TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ምንም ትርጉም የሌለው ትዕዛዝ ነው " - ሩስያ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት (ICC) በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱ ተሰምቷል።

ፕሬዝዳንቱ ህጻናትን በሕገወጥ መንገድ ከዩክሬን ወደ ሩሲያ ማፈናቀልን ጨምሮ በጦር ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ሲል ነው የእስር ትዕዛዙን ያወጣባቸው።

እነዚህ ወንጀሎች የተፈጸሙት ካለፈው ዓመት የካቲት አጋማሽ ጀምሮ መሆኑኑ ተመላክቷል።

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት " ፕሬዝዳንት ፑቲን ህጻናትን በማፈናቀል እጃቸው አለበት " በሚል ክስ የመሰረተው በድርጊቱ በቀጥታ በመሳተፍ እንዲሁም ከሌሎች ጋር እንደፈጸሙት የሚያሳምን በቂ ምክንያት እንዳለው በማመልከት ነው።

በተጨማሪ የሩሲያው መሪ ህጻናቱን ከዩክሬን የሚያባርሩ ሌሎች አካላትን ለማስቆም ያላቸውን ሥልጣናቸውን ሳይጠቀሙ እንደቀሩ ነው ፍርድ ቤቱ ያሳወቀው።

ከፕሬዝዳንት ፑቲን በተጨማሪ የሩሲያ የህጻናት መብት ኮሚሽነር ማሪያ ሎቮቫ-ቤሎቫም በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ተፈላጊ ሰው ሆነዋል።

በፕሬዝዳንቱም ሆነ በኮሚሽነሯ ላይ የፍርድ ቤቱ የእስር ትዕዛዝ ቢወጣም ፍ/ቤቱ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ሥልጣን ግን የለውም።

ይህ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የሚያወጣው ትዕዛዝ ተፈጻሚ የመሆን መብት ያለው ባቋቋሙት እና ስምምነት በፈረሙ አገራት ውስጥ ብቻ ነው።

ሩሲያ የዚህ ስምምነት #ፈራሚ_ባለመሆኗ የፕሬዝዳንት ፑቲን ለፍርድ ቤቱ ተላልፎ የመሰጠት ጉዳይ የመነመነ ነው።

ሩሲያ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ " ምንም ትርጉም የለውም " ብላለች።

ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የሚቀርቡባትን መጠነ ሰፊ ጥሰቶች ክስ በተደጋጋሚ ውድቅ ስታደርግ መቆየቷ ይታወቃል።

መረጃው ከቢቢሲ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋሚያ ኮንፈረንስ በዚህ ሳምንት ለሁለት ቀናት ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸው ተገልጿል። የኮንፈረንሱ ውክልና አስተዳደር፣ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ተልዕኮ፣ የአስተዳደሩ አደረጃጀትና የስልጣን ክፍፍል ላይ ውይይት እንደተደረገበት እና ስምምነት ላይ እንደተደረሰባቸው ተገልጿል። ወደ ጦርነት ያስገቡ የትግራይ…
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ ማግኘታቸው ተነገረ።

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርጎ ነበር።

በዚህም #አቶ_ጌታቸው_ረዳን በትግራይ ክልል ለሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንታዊ እጩ አድርጎ አብላጫ ድምጽ መስጠቱን ቅርበት ያላቸው የፓርቲው ምንጮች እንደገለፁለት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) የትግርኛው አገልግሎት ክፍል ዘግቧል።

የአቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ኣባላት ሹመት፣ የክልሉ አመራሮች ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ጉዳይ ተወያይተው #ካፀደቁት በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ እንደሚጀምር ነው ' ቪኦኤ ትግርኛ ' ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ በዘገባው ያመለከተው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ " የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ብቻ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ተቋርጦ የነበረው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ባጃጆቹ በተመደቡላቸው መስመሮች ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። በመግለጫው ምን ተባለ ? - ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ለተፈጠሩ ችግሮች መንስኤ…
#AddisAbaba

ዛሬ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች በትራንስፖርት ቢሮ የተዘጋጁት መመሪያዎች መሰረት ወደ ስራ መመለሳቸው በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረን ተመልክተናል።

ባጀጆች ዳግም ወደ አገልግሎት ተመልሰው እየሰሩባቸው ያሉት መመሪያዎች ምንድናቸው ?

1. የዘርፉ የስምሪት መስመሮች በከተማዋ ዳርቻዎችና አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በሰፋፊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይቶች እና በተለዩ አንዳንድ የከተማው የውስጥ ለውስጥ አጫጭር መንገዶች ላይ የተወሰነ ነው።

2. በዚህ ስምሪት ስርዓት ውስጥ መሳተፍ የሚችሉት ኮድ 1 ሰሌዳ ያላቸው ባለሦስት እና ባለአራት እግር በተለምዶ ባጃጅ ተብለው የሚጠሩ ተሸከርካሪዎች ብቻ ናቸው።

3. በቢሮው በተለዩ የስምሪት መስመሮች ብቻ ነው አገልግሎት እየተሰጠ የሚገኘው።

4. የመጫን አቅም 3 ሰው ብቻ ነው።

5. ለየትኛውም ርቀት ታሪፍ 5 ብር ነው።

6. መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሰዓት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 03፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።

7. በዋና መንገድና አደባባይ ላይ የስምሪት መነሻና አገልግሎት አሰጣጥ አይፈቀድም፣ የነዳጅ ድጎማ አይደረገም።

@tikvahethiopia
" ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ ተይዟል " - UNICEF

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን እንደገና ለመክፈት ዕቅድ መውጣቱ ተገልጿል።

በትግራይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከመራቃቸው ባለፈ መምህራንም ለሁለት ዓመታት ደመወዝ አልተከፈላቸውም።

ትምህርት ቤቶቹን በመጪው #ሚያዝያ_ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ እንደተያዘም የዩኒሴፍ (UNICEF) የትምህርት ኃላፊ ቻንስ ብሪግስ ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ለBBC Focus on Africa ሬዲዮ ነው።

" በትግራይ ሙሉ በሙሉ የትምህርት ሥርዓቱ ፈርሷል። " ያሉት ቻንስ ብሪግስ " ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ 2.3 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው የሚያሳይ መረጃ አለን "  ብለዋል።

በመቐለ ከባለቤታቸው እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ነዋሪ የሆኑት አቶ መንግሥት ገብረመድኅን የእርስ በርስ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ሁለቱ ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር።

ትምህርት ከተቋረጠም በኋላ " እነሱን ለማስተማር ሞከርኩ፣ ነገር ግን መረጋጋት እና ትኩረታቸውን መሰብሰብ አልቻሉም " ብለዋል።

" የአየር ጥቃቶች እና የድሮን ጥቃቶች ድምጽ ይሰማሉ። ህጻናቱን ጠመንጃ ይዘው የሚሄዱ ወታደሮችንም ያያሉ። እነሱንም ለማስመሰል ይሞክራሉ። " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

በመቐለ ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ መንግሥት ለወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየቱን ተናግረዋል።

" ደመወዛችን አየተሰጠን ስላልነበር ልጆቻችን ምን እንደምንመግባቸው ያስጨንቀን ነበር። ስለዚህ እነሱን በማስተማር ላይ ማተኮር ፈታኝ ነበር። ነገር ግን ትናንትና ደመወዜን ተቀበልኩ፣ አሁን ለልጆቼም ልብስ እና ምግብ መግዛት እችላለሁ " ብለዋል።

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሚሊዮኖች ተማሪዎች  ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል ፤ መምህራን ደግሞ በጦርነት ምክንያት ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቆይቷል።

#ቢቢሲ #BBCFocusonAfrica

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

በሆቴሎች፤ በሱፐርማርኬቶች እና በቅርንጫፎቻችን በሚገኙት የፖስ ማሽኖቻችን የቪዛና ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ግብይትዎን ያቅልሉ፡፡

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

@berhanbanksc
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ማድረግ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በኢትዮጵያ ምን ያህል መስማት የተሳናቸው ሰዎች እንዳሉ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ከመስማት ጋር የተገናኘ ጉዳት ያለባቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል።

የምልክት ቋንቋዎች የራሳቸው ሰዋሰው፣ መዝገበ ቃላት እና ዘዬ ያላቸው የተሟሉ፣ ቋንቋዎች ሲሆኑ፤ ከውልደት ጀምሮ መስማት ለተሳናቸው ሕጻናት ደግሞ ብቸኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ነው፡፡

ከኢትዮጵያ የብሔር ብዝኃነት አንጻር ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑ ቢታወቅም፤ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የግድ አስፈላጊ የሆነውን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አላገኘም።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች። በዚህም የምልክት ቋንቋ ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ አለባት።

የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የሚኖራቸውን የተሳትፎ መጠንና የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ብሎም ሰብአዊ መብቶቻቸው ሙሉና ውጤታማ በሆነ ደረጃ እንዲረጋገጡ ለማስቻል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ሙሉ ጹሑፉን ለማንበብ https://ehrc.org/expertview

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia
#ደቡብ_አፍሪካ

• " የመንግሥት ለውጥ በምርጫ እንጂ በግርግር  አይመጣም " - ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ

• " መንግሥት እየተንቀጠቀጠ ነው ፤ ፈርቷል " - የራማፎሳ ተቃዋሚ ጁሊየስ ማሌማ (የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ)

• በተቃውሞው ሳቢያ የንግድ መደብሮች ገና ካሁኑ ሥጋት አድሮባቸዋል።

#በመጪው_ሳምንት በደቡብ አፍሪካ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ታቅዷል።

በዚህም ሳቢያ የአገሪቱ መንግሥት ቁልፍ የሚባሉ መሠረተ-ልማቶችን ለመጠበቅ እና የጸጥታ ጥበቃውን ለማጠናከር የሀገሪቱን ጦር (ወታደሮች) እንዳሰማራ ዶቼ ቨለ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ጁሊየስ ማሌማ የሚመሩት ግራ ዘመም የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ በመጪው ሰኞ በመላ ደቡብ አፍሪካ የሥራ ማቆም አድማ መጥራቱ ተነግሯል።

ፓርቲው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፖሳ የደቡብ አፍሪቃን ኤኮኖሚ በመሩበት ስልት፣ በመብራት እጥረት እና እየበረታ በሚሔደው የሥራ አጥነት ሳቢያ ከሥልጣን መልቀቅ አለባቸው የሚል አቋም አለው።

የደ/አፍሪቃ ጦር ለአገሪቱ ፖሊስ እገዛ እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውቋል።

ጦሩ በእጁ በሚገኙ የስለላ መረጃዎች መሠረት ሥጋት አለባቸው የተባሉ ቁልፍ ቦታዎችን ለመጠበቅ ከትላንት አርብ ጀምሮ ለአንድ ወር ወታደሮች አሰማርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ከጸጥታ አስከባሪ ተቋማት አቅም በላይ ለሚፈጠሩ ኩነቶች ወታደሮች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል።

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አንድ ዓመት የቀረው ሲሆን ፕሬዜዳንት ራማፎሳ የታቀደው ሰልፍ " ፖለቲካዊ ሴራ ነው "  የሚል አቋም አላቸው።

ፕሬዜዳንቱ ባለፈው ሐሙስ " ሥርዓተ-አልበኝነት እና ግርግር እንደማይፈቀድ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ራማፎሳ የመንግሥት ለውጥ " በምርጫ እንጂ በግርግር " እንደማይመጣም ገልጸዋል።

የኤኮኖሚ ነጻ አውጪዎች ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ትላንት በስዌቶ ለደጋፊዎቻቸው " ማንም አብዮትን ሊያስቆም አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" መንግሥት እየተንቀጠቀጠ ነው፤ ፈርቷል " ያሉት ማሌማ ራማፎሳ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቀዋል።

በተቃውሞው ሳቢያ የንግድ መደብሮች ገና ካሁኑ ሥጋት እንደገባቸው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" እናት እና ልጅን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል "

በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

ትናንት ምሽት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከምሽቱ 12:05 ሰዓት በንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ማንጎ ሰፈር ወንዝ ዳርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጎርፍ ገብቶ እንደነበር ኮሚሽኑ ገልጿል።

በዚህም እናትና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል ብሏል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ፥ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ የ3፣ የ13፣ የ15 እና የ46 ዓመት ሴት ናቸው በጎርፉ የተወሰዱት።

የ46 ዓመቷ ሴት በጎርፍ የተወሰዱት የ13 እና የ15 ታዳጊዎች ወላጅ እናት መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
የአሜሪካ ወረራ ...

የቀድሞ የአሜሪካ መሪ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ እሁድ 20 ዓመት ደፈነ።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ 20 ዓመት ሞልቶታል።

የዛሬ 20 አመት ጦርነቱ ሲጀመር አስደንጋጭ እና አስፈሪ የቦምብ ጥቃት ዘመቻ ባግዳድን አቀጣጥሏት ነበር።

በዚህ ወረራ የአሜሪካ ጦር በስልጣን ላይ የነበረውን የሳዳም ሁሴን መንግስት አፍርሶ ሳዳምን ከስልጣን አውርዷል።

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ እ.አ.አ ግንቦት 1 ቀን 2003 ዓ.ም ተልዕኳቸው መጠናቀቁን ቢያውጁም የሳዳም ባቲስት ፓርቲ አባላት እና ሌሎች አማፂያን ከአሜሪካ እና አጋር ኃይሎቿ ጋር ውጊያ በመቀጠላቸው ጦርነቱ ሊረዘም ችሏል።

ለወረራው ምክንያት የነበረው በኢራቅ አለ የተባለው " የጅምላ ጨራሽ ጦር መሳሪያ " ሲሆን ይህ ግን በኢራቅ አልተገኘም።

በአሜሪካ ወረራ እና እሱን ተከትሎ በቀጠለው ጦርነት የኢራቅ ነዋሪዎች ክፉኛ ዋጋ ከፍለዋል፤ በርከታ የአሜሪካ ወታድሮችም በጦርነቱ ህይወታቸው ጠፍቷል፣ አካላቸው ጎድሏል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂም ስታይንበርግን ጨምሮ በርካታ ተቺዎች አሜሪካ በኢራቅ ውስጥ ያደረገችውን ጣልቃ ገብነት / ወረራ " ጥበብ የጎደለው " ብለውታል።

ፕሬዝዳንት ኦባማ እ.አ.አ በ2011 የጦር ኃይላቸውን ከኢራቅ አስወጥተው የነበረ ቢሆንም ከሶስት አመት በኃላ ግን በኢራቅ ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ የተነሳውን አይኤስ ለመዋጋት በድጋሚ ገብተዋል።

ዛሬ የአሜሪካ ወታደሮች በኢራቅ የሚገኙ ሲሆን ግንኙነታቸው እ.አ.አ በ2003 እንደነበረው በጠላትነት ሳይሆን በቁልፍ አጋርነት መሆኑ ነው የሚነገረው።

በኢራቅ ጦርነት ምክንያት ህፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንን ጨምሬ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን ህይወት የጠፋ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ የአሜሪካ ወታደሮችም ተገድለዋል።

መረጃ ምንጭ ቪኦኤ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካ ወረራ ... የቀድሞ የአሜሪካ መሪ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ እሁድ 20 ዓመት ደፈነ። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ 20 ዓመት ሞልቶታል። የዛሬ 20 አመት ጦርነቱ ሲጀመር አስደንጋጭ እና አስፈሪ የቦምብ ጥቃት ዘመቻ ባግዳድን አቀጣጥሏት ነበር። በዚህ ወረራ የአሜሪካ ጦር በስልጣን ላይ የነበረውን የሳዳም ሁሴን መንግስት አፍርሶ ሳዳምን ከስልጣን…
#ኢራቅ

ዛሬ የቀድሞ #የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ቡሽ ኢራቅ ላይ ወረራ እንዲፈፀም ካዘዙ 20 ዓመት የሞላው ሲሆን በወቅቱ ለወራር ምክንያት የተባለው ኢራቅ ውስጥ አለ የተባለው የጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያ ነው።

ነገር ግን ይህ " አለ " የተባለው የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አልተገኘም።

እኤአ በ2003 ወረራው ከመፈፀሙ ከወራት በፊት በወቅቱ የኢራቅ ፕሬዜዳንት የነበሩት እና ከወራራው በኃላ #በስቅላት የተገደሉት ሳዳም ሁሴን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ (መስከረም 19/2002) ላይ እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር ፦

" ኢራቅ ከኒውክሌር፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል መሳሪያዎች ሁሉ የጸዳች መሆኗን ከዚህ በፊት አውጃለሁ።

#የአሜሪካ_አስተዳደር የመካከለኛው ምስራቅን ዘይት ለመቆጣጠር ኢራቅን ለማጥፋት ይፈልጋል ፤ ይህን ተከትሎ ፖለቲካውን እንዲሁም የመላው ዓለምን የዘይት / ነዳጅ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ይቆጣጠራል። "

@tikvahethiopia