TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የእሳት አደጋ~አዲስ አበባ‼️

በዛሬው ዕለት በመዲናዋ ሶስት ቦታዎች #የእሳት_አደጋ መከሰቱን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ቁስቋም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኝ ንብረትነቱ የንግድ ባንክ በሆነ የቤት እቃዎች መጋዘን ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

ባለስልጣኑም ሁለት ከባድ ተሽከርካሪ፣ 5 ሺህ ሊትር ውሃና 7 የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችን በማሰማራት 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ቅርንጫፍ ጀርባ በሚገኝ አንድ የመኪና ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አንድ ተሽከርካሪና 10 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም፥ ግምቱ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሆነ ንብረት ማዳን ተችሏል።

ከዚህም ሌላ ዛሬ ከሰዓት በአንዋር መስኪድ የሴቶች መግቢያ በር ላይ በሚገኝ አንድ የንግድ ሱቅ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ 30 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
ከአደጋው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነጭ ሳር🔝በአርባምንጭ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ነጭሳር ብሔራዊ ፓርክ ምሽቱን በተከሰተ #የእሳት_አደጋ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ ጎንደር‼️

በደቡብ ጎንደር ዞን ትናንት ምሽት አንድ #መስጂድ ላይ #የእሳት_አደጋ ደረሰ። በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ጃራ ገዶ አካባቢ አደጋው የደረሰው ትላንት ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ነው፡፡

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #መላኩ_አላምረው እንደተናገሩት የቃጠሎ አደጋው በጨለማ መፈፀሙ ከድርጊቱ ጀርባ #የተደራጀ ቡድን መኖሩን ያመላክታል፡፡ ይህም የዳር አገሩን ግጭት ወደ መሃል አገር ለማምጣት ሙከራ እየተደረገ መሆኑን ክልሉ መገንዘቡን አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡

ክልሉ የአደጋውን ሁኔታ የሚከታተል #አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም አመልክቷል፡፡ ቃጠሎ የደረሰበትን መስጂድ ለማጥፋት የአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ማድረጉንና መስጅዱን መልሶ ለመገንባት ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደቡብ ጎንደር እስቴ ላይ በሁለት መስጅዶች ቃጠሎ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ 6 ተጠርጣሪዎችን የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡

ከመስጊድ ቃጠሎው ጀርባ በአካባቢው #የሚንቀሳቅስ ህቡዕ ቡድን መኖሩ እንደተደረሰበትና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ክልሉ እየሰራ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በሀላባ ቁሊቶ በሚገኘው #ፖስታ_ቤት #የእሳት_አደጋ መድረሱን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የአደጋው ምክንያት ባይታወቅም እሳቱን #ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጀሞ 2👆

ዛሬ በአዲስ አበባ ጀሞ 2 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ ባሉ መንደሮች በተነሳ ድንገተኛ #የእሳት_አደጋ በንብረት ላይ #ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ፡፡ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ የተነሳው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በአካባቢው ላይ በሚገኙ የሲልንደር ማከፋፈያ ሱቆች ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር~የትላንት ማታው የእሳት አደጋ👆

በባሕር ዳር ከተማ በተከሰተ #የእሳት_አደጋ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የአደጋው መንስኤ እና የደረሰው ጉዳት ላይ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

እንደ ፖሊስ መረጃ ቃጠሎው የተከሰተው ትናንት ማታ 5፡00 አካባቢ ነው፡፡ በዚህም የሰው ሕይወት ማለፉን፤ በአካል እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ስለአደጋው መንስኤ እና ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም ነው መምሪያው የገለጸው፡፡

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ መምሪያው ዝርዝር መረጃውን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ ከወራት በፊት በደረሰ የእሳት አደጋ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸው እና የከተማ አስተዳደሩና የከተማዋ ነዋሪዎች ተጎጂዎችን የማቋቋም ሥራ እያከናወኑ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert አዲስ አበባ አቃቂ ገበያ #የእሳት_አደጋ መነሳቱን በአካባቢው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰች ጥቆማ አድርሰዋል። ወደአካባቢው የእሳት አደጋ መኪናዎች ደርሰዋል። በአካባቢው የመብራት ኃይልም ተቋርጧል። ለሚመለከተው አካል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የእሳት_አደጋ_በጅግጅጋ

በጅግጅጋ ከተማ በ ቀበሌ 02 በልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ትላንት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

መነሻ መንስዔው ያልታወቀው እሳቱ የተነሳው ከአንድ ሱቅ መሆኑ ተገልጿል።

በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ የተገለፀ ሲሆን እሳቱ በፍጥነት በመዛመቱ 7 የንግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ አድረሷል።

ድምሩ ወደ 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ነው።

#እሳት_አደጋ_በመቅደላ_ወረዳ

ትላንት ምሽት በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

የእሳት አደጋው መነሀሪያ ሸድ ላይ የተከሰተ ነበር።

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን እና ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣራ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ዘይቤ ድረገፅ፣ የመቅደላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የእሳት_አደጋ_በሀዲያ_ዞን

በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች ፦
- ኤራ ጌሜዶ፣
- ኩናፋ
- ጉና ሜጋቾ በደረሰ እሳት አደጋ 4 መቶ 36 የቤተሰብ አባላት መፈናቀላቸውን የዞኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት አሳውቋል።

ፅህፈት ቤቱ አደጋው የተፈጥሮ እሳት አደጋ ነው ብሏል።

በደረሰው አደጋ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መዉደሙ ተጠቁሟል፡፡

በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያዩ የእህል ዘሮች ፣ 18 የንብ ቀፎዎች፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች እና በአካባቢው የነበሩ የጓሮ አትክልቶች በድምሩ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል።

በሌላ መረጃ ፦

በምዕራብ ሶሮ ወረዳ በጃቾ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ250 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል።

አደጋው ታህሳስ 18 ከምሽቱ 2፡30 በመብራት ኮንታክት የደረሰ መሆኑን የወረደው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

አደጋው ህብረተሰቡና የፖሊስ አካላት ባደረጉት ርብርብ ወደ ሌሎች ሱቆችና መኖርያ ቤቶች ሳይሻገር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገልጿል።

(ሀዲያ ዞን ኮሚኒኬሽን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የእሳት_አደጋ

ከየካቲት ወር መጀመሪያ እስከአሁን የተከሰቱ የእሳት አደጋዎች፦

#AddisAbaba📍

- በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ሂርቱ ሞጆ ተብሎ በሚጠራው የጥብቅ ደን ውስጥ ለቆሻሻ ተብሎ የተለኮሰ እሳት ባስከተለው አደጋ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጎማ ተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ አነስተኛ ሆቴል በተከሰተ አደጋ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት መውድሟል።

- በጉለሌ ክፍለ ከተማ በእፅዋት ማእከል በተነሳ የሰደድ እሳት 10ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ለውድመት ተዳርጓል።

- በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታ ኮልፌ እፎይታ ገበያ ማዕከል ፊትለፊት በአራት የንግድ ሱቆቸ በሆኑ የጫማ ማምረቻ እና መሸጫ እንዲሁም ጨርቃ ጨርቅ መሸጫ ላይ በደረሰ ድገተኛ የእሳት አደጋ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

- በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል በተባለ አከባቢ በዶልፊን ኢትዮጲያ የሳሙናና ሻምፖ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ1 ሚሊዮን 85 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

- በአዲስ ከ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መሳለሚያ አከባቢ አራት የንግድ ሱቆች ላይ እና ወረዳ 1 መርካቶ አከባቢ 3 ንግድ ሱቆች በተጨማሪም የካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዘፍነሽ ህንፃ አከባቢ በሶስት ንግድ ሱቆች ላይ በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወደመ።

- በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ገረጂ ኖክ ማደያ 40/60 ኮንዶሚኒየም 13ኛ ፎቅ ላይ ለኮንስትራክሽን ግብዓት የሚውሉ በደረሰ የእሳት አደጋ የ200 ሺህ ብር ንብረት ወድሟል።

ይቀጥላል👇