዳ እንደገና ለመሥራትና ሌሎች የጎደሉ ነገሮች ለማሟላት ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ መንግሥት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብዓት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድረስ ጥራታቸውን በመጠበቅ ማቅረብ ይኖርበታል።

በተጨማሪ ...

በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ተስማሚ የሆኑ ነገሮች እንደሌላቸው ታይቷል። ወጣቶች በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ፣ በኢመደበኛ ዘርፍና በጤና ላይ ያላቸውን በጎ ተግባራትና ያሉባቸው ችግሮች ተለይተው በጥናቱ ተካተዋል።

በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አብዛኛውን የቤት አቅርቦት ተፈጻሚ የሚሆነው በመንግሥት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ቤት አልሚ ድርጅቶች ተቋቁመው የማኅበረሰቡን የቤት ጥያቄ እየመለሱ መሆናቸው የሚበረታታ ነው።

በቤት አቅርቦት ላይ ለውጦች እየመጡ ቢሆንም አሁንም የመሬት አቅርቦት፣ እንዲሁም በዝቅተኛና በመካከለኛ ገቢ ላይ የሚገኙ ሰዎች ቤት ለመሥራት ቢፈልጉ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ነው።

👉 በአጠቃላይ ጥናት የተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታትና በጥናቱ የቀረቡ ግኝቶች መሬት ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የሚቀርቡ ይቀርባሉ ተብሏል።

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#ጥናት

" ሴቶችን በኢንተርኔት ላይ መሳደብ እና ማስፈራራት ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ የኢንተርኔት ላይ መግባቢያ መንገድ ሆኗል "

ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሬዚሊያንስ / #CIR / ጾታን መሰረት ያደረገ የኦንላይን ጥቃትና ትንኮሳ ተፅእኖዎች ላይ ያጠናውን ሰፊ ጥናት በቅርቡ ይፋ አድርጎ ነበር።

ጥናቱ ሁለት ክፍሎች ይዟል።

የመጀመሪያው የከዚህ ቀደም ጥናቶች ፤ በኢንተርኔት መድረኮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያላቸው / የነበራቸውንና ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ቃለ መጠይቅ የያዘ ነው።

ሁለተኛው በ3 (ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ X) የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ጥናት ያደረገ ነው።

በጥናቱ እንደተገለጸው ሴቶች ላይ የሚደርሱ የጥላቻ ንግግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተደረገው ጥናት ምን ተገኘ ?

ጥናቱ በ4 ቋንቋዎች (አማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ) የጥላቻ ንግግሮችን ከኢንተርኔት ላይ ለመለየት የሚያግዙ 2058 ጥቃት አዘል ቃላቶችን በመምረጥ ተደርጓል።

ቃላቶቹ በተከታታይ ውይይቶች እና ጥናቶች የተለዩ የ " ጥላቻ ንግግር " ን ይገልጻሉ የተባሉ ናቸው።

አጠቃላይ ከተሰበሰበው መረጃ 44.5 በመቶ የብሔር ጥላቻን ሲወክሉ ፤ 30.2 በመቶ ፆታን ኢላማ ያደረጉ ጥላቻ ንግግሮች ናቸው። ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ 17.5 ከመቶ ይይዛሉ።

ሴቶች (77.8 ከመቶ) ከወንዶች (22.2 ከመቶ) በላይ የጥላቻ ንግግር ይደረስባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ሴቶች (13.5 ከመቶ) ከወንዶች (9.2 ከመቶ) በለይ ‘#ዛቻ’ የያዙ ንግግሮችን ያስተናግዳሉ፡፡

#ስድቦች ’ ከአጠቃላይ ጥቃት 36.6 ከመቶ በመያዝ ዋና ድርሻ የሚይዙ ሲሆን ዛቻና ማስፈራሪያዎች ደግሞ 13.4 ከመቶ ይይዛል፡፡

በቃ ለመጠይቅ የተሳተፉ ሴቶች ምን አሉ?

" በኢንተርኔት ላይ ሴቶችን መሳደብ እና ማስፈራራት ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ የኢንተርኔት ላይ መግባቢያ መንገድ ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከ21 በመቶ በላይ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ፣ ጥቃት ፈጻሚዎች፣ ሃይማኖትን እንደሽፋን ተጠቅመው ጥቃት እንዳደረሱባቸው አንስተዋል።

በደረሰባቸው ጥቃት በማህበራዊ ትሥሥር ድረ-ገጾች ላይ እንዲሁም ከኢንተርኔት ውጪ ያሉ ማሀበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያቆሙ እና ዝምታን እንዲመርጡ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ጥናቱን በዚህ ያገኛሉ👇
https://www.info-res.org/tfgbvinethiopia

@tikvahethiopia
#ጥናት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር የሚንቀሳቀሰው የጄኖሳይድ አጣሪ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው አዲስ ጥናት በክልሉ የሚገኙ የሥራ አጦች ቁጥር እጅግ አሻቅቧል።

የአጣሪ ኮሚሽኑ ሰነድ ምን ይላል ?

የነፍስ ወከፍ ገቢ ከጥቅል ክልላዊ ምርት አኳያ (GDP Per Capita) ከጦርነቱ በፊት ነበረ ከተባለበት 845 ዶላር ወደ 10.2 ዶላር አሽቆልቁሏል።

የድህነት ምጣኔ ከ29.6 በመቶ ወደ 91.09 በመቶ አሻቅቧል።

የምግብ ደኅንነት ዋስትናን ማስጠበቅ ምጣኔ ከ74.20 በመቶ ወደ 18.73 በመቶ ወርዷል።

አጠቃላይ በየዓመቱ በአማካይ የሚሰበሰብ ሰብል በፊት ከነበረው 20,633,070 ኩንታል ወደ 5.2 ሚሊዮን ኩንታል ዝቅ ብሏል።

የአትክልት ዋጋ ግሽበት ከ8.5 በመቶ ወደ 179.8 በመቶ ከፍ ብሏል።

ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ሆነው ከቀረቡት መካከል አንዱ የሆነው የሥራ አጦች ምጣኔ ነው። ይህም ከጦርነቱ ጅማሮ በፊት ከነበረበት 17 በመቶ በአሁኑ ወቅት ከፍ ብሎ 74.1 በመቶ ላይ ደርሷል።

ኮሚሽኑ ያቀረበው የጥናት ውጤት የክልሉ ወጣቶች ማኅበር በተናጠል ባደረገው ጥናት ግኝት ላይም ተመላክቷል።

የማኅበሩ የጥናት ውጤት ምን ይላል ?

🔴 የሥራ አጥ ምጣኔው ባለፈው ዓመት ከነበረበት 81 በመቶ በዘንድሮው ዓመት ዝቅ ብሏል።

🔴ባለፈው ዓመት በክልሉ ከነበሩ 10 ወጣቶች ስምንቱ ሥራ አጥ ነበሩ።

🔴 በባለፈው ዓመት
ጥናት በክልሉ ከነበሩ አጠቃላይ ወጣቶች 40 በመቶ ያህሉ ቀዬአቸውን ለቀው ሥራ ፍለጋ የመሰደድ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠንቷል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 54 በመቶ ያህሉ ከ29 እስከ 35 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ምርታማ የሚባሉ ወጣቶች ናቸው።

🔴 በያዝነው ዓመት የሥራ አጥ ወጣቶች መጠን በስምንት በመቶ ቢቀንስም ወደ 12 በመቶ የሚጠጉ የክልሉ ወጣቶች የአካል ጉዳትና ጤና እክልን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ሥራ ለመፈለግም ሆነ ለመሥራት አልቻሉም።

🔴 ከሥራ አጥ ወጣቶች መካከል 23.4 በመቶው በየዕለቱ በሥራ ፍለጋ ላይ ቢሰማሩም በፋይናንስ እጥረት፣ በመሠረተ ልማት አለመሟላት፣ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ መሰናክሎችን በመሳሰሉ ዋና ዋና ጉዳዩች ምክንያትነት ሥራ ማግኘት አልቻሉም።

🔴 ከአጠቃላይ የጥናቱ ተሳታፊዎች 52 በመቶው ሥራ የማግኘትም ሆነ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅማቸው በኢኮኖሚያዊ መደላድሎች አለመሟላት እንደተደናቀፈባቸው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ወደ 46 በመቶ የሚጠጉት ደግሞ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ የሥራ ፍለጋ ሁኔታቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

🔴 ወጣቶች ሌሎች የሥራ ሁኔታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ እንደሆነ ከገለጿቸው ጉዳዩች መካከል፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶች አለመሟላት፣ የተለያዩ የጤና እክሎች፣ ማንነት፣ እንዲሁም ፆታና ዕድሜን መሠረት ያደረገ አድልኦና መገለል ተጠቃሽ ናቸው።


አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አካል በ2016 ዓ.ም. ብቻ በክልሉ 49 ወረዳዎች በተደረገ ጥናት 27,000 ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ ውጭ አገሮች ለመሰደድ ቀዬአቸውን ለቀው መውጣታቸውን ቤተሰቦቻቸው መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶች በብዛት እየተሰደዱ ካሉባቸው ሥፍራዎችም የኢሮብ ብሔረሰብ ወረዳዎችና የማዕከላዊ ትግራይ ዞን አካባቢዎች ይገኙበታል።

" በ2016 ዓ.ም. በኢሮብ ወረዳ ብቻ ከተሰበሰበ መረጃ 32 ወጣቶች ወደ ውጭ አገሮች በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ በረሃ ላይ በተለያዩ መንገዶች ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ተረድተዋል " ብለዋል።

ከክልሉ በተገኘ መረጃ በጂቡቲና በሶማሊያ በኩል ወደ የመን በሕገወጥ መንገድ ለመሰደድ ዜጎች ከ300 እስከ 500 ሺሕ ብር እየከፈሉ ናቸው።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የመረጃ ምንጭ፣ " ወጣቱ ለስደት ወጥቶ ሕይወቱ ያለፈ ወንድሙን ለቅሶ አርባ ቀን እንኳን ሳያወጣ ነው ተነስቶ ለስደት እየወጣ ያለው "  ብለዋል።

ሴቶች በደላሎቹ እጅግ ተፈላጊ መሆናቸውንና ሴቶችን ለሚያመጡ ወንዶች እስከ ነፃ ጉዞ ድረስ የሚደርስ ድርድር እንደሚያደርጉ ከስደተኞች መስማታቸውንም ተናግረዋል።

ወጣቶች በገፍ እየተሰደዱ ያለበትን ምክንያት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ " የመጀመሪያው የደኅንነት ጉዳይ ነው፣ ደኅንነት እየተሰማቸው አይደለም፡፡ በተለይ በድንበር አካባቢ ያለው ወጣት በአንድ በኩል የኤርትራ ኃይል በየቀኑ ሰውን እያፈሰ ሲወስድ ይመለከታል፡፡ ሕዝቡ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው። ሌላው የሚሰደደው የሥራ ዕድል ለመፍጠርም ሆነ ሥራ ለማግኘትም ያልቻለ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጦርነት እንዳያገረሽ ሥጋት ያለበትም እንዲሁ እየተሰደደ ነው " ብለዋል።

(ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው)

@tikvahethiopia