TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ትምህርት ቤቶቹን በመጪው ሚያዝያ ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ ተይዟል " - UNICEF

በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን እንደገና ለመክፈት ዕቅድ መውጣቱ ተገልጿል።

በትግራይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከመራቃቸው ባለፈ መምህራንም ለሁለት ዓመታት ደመወዝ አልተከፈላቸውም።

ትምህርት ቤቶቹን በመጪው #ሚያዝያ_ወር እንደገና ለመክፈት ዕቅድ እንደተያዘም የዩኒሴፍ (UNICEF) የትምህርት ኃላፊ ቻንስ ብሪግስ ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ለBBC Focus on Africa ሬዲዮ ነው።

" በትግራይ ሙሉ በሙሉ የትምህርት ሥርዓቱ ፈርሷል። " ያሉት ቻንስ ብሪግስ " ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ 2.3 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው የሚያሳይ መረጃ አለን "  ብለዋል።

በመቐለ ከባለቤታቸው እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ነዋሪ የሆኑት አቶ መንግሥት ገብረመድኅን የእርስ በርስ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ወቅት ሁለቱ ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ነበር።

ትምህርት ከተቋረጠም በኋላ " እነሱን ለማስተማር ሞከርኩ፣ ነገር ግን መረጋጋት እና ትኩረታቸውን መሰብሰብ አልቻሉም " ብለዋል።

" የአየር ጥቃቶች እና የድሮን ጥቃቶች ድምጽ ይሰማሉ። ህጻናቱን ጠመንጃ ይዘው የሚሄዱ ወታደሮችንም ያያሉ። እነሱንም ለማስመሰል ይሞክራሉ። " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

በመቐለ ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ መንግሥት ለወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየቱን ተናግረዋል።

" ደመወዛችን አየተሰጠን ስላልነበር ልጆቻችን ምን እንደምንመግባቸው ያስጨንቀን ነበር። ስለዚህ እነሱን በማስተማር ላይ ማተኮር ፈታኝ ነበር። ነገር ግን ትናንትና ደመወዜን ተቀበልኩ፣ አሁን ለልጆቼም ልብስ እና ምግብ መግዛት እችላለሁ " ብለዋል።

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሚሊዮኖች ተማሪዎች  ከትምህርት ገበታቸው ርቀዋል ፤ መምህራን ደግሞ በጦርነት ምክንያት ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቆይቷል።

#ቢቢሲ #BBCFocusonAfrica

@tikvahethiopia