TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የስራ ሀላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ዝናቡ_ቱኑ፡፡ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል፡፡

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል ነው ተብሏል፡፡

ዘርፉ እየተለየ ምርመራ የማድረግና ተጠያቂዎችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የ100 ቀን እቅድ አውጥቶ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እየሰራ መሆኑን ተሰምቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

በሌብነትና በሙስና የተጠረጠሩ ዋና ዋና የመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይህን ያለው ከተያዘው ወር መጀመሪያ ጀምሮ ባለፉት 100 ቀናት አከናውናቸዋለሁ ያላቸውን ተግባራት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡

በየትኞቹ ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ እንደተጀመረ ለመናገር አሁን ጊዜው አለመሆኑን የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ተናግረዋል፡፡

የሌብነት፣ የሙስናና የምዝበራ ተግባራት ተፈፅሞባቸዋል የተባሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በጥናት ተለይተው ምርመራ መጀመሩን አቶ ዝናቡ ተናግረዋል።

ህገወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውርን፣ የመንጋ ፍትህን እና ስርዓት አርበኝነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ረቂቅ የህግ ማሻሻያዎች መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ተናገረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ያለው የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ የተንዛዛ ምልልስ የበዛበትና ፍትሃዊነት የጎደለው በመሆኑ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ሊወጣ ነው‼️

ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ልታወጣ መሆኗን አስታወቀች።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ #የጥላቻ_ንግግርን የተመለከተና ተጠያቂነትን የሚያመጣ አዲስ ረቂቅ ህግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደገለጹት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ሃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሀሰት ወሬዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በመሆናቸው መንግስት ይህን አደጋ ለማስወገድ ህጋዊ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር በማርቀቅ ላይ ነው።

ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ምሁራን አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

የጥላቻ ንንግሮች የዓለማችን የወቅቱ ፈተና እንደሆኑ ይገለጻል።

በሃገረ አሜሪካ የጥላቻ ንግግር ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር ተያይዞ ሰፊ የውይይት አጀንዳ የከፈተ ጉዳይ ነው።

አሜሪካ በህገመንግስቷ የመጀመሪያ ክፍል ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሳይሸራረፍ እንዲከበር ማድርጓ ለጥላቻ ንግግር መበራከት አስተዋጽኦ አድርጓል የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም ህዝብን ከህብ የሚያጋጩ፣ ሁከትን የሚፈጥሩና ሰላምን የሚያውኩ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ግን አሜሪካ ጠበቅ ያለ ርምጃ ትወስዳለች።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መምጣትና መስፋፋት ለጥላቻ ንግግሮች መበራከት አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚገልጹ የዘርፉ ባለሙያዎች ዓለማችን ከገጠሟት የጊዜው ብርቱ አደጋዎች አንዱ እንደሆነም ያስምራሉ።

ኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግሮች ሰላባ ለመሆኗ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚከሰቱ #ግጭቶች አይነተኛ ማሳያ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የጥላቻ ንግግሮችና #ሀሰተኛ_ወሬዎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ሰበብ ምክንያት መሆናቸውን እንዳመነበት ገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ይህን አደጋ ለመቀነስ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ገደብና ተጠያቂነት የሚያሰፍን ህግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

አቶ ዝናቡ እንዳሉት ኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ላይ መገኘቷን ተከትሎ ለጀመረችው የለውጥ ጎዳና እንቅፋት የሚሆኑትን ጉዳዮች በመለየት በህግ ልትፈታቸው ተዘጋጅታለች።

በተለይም ለህዝብ የሚቀርቡ ንግግሮችና የሚተላለፉ መልዕክቶችን በተመለከተ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ነው አቶ ዝናቡ የገለጹት።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መበራከት ከጥቅማቸው እኩል ጉዳቶችንም ማስከተላቸውን የጠቀሱት አቶ ዝናቡ በጥላቻ ንግግሮችና ሃላፊነት በጎደላቸው እንቅስቃሴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።

በመሆኑም መንግስት እነዚህን ግጭት ቀስቃሽና ሰላም አዋኪ የሆኑ የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቆም ረቂቅ ህግ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ለውይይት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

አንዳንድ ምሁራን ጉዳዩ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋው ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሳንሱር ማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ህጉ በምን ዓይነት መልኩ ችግሩን ለማስቀረት እንዳሰበ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነም ይገልጻሉ።

የጥላቻ ንግግሮችን በህግ ለማስቀረት የሚቻል ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ነው ምሁራን የሚገልጹት።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድብቅ እስር ቤቶቹ‼️

በአዲስ አበባ የተገኙት 7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች #ንብረትነታቸው የቤቶች ኮርፖሬሽን መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለሸገር ራድዮ ተናገረ፡፡

ዜጎች የተለያየ ስቃይ እና እንግልትን አሳልፈውባቸዋል የተባሉት እነዚህ ድብቅ እስር ቤቶች በቀድሞው የኪራይ ቤቶች ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በአሁኑ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሲተዳደሩ እንደቆዩ #ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደነገሩን ከ7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች መካከል የሚደረግባቸው
ምርመራ ተጠናቆ የተወሰኑት ለቤቶች ኮርፖሬሽን ተመልሰዋል፡፡ የቀሩት ግን የሚካሄደው ምርመራ ስላላለቀ ታሽገው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በድብቅ እስር ቤትነት ሲያገለግሉ የቆዩት ቤቶች በየትኛው ክፍለ ከተማና ወረዳ የሚገኙ እንደሆኑ ግን አቶ ዝናቡ በግልፅ ለመናገር #አልፈቀዱም፡፡

#የቤቶች_ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚያስተዳድራቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶቹን ገሚሱን ለመንግስት ሹማምንት በመስጠት የተረፉትንም ለተለያዩ ግለሰቦች በዝቅተኛ ዋጋ #በማከራየት ያስተዳድራል፡፡

ድብቅ እስር ቤት ሆነው ቆይተዋል የተባሉት ቤቶች ኮርፖሬሽኑ ለባለስልጣናት ከሰጣቸው መኖሪያዎች መካከል ይሁኑ ወይንም ሌላ እስካሁን አልታወቀም፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

"ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ የሱማሌ ክልል #ባለስልጣናትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት #ተጠናቋል"- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
.
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ዛሬ ከሰዐት በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት #እንዲጠፋ፣ ህገመንግስታዊ ስርዐትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ንብረት እንዲወድምና በተያያዥ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሌሎቹ 40 ግን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተሸሽገዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ዝናቡ ገለፃ ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በሀገር ውስጥ የተደበቁትንም አፈላልጎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች #ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ መብታቸውን #በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት አቶ ዝናቡ ህዝቡ የተሸሸጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በተመለከተ ከክልሉ ጋር እየሰራን ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
.
.

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ አርብ ጥር 17 ቀን ከሰዓት በኋላ በሰጠው መግለጫ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች ተነስቶ ከነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ሳከናውነው የቆየሁትን ምርመራ #አጠናቅቄያለሁ ብሏል።

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ተመስገን_ላጲሶ በበኩላቸው ለምርመራው መነሻ የሆነው ከሐምሌ 28 እስከ 30 2010 ዓ.ም የተፈፀሙ ወንጀሎች ቢሆኑም በምርመራው ሂደት አቶ አብዲ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንድንመረምር የሚያስችሉ ማስረጃዎችን አግኝተናል ብለዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ምርመራውን ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የመረጃ ደህንነት ጽሕፈት ቤት በጋራ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

ኃላፊው ምርመራው አምስት ወራት የፈጀው የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የተሳተፉበት በመሆኑ ይህ ወንጀሉን ውስብስብ ማድረጉን አስረድተዋል።

ከሶማሌ ብሔር ውጭ የሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ነበሩ ባሏቸው ጥቃቶች የተሳተፉ ናቸው የተባሉ 46 ተጠርጣሪዎችን ሕገ መንግሥትን ለመናድ በመሞከር፣ በማነሳሳት፣ በአስቃቂ ግድያና በአስገድዶ መድፈር ከሰናል ብለዋል ኃላፊው

ይሁን እንጂ ከተከሳሾቹ መካከል በቁጥጥር ስር ውለው የሚገኙት ስድስት ብቻ ናቸው። ሌሎቹ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ተደብቀው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አቶ ዝናቡ በቀድሞው የክልሉ መንግሥት በተደራጀ እና በተጠና መልኩ ዕቅድ ተይዞ እና አስፈላጊ የሰው ኃይልም ቀርቦ የተከናወኑ ናቸው ባሏቸው ጥቃቶች በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል፣ ከዚህም ውስጥ በእሳት በማቃጠል፣ አንገት በመቅላት መግደል፣ እንዲሁም በህይወት እያሉ መቅበር ተከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል።

"የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ዑመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምርመራ ሪፖርቱ ተረድተናል" ያሉት አቶ ዝናቡ ከፌዴራል የሚመጣ ኃይልን እንመክታለን በሚል የክልሉ ኃላፊዎች ያስተባብሩ እንደነበርም ገልፀዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንደተናገሩት የ58 ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 50 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል ብለዋል። እርሳቸው እንዳሉት አርባ ሁለቱ አንድ ላይ፣ ስምንቱ ደግሞ ሌላ ቦታ በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል። በተጨማሪ ሌሎች 200 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ቢገኙም የእርሱ ምርመራ ገና አልተጠናቀቀም።

በምርመራ ተደረሰበት በተባለው ግድያም የኦርቶዶክስ እምነት ካህናት እና ምዕመናን በቤተ ክርስትያን ግቢ ውስጥ ተገድለዋል፤ ተቀብረዋል ተብሏል።

እንደ አቶ ዝናቡ 266 ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 10 ሴቶች ሄጎ በሚባለው ጥቃት አድራሽ ቡድን እና በክልሉ ልዩ ኃይል ተደፍረዋል፤ ይሁንና ይህ ቁጥር መደፈራቸውን የደበቁ ሴቶች የሚኖሩ በመሆኑ ከፍ ሊልም ይችላል ተብሏል።

የተዘረፈ እና የተቃጠለ ንብረት ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል ብለዋል አቶ ዝናቡ

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ስለዋሉት አቶ በረከትና አቶ ታደሰን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ምርመራውን የሚያከናውነው የአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ ነው፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አይደለም፤ ስለዚህ የምንለው የለም" ብለዋል።

አክለውም የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተም ካልተያዙ ሰዎች መካከል እንደሚገኙ አመልክተው፤ በመሆኑም ይህንን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራን ነው፤ ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከጅግጅጋ ብጥብጥ ተጠርጣሪዎች መካከል ደግሞ የተወሰኑት ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ እርሱን በተመለከተም ከክልሉ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል።

አሁን ባለው የምርመራ ሂደት አቶ አህመድ ሽዴ ከተጠርጣሪዎች መካከል እንደማይገኙበትም ጠቁመዋል።

ምንጭ:- BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታወቁ።

በመቶ ቀን ዕቅዱ ተፈጻሚ ከሚሆኑት ተግባራት መካከል የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ ሰዎች የሕግ ተጠያቂ የሚሆኑበትን የአሰራር ስርዓት በመዘርጋትና ተፈጻሚነቱን ማረጋገጥ፣ በሌሎች በተመረጡ ዋነኛ ሴክተሮችና ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሙስና ወንጀል ምርመራና ክስ ስራ መጀመር፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ሪፎርም ዕገዛ በማድረግ የዴሞክራሲያዊ ምህዳሩን የበለጠ ማስፋት፣ የምርጫ ሕጎችን ማጠቃለልና ማፀደቅ፣ የፀደቀውን የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በሙሉ አቅም እንዲተገበር ኤጄንሲውን መምራትና መደገፍ፣ የተያዙና የተከሰሱ የታራሚዎች አያያዝ ለማሻሻል ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀትና መተግበር፣ የፀረ ጥላቻ ንግግር ወንጀል ሕግ ማውጣትና መተግበር፣ የህብረተሰቡን ተሳትፎና ግንዛቤ ለማሳደግ በፀደቁና በሚሻሻሉ ሕጎች ዙርያ በተመረጡ ክልሎችና ክፍለ ከተሞች ለመቶ ሺ ሰዎች የምክክር መድረኮች እንደሚካሄዱ አቶ ዝናቡ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሂደት ላይ ያሉ ሕጎች እንደ የፀረ ሽብርተኝነት ረቂቅ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ማሻሻያ አዋጅ፣ የምርጫ ሕግ፣ የጦር መሳሪያ አያያዝና አስተዳደር አዋጅ፣ የመረጃ ነፃነትና የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣ የኃይል አጠቃቀም አዋጅ፣ የማረሚያ ቤት ኮሚሽንን እንደገና ማቋቋያ ረቂቅ አዋጅ የመሳሰሉት ላይ በዋናነት ትኩረት የሚሹ ጉዳዬች በመሆናቸው ተቋሙ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ እንደሚያከናውን ጭምር አብራርተዋል፡፡

ምንጭ፦ የፌዴራል ጠ/አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia