TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደቡብ ጎንደር‼️

በደቡብ ጎንደር ዞን ትናንት ምሽት አንድ #መስጂድ ላይ #የእሳት_አደጋ ደረሰ። በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ጃራ ገዶ አካባቢ አደጋው የደረሰው ትላንት ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ነው፡፡

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #መላኩ_አላምረው እንደተናገሩት የቃጠሎ አደጋው በጨለማ መፈፀሙ ከድርጊቱ ጀርባ #የተደራጀ ቡድን መኖሩን ያመላክታል፡፡ ይህም የዳር አገሩን ግጭት ወደ መሃል አገር ለማምጣት ሙከራ እየተደረገ መሆኑን ክልሉ መገንዘቡን አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡

ክልሉ የአደጋውን ሁኔታ የሚከታተል #አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም አመልክቷል፡፡ ቃጠሎ የደረሰበትን መስጂድ ለማጥፋት የአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ማድረጉንና መስጅዱን መልሶ ለመገንባት ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደቡብ ጎንደር እስቴ ላይ በሁለት መስጅዶች ቃጠሎ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ 6 ተጠርጣሪዎችን የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡

ከመስጊድ ቃጠሎው ጀርባ በአካባቢው #የሚንቀሳቅስ ህቡዕ ቡድን መኖሩ እንደተደረሰበትና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ክልሉ እየሰራ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia