TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በኢትዮጵያ አማካይ የኤች አይ ቪ/ኤድስ #ስርጭት 0.9 መድረሱን #ጥናት አመለከተ። ጥናቱ የተካሄደው በዋናነት በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲሆን ጤና ሚኒስቴር፣ የአሜሪካ መንግስት የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል፣ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አይካፕ፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤትና ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ነው።

©ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰኔ_30 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፦

የውሃ:መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በወቅታዊ የኤሌክትሪክ ኃይል #አቅርቦት እና #ስርጭት ዙርያ ሐምሌ 01 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዐት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መገለጫ ይሰጣል ተብሏል። ሚዲያዎችም በመግለጫው ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

📩የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

🗞ቀን ሰኔ 30/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በማዕከል ደረጃ ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ከፍተኛ የሥራ ጫና ወደ አለባቸው ወረዳ እና ተቋማት #ስርጭት እንዲደረግ ወስኗል።

ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ እና ለህብረተሰብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ የተወሰነ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ይህንንም ውሳኔ ተቋማት ሙያዊ እና ተፈላጊ ችሎታን ታሳቢ አድርገው  እንዲያስተገብሩ እንዲደረግ ትዕዛዝ ተላልፏል።

በተጨማሪም አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ (Outsource) መስራትን የሚያስችል ውሳኔም ተላልፏል።

ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉት ሥራዎች ጥሩ እና ተፈላጊውን ውጤት ያመጣሉ ተብለው በጥናት የተለዩ አገልግሎቶች እንደሆኑ ነው የተጠቆመው።

Via Addis Ababa Communication

@tikvahethiopia