TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በተመለከተ ከክልሉ ጋር እየሰራን ነው" ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
.
.

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ አርብ ጥር 17 ቀን ከሰዓት በኋላ በሰጠው መግለጫ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና ሌሎችም አካባቢዎች ተነስቶ ከነበረው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ ሳከናውነው የቆየሁትን ምርመራ #አጠናቅቄያለሁ ብሏል።

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ፣ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ተመስገን_ላጲሶ በበኩላቸው ለምርመራው መነሻ የሆነው ከሐምሌ 28 እስከ 30 2010 ዓ.ም የተፈፀሙ ወንጀሎች ቢሆኑም በምርመራው ሂደት አቶ አብዲ የክልሉ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንድንመረምር የሚያስችሉ ማስረጃዎችን አግኝተናል ብለዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ምርመራውን ፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የመረጃ ደህንነት ጽሕፈት ቤት በጋራ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

ኃላፊው ምርመራው አምስት ወራት የፈጀው የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የተሳተፉበት በመሆኑ ይህ ወንጀሉን ውስብስብ ማድረጉን አስረድተዋል።

ከሶማሌ ብሔር ውጭ የሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ነበሩ ባሏቸው ጥቃቶች የተሳተፉ ናቸው የተባሉ 46 ተጠርጣሪዎችን ሕገ መንግሥትን ለመናድ በመሞከር፣ በማነሳሳት፣ በአስቃቂ ግድያና በአስገድዶ መድፈር ከሰናል ብለዋል ኃላፊው

ይሁን እንጂ ከተከሳሾቹ መካከል በቁጥጥር ስር ውለው የሚገኙት ስድስት ብቻ ናቸው። ሌሎቹ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ተደብቀው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

አቶ ዝናቡ በቀድሞው የክልሉ መንግሥት በተደራጀ እና በተጠና መልኩ ዕቅድ ተይዞ እና አስፈላጊ የሰው ኃይልም ቀርቦ የተከናወኑ ናቸው ባሏቸው ጥቃቶች በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል፣ ከዚህም ውስጥ በእሳት በማቃጠል፣ አንገት በመቅላት መግደል፣ እንዲሁም በህይወት እያሉ መቅበር ተከናውኗል ሲሉ ተናግረዋል።

"የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ዑመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከምርመራ ሪፖርቱ ተረድተናል" ያሉት አቶ ዝናቡ ከፌዴራል የሚመጣ ኃይልን እንመክታለን በሚል የክልሉ ኃላፊዎች ያስተባብሩ እንደነበርም ገልፀዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንደተናገሩት የ58 ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 50 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል ብለዋል። እርሳቸው እንዳሉት አርባ ሁለቱ አንድ ላይ፣ ስምንቱ ደግሞ ሌላ ቦታ በጅምላ ተቀብረው ተገኝተዋል። በተጨማሪ ሌሎች 200 ሰዎች በጅምላ ተቀብረው ቢገኙም የእርሱ ምርመራ ገና አልተጠናቀቀም።

በምርመራ ተደረሰበት በተባለው ግድያም የኦርቶዶክስ እምነት ካህናት እና ምዕመናን በቤተ ክርስትያን ግቢ ውስጥ ተገድለዋል፤ ተቀብረዋል ተብሏል።

እንደ አቶ ዝናቡ 266 ሰዎች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 10 ሴቶች ሄጎ በሚባለው ጥቃት አድራሽ ቡድን እና በክልሉ ልዩ ኃይል ተደፍረዋል፤ ይሁንና ይህ ቁጥር መደፈራቸውን የደበቁ ሴቶች የሚኖሩ በመሆኑ ከፍ ሊልም ይችላል ተብሏል።

የተዘረፈ እና የተቃጠለ ንብረት ከ421 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል ብለዋል አቶ ዝናቡ።

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ስለዋሉት አቶ በረከትና አቶ ታደሰን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ምርመራውን የሚያከናውነው የአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ ነው፤ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አይደለም፤ ስለዚህ የምንለው የለም" ብለዋል።

አክለውም የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተም ካልተያዙ ሰዎች መካከል እንደሚገኙ አመልክተው፤ በመሆኑም ይህንን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራን ነው፤ ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከጅግጅጋ ብጥብጥ ተጠርጣሪዎች መካከል ደግሞ የተወሰኑት ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ እርሱን በተመለከተም ከክልሉ ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል።

አሁን ባለው የምርመራ ሂደት አቶ አህመድ ሽዴ ከተጠርጣሪዎች መካከል እንደማይገኙበትም ጠቁመዋል።

ምንጭ:- BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia